Skip to content
← Isaiah

Chapter 5 · Amharic

Isaiah

1አኹን፡ስለ፡ወዳጄና፡ስለወይን፡ቦታው፡ለወዳጄ፡ቅኔ፡እቀኛለኹ።ለወዳጄ፡በፍሬያማው፡ኰረብታ፡ላይ፡ የወይን፡ቦታ፡ነበረው።

2በዙሪያው፡ቈፈረ፥ድንጋዮችንም፡ለቅሞ፡አወጣ፥ምርጥ፡የኾነውንም፡ዐረግ፡ተከለበት፥በመካከሉም፡ ግንብ፡ሠራ፥ደግሞም፡የመጥመቂያ፡ጕድጓድ፡ማሰበት፤ወይንንም፡ያፈራ፡ዘንድ፡ተማመነ፥ዳሩ፡ግን፡ ሖምጣጣ፡ፍሬ፡አፈራ።

3አኹንም፡እናንተ፡በኢየሩሳሌም፡የምትኖሩ፡የይሁዳ፡ሰዎች፡ሆይ፥በእኔና፡በወይኑ፡ቦታዬ፡መካከል፡እስኪ፡ ፍረዱ።

4ለወይኔ፡ያላደረግኹለት፥ከዚህ፡ሌላ፡አደርግለት፡ዘንድ፡የሚገ፟ባ፟ኝ፡ምንድር፡ነው፧ወይንን፡ያፈራል፡ብዬ፡ ስተማመን፡ስለ፡ምን፡ሖምጣጣ፡ፍሬ፡አፈራ፧

5አኹንም፡በወይኔ፡ላይ፡የማደርገውን፡እነግራችዃለኹ፤ዐጥሩን፡እነቅላለኹ፥ለማሰማሪያም፡ ይኾናል፤ቅጥሩንም፡አፈርሳለኹ፥ለመራገጫም፡ይኾናል።

6ባድማ፡አደርገዋለኹ፤አይቈረጥም፥አይኰተኰትም፤ኵርንችትና፡ሾኽ፡ይበቅልበታል፤ዝናብንም፡ እንዳያዘንቡበት፡ዳመናዎችን፡አዛ፟ለኹ።

7የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ወይን፡ቦታ፡ርሱ፡የእስራኤል፡ቤት፡ነው፥የደስታውም፡አትክልት፡የይሁዳ፡ ሰዎች፡ናቸው፤ፍርድን፡ተስፋ፡ያደርግ፡ነበር፥እንሆም፡ደም፡ማፍሰስ፡ኾነ፤ጽድቅንም፡ይተማመን፡ ነበር፥እንሆም፥ጩኸት፡ኾነ።

8ስፍራ፡እስከማይቀር፡ድረስ፡እናንተም፡በምድር፡ላይ፡ብቻችኹን፡እስክትቀመጡ፡ድረስ፥ቤትን፡ከቤት፡ ጋራ፡ለሚያያይዙ፡ዕርሻንም፡ከዕርሻ፡ጋራ፡ለሚያቀራርቡ፡ወዮላቸው!

9የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በዦሮዬ፡እንዲህ፡አለ፦በእውነት፡ብዙ፡ታላቅና፡መልካም፡ቤት፡ባድማ፡ ይኾናል፥የሚቀመጥበትም፡አይገኝም።

10ከወይኑ፡ቦታ፡ዐሥር፡ጥማድ፡በሬ፡ካረሰው፡አንድ፡የባዶስ፡መስፈሪያ፡ብቻ፡ይወጣል፤አንድ፡የቆሮስ፡ መስፈሪያ፡ዘር፡አንድ፡የኢፍ፡መስፈሪያ፡ብቻ፡ይሰጣል።

11ስካርን፡ለመከተል፡በጧት፡ለሚማልዱ፥የወይን፡ጠጅም፡እስኪያቃጥላቸው፡እስከ፡ሌሊት፡ድረስ፡ ለሚዘገዩ፡ወዮላቸው!

12መሰንቆና፡በገና፡ከበሮና፡እንቢልታም፡የወይን፡ጠጅም፡በግብዣቸው፡አለ፤የእግዚአብሔርን፡ሥራ፡ግን፡ አልተመለከቱም፥እጁም፡ያደረገችውን፡አላስተዋሉም።

13ስለዚህ፥ሕዝቤ፡ወደ፡ምርኮ፡ኼዱ፥ጌታን፡አላወቁትምና፤ከበርቴዎቻቸውም፡ተራቡ፥ሕዝባቸውም፡ ተጠሙ።

14ሲኦልም፡ሆዷን፡አስፍታለች፥አፏንም፡ያለልክ፡ከፍታለች፤ከበርቴዎቻቸውና፡ዐዛውንቶቻቸው፡ ባለጠጋዎቻቸውም፡ደስተኛዎቻቸውም፡ወደ፡ርሷ፡ይወርዳሉ።

15ሰውም፡ይጐሰቍላል፥ሰውም፡ይዋረዳል፥የትዕቢተኛዎችም፡ዐይን፡ትዋረዳለች፤

16የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ግን፡በፍርድ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏል፥ቅዱሱም፡አምላክ፡በጽድቅ፡ተቀድሷል።

17የበግ፡ጠቦቶች፡በማሰማሪያቸው፡ውስጥ፡ይሰማራሉ፥እንግዳዎችም፡የሰቡትን፡ባድማ፡ይበላሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

18በደልን፡በምናምንቴ፡ገመድ፥ኀጢአትንም፡በሠረገላ፡ማሰሪያ፡ወደ፡ራሳቸው፡ለሚስቡ፦እናይ፡ዘንድ፡ ይቸኵል፥

19ሥራውንም፡ያፋጥን፤እናውቃትም፡ዘንድ፡የእስራኤል፡ቅዱስ፡ምክር፡ትቅረብ፥ትምጣ፡ለሚሉ፡ወዮላቸው!

20ክፉውን፡መልካም፡መልካሙን፡ክፉ፡ለሚሉ፥ጨለማውን፡ብርሃን፡ብርሃኑንም፡ጨለማ፡ ለሚያደርጉ፥ጣፋጩን፡መራራ፡መራራውንም፡ጣፋጭ፡ለሚያደርጉ፡ወዮላቸው!

21በዐይናቸው፡ጥበበኛዎች፡በነፍሳቸውም፡አስተዋዮች፡ለኾኑ፡ወዮላቸው!

22የወይን፡ጠጅ፡ለመጠጣት፡ኀያላን፡የሚያሰክረውንም፡ለማደባለቅ፡ጨካኞች፡ለኾኑ፤

23በደለኛውን፡ስለ፡ጕቦ፡ጻድቅ፡ለሚያደርጉ፥የጻድቁንም፡ጽድቅ፡ለሚያስወግዱበት፡ወዮላቸው!

24ስለዚህ፥የእሳት፡ወላፈን፡ቃርሚያን፡እንደሚበላ፥እብቅም፡በነበልባል፡ውስጥ፡እንደሚጠፋ፥እንዲሁ፡ የእነርሱ፡ሥር፡የበሰበሰ፡ይኾናል፥ቡቃያቸውም፡እንደ፡ትቢያ፡ይበና፟ል፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ ጥለዋልና፥የእስራኤልም፡ቅዱስ፡የተናገረውን፡ቃል፡አቃለ፟ዋልና።

25ስለዚህ፥የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በሕዝቡ፡ላይ፡ነዷ፟ል፥እጁንም፡በላያቸው፡ዘርግቶ፡ መትቷቸዋል፤ተራራዎችም፡ተንቀጠቀጡ፥ሬሳቸውም፡በአደባባይ፡መካከል፡እንደ፡ጕድፍ፡ኾኗል።በዚህም፡ ዅሉ፡እንኳ፡ቍጣው፡አልተመለሰችም፥ነገር፡ግን፥እጁ፡ገና፡ተዘርግታ፡ትኖራለች።

26ለአሕዛብም፡በሩቅ፡ምልክትን፡ያቆማል፥ከምድርም፡ዳርቻ፡በፉጨት፡ይጠራቸዋል፤እንሆም፥እየተጣደፉ፡ ፈጥነው፡ይመጣሉ።

27ደካማና፡ስንኵል፡የለባቸውም፥የሚያንቀላፋና፡የሚተኛም፡የለም፤የወገባቸውም፡መቀነት፡ አይፈታም፥የጫማቸውም፡ማዘቢያ፡አይበጠስም።

28ፍላጻዎቻቸው፡ተስለዋል፥ቀስቶቻቸውም፡ዅሉ፡ተለጥጠዋል፤የፈረሶቻቸውም፡ኰቴ፡እንደ፡ቡላድ፡ የሠረገላዎቻቸውም፡መንኰራኵር፡እንደ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡ይቈጠራል።

29ጩኸታቸው፡እንደ፡አንበሳ፡ነው፥እንደ፡አንበሳ፡ደቦሎችም፡ያገሣሉ፤ንጥቂያንም፡ይዘው፡ ያገሣሉ፥ይወስዱትማል፥የሚያድንም፡የለም።

30በዚያም፡ቀን፡እንደ፡ባሕር፡መትመም፡ይተምሙባቸዋል፤ወደ፡ምድርም፡ቢመለከቱ፥እንሆ፥ጨለማና፡ መከራ፡አለ፤ብርሃንም፡በደመናዎቿ፡ውስጥ፡ጨልሟል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source