Skip to content
← Isaiah

Chapter 6 · Amharic

Isaiah

1ንጉሡ፡ዖዝያን፡በሞተበት፡ዓመት፡እግዚአብሔርን፡በረዥምና፡ከፍ፡ባለ፡ዙፋን፡ላይ፡ተቀምጦ፡ አየኹት፥የልብሱም፡ዘርፍ፡መቅደሱን፡ሞልቶት፡ነበር።

2ሱራፌልም፡ከርሱ፡በላይ፡ቆመው፡ነበር፥ለያንዳንዱም፡ስድስት፡ክንፍ፡ነበረው፤በኹለት፡ክንፍ፡ፊቱን፡ ይሸፍን፡ነበር፥በኹለቱም፡ክንፍ፡እግሮቹን፡ይሸፍን፡ነበር፥በኹለቱም፡ክንፍ፡ይበር፡ነበር።

3አንዱም፡ለአንዱ፦ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ምድር፡ዅሉ፡ከክብሩ፡ ተሞልታለች፡እያለ፡ይጮኽ፡ነበር።

4የመድረኩም፡መሠረት፡ከጯኺው፡ድምፅ፡የተነሣ፡ተናወጠ፥ቤቱንም፡ጢስ፡ሞላበት።

5እኔም፦ከንፈሮቼ፡የረከሱብኝ፡ሰው፡በመኾኔ፥ከንፈሮቻቸውም፡በረከሱባቸው፡ሕዝብ፡መካከል፡ በመቀመጤ፡ዐይኖቼ፡የሰራዊትን፡ጌታ፡ንጉሡን፡እግዚአብሔርን፡ስለ፡አዩ፡ጠፍቻለኹና፡ወዮልኝ! አልኹ።

6ከሱራፌልም፡አንዱ፡እየበረረ፡ወደ፡እኔ፡መጣ፥በእጁም፡ከመሠዊያው፡በጕጠት፡የወሰደው፡ፍም፡ነበረ።

7አፌንም፡ዳሰሰበትና፦እንሆ፥ይህ፡ከንፈሮችኽን፡ነክቷል፤በደልኽም፡ከአንተ፡ተወገደ፥ኀጢአትኽም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ተሰረየልኽ፡አለኝ።

8የጌታንም፡ድምፅ፦ማንን፡እልካለኹ፧ማንስ፡ይኼድልናል፧ሲል፡ሰማኹ።እኔም፦እንሆኝ፥እኔን፡ላከኝ፡ አልኹ።

9ርሱም፦ኺድ፥ይህን፡ሕዝብ፦መስማትን፡ትሰማላችኹ፡አታስተውሉምም፤ማየትንም፡ታያላችኹ፡ አትመለከቱምም፡በላቸው።

10በዐይናቸው፡እንዳያዩ፥በዦሯቸውም፡እንዳይሰሙ፥በልባቸውም፡እንዳያስተውሉ፥ተመልሰውም፡ እንዳይፈወሱ፥የዚህን፡ሕዝብ፡ልብ፡አደንድን፥ዦሯቸውንም፡አደንቍር፥ዐይናቸውንም፡ጨፍን፡አለኝ።

11እኔም፦ጌታ፡ሆይ፥እስከ፡መቼ፡ድረስ፡ነው፧አልኹ።ርሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ከተማዎች፡ የሚኖርባቸውን፡ዐጥተው፡እስኪፈርሱ፡ድረስ፥ቤቶችም፡ሰው፡አልቦ፡እስኪኾኑ፡ምድርም፡ፈጽሞ፡ባድማ፡ኾና፡ እስክትቀር፡ድረስ፥

12እግዚአብሔርም፡ሰዎችን፡እስኪያርቅ፥በምድርም፡መካከል፡ውድማው፡መሬት፡እስኪበዛ፡ድረስ፡ነው።

13በርሷም፡ዘንድ፡ዐሥረኛ፡እጅ፡ቀርቶ፡እንደ፡ኾነ፡ርሱ፡ደግሞ፡ይቃጠላል፤በተቈረጡ፡ጊዜ፡ጕቶቻቸው፡ እንደ፡ቀሩ፡እንደ፡ግራርና፡እንደ፡ኮምበል፡ዛፍ፡ኾኖ፥ጕቶው፡የተቀደሰ፡ዘር፡ይኾናል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source