Skip to content
← Isaiah

Chapter 20 · Amharic

Isaiah

1የአሶር፡ንጉሥ፡ሳርጎን፡ተርታንን፡በሰደደ፡ጊዜ፥ርሱም፡ወደ፡አዛጦን፡በመጣ፡ጊዜ፥አዛጦንንም፡ወግቶ፡ በያዛት፡ጊዜ፥

2በዚያ፡ዓመት፡እግዚአብሔር፡የዓሞጽን፡ልጅ፡ኢሳይያስን፦ኺድ፥ማቅኽን፡ከወገብኽ፡ አውጣ፥ጫማኽንም፡ከእግርኽ፡አውልቅ፡ብሎ፡ተናገረው።እንዲህም፡አደረገ፥ዕራቍቱንም፡ባዶ፡እግሩንም፡ ኼደ።

3እግዚአብሔርም፡አለ፦ባሪያዬ፡ኢሳይያስ፡በግብጽና፡በኢትዮጵያ፡ላይ፡ሦስት፡ዓመት፡ለምልክትና፡ ለተኣምራት፡ሊኾን፡ዕራቍቱንና፡ባዶ፡እግሩን፡እንደ፡ኼደ፥

4እንዲሁ፡የአሶር፡ንጉሥ፡የግብጽንና፡የኢትዮጵያን፡ምርኮ፥ጐበዛዝቱንና፡ሽማግሌዎቹን፥ዕራቍታቸውንና፡ ባዶ፡እግራቸውን፡አድርጎ፥ገላቸውንም፡ገልጦ፥ለግብጽ፡ጕስቍልና፡ይነዳቸዋል።

5እነርሱም፡ከተስፋቸው፡ከኢትዮጵያ፡ከትምክሕታቸውም፡ከግብጽ፡የተነሣ፡ይፈራሉ፡ያፍሩማል፤

6በዚያም፡ቀን፡በዚች፡ባሕር፡ዳርቻ፡የሚቀመጡ፦እንሆ፥ከአሶር፡ንጉሥ፡እንድን፡ዘንድ፥ለርዳታ፡ወደ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እነርሱ፡የሸሸንበት፡ተስፋችን፡ይህ፡ነበረ፤እኛስ፡እንዴት፡እናመልጣለን፧ይላሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source