1በምድርም፡ላይ፡ለሠለጠነው፡አለቃ፡የበግ፡ጠቦቶችን፡በምድረ፡በዳ፡ካለችው፡ከሴላ፡ወደጽዮን፡ሴት፡ ልጅ፡ተራራ፡ስደዱ።
2እንደሚበር፟፡ወፍ፡እንደ፡ተበተኑም፡ጫጩቶች፡እንዲሁ፡የሞዐብ፡ሴቶች፡ልጆች፡በአርኖን፡መሻገሪያዎች፡ ይኾናሉ።
3ምክርን፡ምከሪ፥ፍርድን፡አድርጊ፥በቀትር፡ጊዜ፡ጥላሽን፡እንደ፡ሌሊት፡አድርጊ፤የተሰደዱትን፡ ሸሽጊ፥የሸሹትን፡አትግለጪ።
4ከሞዐብ፡የተሰደዱት፡ከአንቺ፡ጋራ፡ይቀመጡ፤ከሚያጠፋቸው፡ፊት፡መጋረጃ፡ኹኛቸው።የሚያስጨንቁ፡ አልቀዋል፥ጥፋትም፡ቀርቷል፤ይጨቍኑ፡የነበሩ፡ከምድር፡ጠፍተዋል።
5ዙፋንም፡በምሕረት፡ይቀናል፥በዚያም፡ላይ፡በዳዊት፡ድንኳን፡ፍርድን፡የሚሻ፡ጽድቅንም፡የሚያፈጥን፡ ፈራጅ፡በእውነት፡ይቀመጣል፡
6ስለሞዐብ፡ትዕቢት፡እጅግ፡ስለ፡መታበዩ፥ስለ፡ኵራቱና፡ስለ፡ትዕቢቱ፡ስለ፡ቍጣውም፡ ሰምተናል፤ትምክሕቱ፡ከንቱ፡ነው።
7ስለዚህ፥ሞዐብ፡ስለ፡ሞዐብ፡ዋይ፡ይላል፤ዅሉም፡ዋይ፡ይላል፤ስለቂርሐራሴት፡መሠራት፡በጥልቅ፡ሐዘን፡ ታለቅሳላችኹ።
8የሐሴቦን፡ዕርሻዎችና፡የሴባማ፡ወይን፡ግንዶች፡አዝነዋል።የአሕዛብ፡አለቃዎች፡የሰባበሯቸው፡ቅርንጫፎች፡ እስከ፡ኢያዜር፡ደርሰው፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡ወጥተው፡ነበር፤ቍጥቋጦቹም፡ተዘርግተው፡ባሕርን፡ተሻግረው፡ ነበር።
9ስለዚህ፥በኢያዜር፡ልቅሶ፡ስለሴባማ፡ወይን፡ግንድ፡አለቅሳለኹ፤ሐሴቦንና፡ኤልያሊ፡ሆይ፥በዛፍሽ፡ፍሬና፡ በወይንሽ፡መከር፡የጦር፡ጩኸት፡ወድቋልና፥በእንባዬ፡አረካሻለኹ። 258 ዕብ.፥ዔግላ፡(ዕጕል•ግልገል፥እንቦሳ፥ጥጃ)። 259 ዕብ.፥ሽሊሺ፡(ሣልስት•ሦስተኚት)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
10ደስታና፡ሐሤትም፡ከፍሬያማው፡ዕርሻ፡ተወስዷል፥በወይኑም፡ቦታዎች፡ዝማሬና፡እልልታ፡ የለም፤በመጥመቂያም፡ወይን፡የሚረግጥ፡የለም፤የረጋጮቹን፡እልልታ፡አጥፍቻለኹ።
11ስለዚህ፥ልቤ፡ስለ፡ሞዐብ፥አንዠቴም፡ስለ፡ቂርሔሬስ፡እንደ፡መሰንቆ፡ትጮኻለች።
12ሞዐብም፡መጥቶ፡በኰረብታ፡መስገጃ፡ላይ፡በደከመና፡ለጸሎት፡ወደ፡መቅደሱ፡በገባ፡ጊዜ፡አያሸንፍም፡
13እግዚአብሔር፡በሞዐብ፡ላይ፡በድሮ፡ዘመን፡የተናገረው፡ነገር፡ይህ፡ነው።
14አኹን፡ግን፡እግዚአብሔር፦በሦስት፡ዓመት፡ውስጥ፡እንደ፡ምንደኛ፡ዓመት፡የሞዐብ፡ክብርና፡የሕዝቡ፡ ዅሉ፡ብዛት፡ይዋረዳል፥ቅሬታውም፡እጅግ፡ያነሰና፡የተጠቃ፡ይኾናል፡ይላል።