1በዚያም፡ቀን፡ሰባት፡ሴቶች።የገዛ፡እንጀራችንን፡እንበላለን፡የገዛ፡ልብሳችንንም፡እንለብሳለን፤ስምኽ፡ብቻ፡ በእኛ፡ላይ፡ይጠራ፥መሰደባችንንም፡አርቅ፡ብለው፡አንዱን፡ወንድ፡ይይዙታል።
2በዚያም፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ቍጥቋጥ፡ለጌጥና፡ለክብር፡ይኾናል፥ከእስራኤልም፡ወገን፡ላመለጡ፡ሰዎች፡ የምድሪቱን፡ፍሬ፡ለትምክሕትና፡ለውበት፡ይኾናል።
4ጌታም፡የጽዮንን፡ቈነዣዥት፡እድፍ፡ባጠበ፡ጊዜ፥የኢየሩሳሌምንም፡ደም፡በፍርድ፡መንፈስና፡ በሚያቃጥል፡መንፈስ፡ከመካከሏ፡ባነጻ፡ጊዜ፥በጽዮን፡የቀረ፡በኢየሩሳሌምም፡የተረፈ፥በኢየሩሳሌም፡ለሕይወት፡ የተጻፈ፡ዅሉ፥ቅዱስ፡ይባላል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
5እግዚአብሔርም፡በጽዮን፡ተራራ፡ላይ፡ባለ፡ማደሪያ፡ዅሉ፡በጉባኤያቸውም፡ላይ፡በቀን፡ዳመናንና፡ጢስን፡ በሌሊትም፡የሚቃጠለውን፡የእሳት፡ብርሃን፡ይፈጥራል፤በክብርም፡ዅሉ፡ላይ፡መጋረጃ፡ይኾናል።
6በቀን፡ከሙቀት፡ለጥላ፥ከዐውሎ፡ነፋስና፡ከዝናብም፡ለመጠጊያና፡ለመሸሸጊያ፡ጐዦ፡ይኾናል።