1እግዚአብሔርም፡ያዕቆብን፡ይምረዋል፥እስራኤልንም፡ደግሞ፡ይመርጠዋል፥በአገራቸውም፡ ያኖራቸዋል፤መጻተኛም፡ከርሱ፡ጋራ፡ይተባበራል፥ከያዕቆብም፡ቤት፡ጋራ፡ይጣበቃል።
2አሕዛብም፡ይዘው፡ወደ፡ስፍራቸው፡ያመጧቸዋል፥የእስራኤልም፡ቤት፡በእግዚአብሔር፡ምድር፡እንደ፡ ሎሌዎችና፡እንደ፡ገረዶች፡አድርገው፡ይገዟቸዋል፤የማረኳቸውን፡ይማርካሉ፥አስጨናቂዎችንም፡ይገዛሉ።
3በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡ከሐዘንኽና፡ከመከራኽ፡ከተገዛኽለትም፡ከጽኑ፡ባርነት፡ ያሳርፍኻል።
4ይህንም፡ምሳሌ፡በባቢሎን፡ንጉሥ፡ላይ፡ታነሣለኽ፡እንዲህም፡ትላለኽ፦አስጨናቂ፡እንዴት፡ዐረፈ! አስገባሪም፡እንዴት፡ጸጥ፡አለ!
6አሕዛብንም፡በመዓትና፡በማያቋርጥ፡መምታት፡የመታውን፥አሕዛብንም፡ባልተከለከለ፡መከራ፡ በቍጣው፡የገዛውን፡የኃጥኣንን፡በትር፡የአለቃዎችንም፡ዘንግ፡እግዚአብሔር፡ሰብሯል።
7ምድርም፡ዅሉ፡ዐርፋ፡በጸጥታ፡ተቀምጣለች፡እልልም፡ብላለች።
8ጥድና፡የሊባኖስ፡ዝግባ፦አንተ፡ከተዋረድኽ፡ዠምሮ፡ማንም፡ይቈርጠን፡ዘንድ፡አልወጣብንም፡ብለው፡ ባንተ፡ደስ፡አላቸው።
9ሲኦል፡በመምጣትኽ፡ልትገናኝኽ፡በታች፡ታወከች፤የሞቱትንም፥የምድርን፡ታላላቆች፡ዅሉ፥ለአንተ፡ አንቀሳቀሰች፥የአሕዛብንም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡ከዙፋኖቻቸው፡አስነሣች።
10እነዚህ፡ዅሉ፦አንተ፡ደግሞ፡እንደ፡እኛ፡ደክመኻልን፧እኛንስ፡መስለኻልን፧ጌጥኽና፡የበገናኽ፡ድምፅ፡ ወደ፡ሲኦል፡ወረደ፤
11በበታችኽም፡ብል፡ተነጥፏል፥ትልም፡መደረቢያኽ፡ኾኗል፡ብለው፡ይመልሱልኻል።
12አንተ፡የንጋት፡ልጅ፡አጥቢያ፡ኮከብ፡ሆይ፥እንዴት፡ከሰማይ፡ወደቅኽ! አሕዛብንም፡ያዋረድኽ፡አንተ፡ ሆይ፥እንዴት፡እስከ፡ምድር፡ድረስ፡ተቈረጥኽ! http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
13አንተን፡በልብኽ፦ወደ፡ሰማይ፡ዐርጋለኹ፥ዙፋኔንም፡ከእግዚአብሔር፡ከዋክብት፡በላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ አደርጋለኹ፥በሰሜንም፡ዳርቻ፡በመሰብሰቢያ፡ተራራ፡ላይ፡እቀመጣለኹ፤
14ከዳመናዎች፡ከፍታ፡በላይ፡ዐርጋለኹ፥በልዑልም፡እመሰላለኹ፡አልኽ።
15ነገር፡ግን፥ወደ፡ሲኦል፡ወደጕድጓዱም፡ጥልቅ፡ትወርዳለኽ።
16የሚያዩኽ፡ይመለከቱኻልና፦በእውኑ፡ምድርን፡ያንቀጠቀጠ፥መንግሥታትንም፡ያናወጠ፥
17ዓለሙን፡ዅሉ፡ባድማ፡ያደረገ፥ከተማዎችንም፡ያፈረሰ፥ምርኮኛዎቹንም፡ወደ፡ቤታቸው፡ያልሰደደ፡ሰው፡ ይህ፡ነውን፧ብለው፡ያስተውሉኻል።
18የአሕዛብ፡ነገሥታት፡ዅሉ፡በየቤታቸው፡በክብር፡አንቀላፍተዋል።
19አንተ፡ግን፡እንደ፡ተጠላ፡ቅርንጫፍ፡ከመቃብርኽ፡ተጥለኻል፤በሰይፍም፡የተወጉት፥ተገድለውም፡ ወደጕድጓዱ፡ድንጋዮች፡የወረዱት፡ከድነውኻል፤እንደ፡ተረገጠም፡ሬሳ፡ኾነኻል።
20ምድርኽን፡አጥፍተኻልና፥ሕዝብኽንም፡ገድለኻልና፥ከነርሱ፡ጋራ፡በመቃብር፡በአንድነት፡ አትኾንም፤የክፉዎች፡ዘር፡ለዘለዓለም፡የተጠራ፡አይኾንም።
21እንዳይነሡም፥ምድርንም፡እንዳይወርሱ፥የዓለሙንም፡ፊት፡በከተማዎች፡እንዳይሞሉ፡ስላባቶቻቸው፡በደል፡ ለልጆቹ፡ሞትን፡አዘጋጁላቸው።
22በእነርሱ፡ላይ፡እነሣለኹ፡ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ከባቢሎን፡ስምንና፡ቅሬታን፥ዘርንና፡ ትውልድንም፡እቈርጣለኹ፡ይላል፡እግዚአብሔር።
23የዣርት፡መኖሪያ፡የውሃም፡መቋሚያ፡አደርጋታለኹ፤በጥፋትም፡መጥረጊያ፡እጠርጋታለኹ፡ይላል፡ የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
24የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ምሏል።እንደ፡ተናገርኹ፡በርግጥ፡ይኾናል፥እንደ፡ ዐሰብኹም፡እንዲሁ፡ይቆማል።
25አሶርን፡በምድሬ፡ላይ፡እሰብረዋለኹ፥በተራራዬም፡ላይ፡እረግጠዋለኹ፤ቀንበሩም፡ከነርሱ፡ላይ፡ ይነሣል፥ሸክሙም፡ከጫንቃቸው፡ላይ፡ይወገዳል።
26በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡እግዚአብሔር፡ያሰበው፡ዐሳብ፡ይህ፡ነው፥በአሕዛብም፡ዅሉ፡ላይ፡የተዘረጋች፡እጅ፡ ይህች፡ናት።
27የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ዐስቧል፤የሚያስጥለውስ፡ማን፡ነው፧እጁም፡ ተዘርግታለች፤የሚመልሳትስ፡ማን፡ነው፧
28ንጉሡ፡አካዝ፡በሞተበት፡ዓመት፡ይህ፡ሸክም፡ኾነ።
29ፍልስጥኤም፡ሆይ፥ከእባቡ፡ሥር፡እፍኝት፡ይወጣልና፥ፍሬውም፡የሚበር፟ና፡እሳት፡የሚመስል፡እባብ፡ ይኾናልና፥የመታሽ፡በትር፡ስለ፡ተሰበረ፡ዅላችኹም፡ደስ፡አይበላችኹ።
30የድኻዎችም፡የበኵር፡ልጆች፡ይሰማራሉ፥ችግረኛዎችም፡ተዘልለው፡ይተኛሉ፤ሥርኽንም፡በራብ፡ እገድላለኹ፥ቅሬታኽም፡ይገደላል።
31አንተ፡በር፡ሆይ፥ወዮ፡በል፡አንቺም፡ከተማ፡ሆይ፥ጩኺ፤ፍልስጥኤም፡ሆይ፥ዅላችኹም፡ ቀልጣችዃል፤ጢስ፡ከሰሜን፡ይመጣል፡ከጭፍራውም፡ተለይቶ፡የሚቀር፡የለም።
32ለሕዝቡም፡መልእክተኛዎች፡ምን፡ብሎ፡መመለስ፡ይገ፟ባ፟ል፧እግዚአብሔር፡ጽዮንን፡እንደ፡ መሠረተ፥የሕዝቡም፡ችግረኛዎች፡በርሷ፡ውስጥ፡እንደሚጠጉ፡ነው።