1ስለ፡ሞዐብ፡የተነገረ፡ሸክም።የሞዐብ፡ዔር፡በሌሊት፡ፈርሶ፡ጠፋ፤ቂር፡የሚባልም፡የሞዐብ፡ምሽግ፡ በሌሊት፡ፈርሶ፡ጠፋ።
2ወደ፡ባይት፡ወደ፡ዲቦንም፡ወደኰረብታ፡መስገጃዎችም፡ለልቅሶ፡ወጥተዋል፤ሞዐብ፡በናባው፡በሜድባ፡ ላይ፡ታለቅሳለች፤ራሳቸው፡ዅሉ፡ተነጭቷል፥ጢማቸውም፡ዅሉ፡ተላጭቷል።
3በየመንገዳቸውም፡በማቅ፡ታጥቀዋል፤በየሰገነቶቻቸውና፡በያደባባዮቻቸው፡እንባ፡እጅግ፡እያፈሰሱ፡ዅሉም፡ አልቅሰዋል።
4ሐሴቦንና፡ኤልያሊ፡ጮኹ፤ድምፃቸው፡እስከ፡ያሀጽ፡ድረስ፡ይሰማል፤ስለዚህ፥የሞዐብ፡ሰልፈኛዎች፡ ጮኹ፤ነፍሷ፡በውስጧ፡ተንቀጠቀጠች።
5ልቤ፡ስለ፡ሞዐብ፡ጮኸ፤ከርሷም፡የሚሸሹ፡ወደ፡ዞዓር፡ወደ፡ዔግላት ፡ሺሊሺያ ፡ኰበለሉ፤በሉሒት፡ ዐቀበት፡ላይ፡እያለቀሱ፡ይወጣሉ፥በሖሮናይምም፡መንገድ፡የዋይታ፡ጩኸት፡ያነሣሉ።
6የኔምሬም፡ውሃዎች፡ይደርቃሉ፤ሣሩም፡ደርቋል፥ለጋውም፡ጠውልጓል፥ልምላሜውም፡ዅሉ፡የለም።
7ስለዚህ፥የሰበሰቡትን፡ሀብትና፡መዝገባቸውን፡ወደአሓያ፡ዛፍ፡ወንዝ፡ማዶ፡ይወስዱታል።
8ጩኸት፡የሞዐብን፡ዳርቻ፡ዅሉ፡ዞረ፤ልቅሶዋም፡ወደ፡ኤግላይምና፡ወደ፡ብኤርኢሊም፡ደረሰ።
9የዲሞንም፡ውሃ፡ደም፡ተሞልታለች፤በዲሞንም፡ላይ፡ሥቃይን፡እጨምራለኹ፥ከሞዐባውያንም፡ በሚያመልጡ፥ከምድርም፡በሚቀሩ፡ላይ፡አንበሳን፡አመጣለኹ።