Skip to content
← Isaiah

Chapter 7 · Amharic

Isaiah

1እንዲህም፡ኾነ፤በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዖዝያን፡ልጅ፡በኢዮአታም፡ልጅ፡በአካዝ፡ዘመን፡የሶርያ፡ንጉሥ፡ ረአሶን፡የእስራኤልም፡ንጉሥ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ፋቁሔ፡ኢየሩሳሌምን፡ሊወጉ፡ወጡ፥ሊያሸንፏትም፡አልቻሉም።

2ለዳዊትም፡ቤት፦ሶርያ፡ከኤፍሬም፡ጋራ፡ተባብረዋል፡የሚል፡ወሬ፡ተነገረ፤የርሱም፡ልብ፡የሕዝቡም፡ ልብ፡የዱር፡ዛፍ፡በነፋስ፡እንድትናወጥ፡ተናወጠ።

3እግዚአብሔርም፡ኢሳይያስን፡አለው፦አንተና፡ልጅኽ፡ያሱብ፡አካዝን፡ትገናኙት፡ዘንድ፡በልብስ፡ዐጣቢው፡ ዕርሻ፡መንገድ፡ወዳለው፡ወደ፡ላይኛው፡የኵሬ፡መስኖ፡ጫፍ፡ውጡ፤

4እንዲህም፡በለው፦ተጠበቅ፥ዝምም፡በል፤ስለ፡እነዚህ፡ስለሚጤሱ፡ስለ፡ኹለት፡የዕንጨት፡ ጠለሸቶች፥ስለ፡ሶርያና፡ስለ፡ረአሶን፡ስለ፡ሮሜልዩም፡ልጅ፡ቍጣ፡አትፍራ፥ልብኽም፡አይድከም።

6ሶርያና፡ኤፍሬም፣የሮሜልዩም፡ልጅ፦ወደ፡ይሁዳ፡እንውጣ፡ እናስጨንቀውም፥እንስበረውም፥የጣብኤልንም፡ልጅ፡እናንግሥበት፡ብለው፡ክፋት፡ስለ፡መከሩብኽ፤

7ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ምክር፡አይጸናምና፥አይኾንም።

8የሶርያ፡ራስ፡ደማስቆ፡ነው፥የደማስቆም፡ራስ፡ረአሶን፡ነው፤በስድሳ፡ዐምስት፡ዓመት፡ውስጥ፡ኤፍሬም፡ ይሰባበራልና፥ሕዝብ፡አይኾንም፤

9የኤፍሬምም፡ራስ፡ሰማርያ፡ነው፥የሰማርያም፡ራስ፡የሮሜልዩ፡ልጅ፡ነው።ባታምኑ፡አትጸኑም።

10እግዚአብሔርም፡ደግሞ፡አካዝን፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረው፦

11ከጥልቁ፡ወይም፡ከከፍታው፡ቢኾን፡ከአምላክኽ፡ከእግዚአብሔር፡ምልክትን፡ለምን።

12አካዝም፦አልለምንም፥እግዚአብሔርንም፡አልፈ፟ታተንም፡አለ።

13ርሱም፡አለ፦እናንተ፡የዳዊት፡ቤት፡ሆይ፥ስሙ፤በእውኑ፡ሰውን፡ማድከማችኹ፡ቀላል፡ ነውን፧አምላኬን፡ደግሞ፡የምታደክሙ፤

14ስለዚህ፥ጌታ፡ራሱ፡ምልክት፡ይሰጣችዃል፤እንሆ፥ድንግል፡ትፀንሳለች፥ወንድ፡ልጅም፡ ትወልዳለች፥ስሙንም፡ዐማኑኤል፡ብላ፡ትጠራዋለች።

15ክፉን፡ለመጥላት፡መልካሙንም፡ለመምረጥ፡ሲያውቅ፡ቅቤና፡ማር፡ይበላል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

16ሕፃኑ፡ክፉን፡ለመጥላት፡መልካሙን፡ለመምረጥ፡ሳያውቅ፡የፈራኻቸው፡የኹለቱ፡ነገሥታት፡አገር፡ ባድማ፡ትኾናለች።

17እግዚአብሔርም፡ኤፍሬም፡ከይሁዳ፡ከተለየበት፡ቀን፡ዠምሮ፡ያልመጣውን፡ዘመን፡በአንተና፡በሕዝብኽ፡ በአባትኽም፡ቤት፡ላይ፡ያመጣል፤ርሱም፡የአሶር፡ንጉሥ፡መምጣት፡ነው።

18በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡በግብጽ፡ወንዝ፡ዳርቻ፡ያለውን፡ዝምብ፡በአሶርም፡አገር፡ ያለውን፡ንብ፡በፉጨት፡ይጠራል።

19ይመጡማል፥እነርሱም፡ዅሉ፡በበረሓ፡ሸለቆ፡በድንጋይም፡ዋሻ፡ውስጥ፡በሾኽ፡ቍጥቋጦ፡ዅሉ፡ላይ፡ በማሰማሪያውም፡ዅሉ፡ላይ፡ይሰፍራሉ።

20በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ከወንዙ፡ማዶ፡በተከራየው፡ምላጭ፡በአሶር፡ንጉሥ፡የራሱንና፡የእግሩን፡ ጠጕር፡ይላጨዋል፤ምላጩም፡ጢሙን፡ደግሞ፡ይበላል።

21በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ሰው፡አንዲት፡ጊደርን፡ኹለት፡በጎችንም፡ያሳድጋል፤

22ከሚሰጡት፡ወተት፡ብዛት፡የተነሣ፡ቅቤ፡ይበላል፤በአገሪቱም፡መካከል፡የቀረ፡ዅሉ፡ቅቤና፡ማር፡ ይበላል።

23በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ሺሕ፡ብር፡የተገመተ፡ሺሕ፡የወይን፡ግንድ፡በነበረበት፡ስፍራ፡ዅሉ፡ ለኵርንችትና፡ለሾኽ፡ይኾናል።

24ኵርንችትና፡ሾኽ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ነውና፥በፍላጻና፡በቀስት፡ወደዚያ፡ይገባሉ።

25በመቈፈሪያም፡ወደተቈፈሩ፡ኰረብታዎች፡ዅሉ፡ከኵርንችትና፡ሾኽ፡ፍርሀት፡የተነሣ፡ወደዚያ፡ አትኼድም፤ነገር፡ግን፥የበሬ፡ማሰማሪያና፡የበግ፡መራገጫ፡ይኾናል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source