Skip to content
← Isaiah

Chapter 13 · Amharic

Isaiah

1የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ያየው፡ስለ፡ባቢሎን፡የተነገረ፡ሸክም።

2ምድረ፡በዳ፡በኾነ፡ተራራ፡ላይ፡ምልክትን፡አቁሙ፥ድምፅንም፡ከፍ፡አድርጉባቸው፤በአለቃዎችም፡ደጆች፡ እንዲገቡ፡በእጅ፡ጥቀሱ።

3ቍጣዬን፡ይፈጽሙ፡ዘንድ፡ቅዱሳኔን፡አዝዣለኹ፥እኔ፡ኀያላኔንና፡በታላቅነቴ፡ደስ፡የሚላቸውን፡ ጠርቻለኹ።

4በተራራዎች፡ላይ፡እንደ፡ታላቅ፡ሕዝብ፡ድምፅ፡የኾነ፡የብዙ፡ሰው፡ድምፅ፡አለ።የከተማቹት፡የአሕዛብ፡ መንግሥታት፡የውካታ፡ጫጫታ፡አለ።የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ሰራዊትን፡ለሰልፍ፡አሰልፏል።

5እግዚአብሔርና፡የቍጣው፡የጦር፡ዕቃ፡ምድርን፡ዅሉ፡ያጠፏት፡ዘንድ፡ከሩቅ፡አገር፡ከሰማይ፡ዳርቻ፡ ይመጣሉ።

6የእግዚአብሔር፡ቀን፡ቀርቧልና፥አልቅሱ፤ዅሉን፡ከሚችል፡አምላክ፡ዘንድ፡እንደሚመጣ፡ጥፋት፡ ይመጣል።

7ስለዚህ፥እጅ፡ዅሉ፡ትዝላለች፥የሰውም፡ዅሉ፡ልብ፡ይቀልጣል።

8ይደነግጣሉ፤ምጥና፡ሕማም፡ይይዛቸዋል፥እንደምትወልድ፡ሴትም፡ያምጣሉ፤አንዱም፡በሌላው፡ ይደነቃል፥ፊታቸውም፡የነበልባል፡ፊት፡ነው።

9እንሆ፥ምድሪቱን፡ባድማ፡ሊያደርግ፥ኀጢአተኛዎቿንም፡ከርሷ፡ዘንድ፡ሊያጠፋ፡ጨካኝ፡ኾኖ፡በመዓትና፡ በጽኑ፡ቍጣ፡ተሞልቶ፡የእግዚአብሔር፡ቀን፡ይመጣል።

10የሰማይም፡ከዋክብትና፡ሰራዊቱ፡ብርሃናቸውን፡አይሰጡም፥ፀሓይም፡በወጣች፡ጊዜ፡ ትጨልማለች፥ጨረቃም፡በብርሃኑ፡አያበራም።

11ዓለሙን፡ስለ፡ክፋታቸው፡ክፉዎቹንም፡ስለ፡በደላቸው፡እቀጣለኹ፤የትዕቢተኛዎችንም፡ኵራት፡አዋርዳለኹ።

12የቀሩትም፡ከጥሩ፡ወርቅ፡ይልቅ፡የከበሩ፡ይኾናሉ፥ሰውም፡ከኦፊር፡ወርቅ፡ይልቅ፡የከበረ፡ይኾናል።

13ስለዚህ፥በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡መዓት፡በጽኑ፡ቍጣ፡ቀንም፡ሰማያትን፡አነቃንቃለኹ፥ምድርም፡ ከስፍራዋ፡ትናወጣለች። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

14እንደ፡ተባረረም፡ሚዳቋ፥ማንም፡እንደማይሰበስበው፡እንደ፡በግ፡መንጋ፥ሰው፡ዅሉ፡ወደ፡ወገኑ፡ ይመለሳል፥ዅሉም፡ወደ፡አገሩ፡ይሸሻል።

15የተገኘ፡ዅሉ፡የተወጋ፡ይኾናል፥የተያዘም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ይወድቃል።

16ሕፃናታቸውም፡በፊታቸው፡ይጨፈጨፋሉ፥ቤቶቻቸውም፡ይበዘበዛሉ፥ሚስቶቻቸውም፡ይነወራሉ።

17እንሆ፥ብር፡የማይሹትን፥ወርቅም፡የማያምራቸውን፡ሜዶናውያንን፡በላያቸው፡አስነሣለኹ።

18ፍላጻዎቻቸውም፡ጐበዞችን፡ይጨፈጭፋሉ፥የማሕፀንንም፡ፍሬ፡አይምሩም፥ዐይኖቻቸውም፡ለሕፃናት፡ አይራሩም።

19እግዚአብሔርም፡ሰዶምንና፡ገሞራን፡ባፈረሰ፡ጊዜ፡እንደ፡ነበረው፥የመንግሥታት፡ክብር፡የከለዳውያንም፡ ትዕቢት፡ጌጥ፡ባቢሎን፡እንዲሁ፡ትኾናለች።

20ለዘለዓለም፡የሚቀመጥባት፡አይገኝም፥ከትውልድ፡እስከ፡ትውልድ፡ድረስ፡ሰው፡ አይኖርባትም፤ዐረባውያንም፡ድንኳንን፡በዚያ፡አይተክሉም፥እረኛዎችም፡መንጋዎቻቸውን፡በዚያ፡አያሳርፉም።

21በዚያም፡የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ያርፋሉ፥ጕጕቶችም፡በቤቶቻቸው፡ይሞላሉ፤ሰጐኖችም፡በዚያ፡ ይኖራሉ፥በዚያም፡አጋንንት፡ይዘፍናሉ።

22ተኵላዎችም፡በግንቦቻቸው፥ቀበሮዎችም፡በሚያማምሩ፡አዳራሾቻቸው፡ይጮኻሉ፤ጊዜዋም፡ለመምጣት፡ ቀርቧል፥ቀኗም፡አይዘገይም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source