Skip to content
← Isaiah

Chapter 12 · Amharic

Isaiah

1በዚያም፡ቀን፦አቤቱ፥ተቈጥተኸኛልና፥ቍጣኽንም፡ከእኔ፡መልሰኻልና፥አጽናንተኸኛልምና፡ አመሰግንኻለኹ።

2እንሆ፥አምላክ፡መድኀኒቴ፡ነው፤ጌታ፡እግዚአብሔር፡ኀይሌና፡ዝማሬዬ፡ነውና፥መድኀኒቴም፡ ኾኗልና፥በርሱ፡ታምኜ፡አልፈራም፡ትላለኽ።

3ውሃውንም፡ከመድኀኒት፡ምንጮች፡በደስታ፡ትቀዳላችኹ።

4በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ትላላችኹ።እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፥ስሙንም፡ጥሩ፤በአሕዛብ፡መካከል፡ ሥራውን፡አስታውቁ፤ስሙ፡ከፍ፡ያለ፡እንደ፡ኾነ፡ተናገሩ።

5ታላቅ፡ሥራ፡ሠርቷልና፥ለእግዚአብሔር፡ተቀኙ፤ይህንም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡አስታውቁ።

6አንቺ፡በጽዮን፡የምትኖሪ፡ሆይ፥የእስራኤል፡ቅዱስ፡በመካከልሽ፡ከፍ፡ከፍ፡ብሏልና፥ደስ፡ይበልሽ፡ እልልም፡በዪ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source