Skip to content
← Isaiah

Chapter 21 · Amharic

Isaiah

1በባሕር፡አጠገብ፡ስላለው፡ስለ፡ምድረ፡በዳ፡የተነገረ፡ሸክም።ዐውሎ፡ነፋስ፡ከደቡብ፡ እንደሚወጣ፥እንዲሁ፡ከሚያስፈራ፡አገር፡ከምድረ፡በዳ፡ይወጣል።

2ከባድ፡ራእይ፡ተነገረኝ፤ወንጀለኛው፡ይወነጅላል፥አጥፊውም፡ያጠፋል።ዔላም፡ሆይ፥ውጪ፤ሜዶን፡ ሆይ፥ክበቢ፤ትካዜውን፡ዅሉ፡አስቀርቻለኹ።

3ስለዚህ፥ወገቤ፡ሕመም፡ተሞላ፤እንደምትወልድ፡ሴት፡ምጥ፡ያዘኝ፤ከሕመሜ፡የተነሣ፡ አልሰማም፥ከድንጋጤም፡የተነሣ፡አላይም።

4ልቤ፡ተንበደበደ፥ድንጋጤ፡አስፈራኝ፥ተስፋ፡ያደረግኹትም፡ድንግዝግዝታ፡መንቀጥቀጥ፡ኾነብኝ።

5ማዕዱን፡ያዘጋጃሉ፥ምንጣፉንም፡ይዘረጋሉ፥ይበሉማል፥ይጠጡማል፤እናንተ፡መሳፍንት፡ ሆይ፥ተነሡ፥ጋሻውን፡አዘጋጁ።

6ጌታ፡እንዲህ፡ብሎኛልና፦ኺድ፥ጕበኛም፡አቁም፥የሚያየውንም፡ይናገር።

7በከብት፡የሚቀመጡትን፥ኹለት፡ኹለት፡እየኾኑ፡የሚኼዱት፡ፈረሰኛዎች፥በአህያዎች፡የሚቀመጡትንና፡ በግመሎች፡የሚቀመጡትን፡ባየ፡ጊዜ፡በጽኑ፡ትጋት፡አስተውሎ፡ተግቶም፡ያድምጥ።

8ያየውም፦ጌታ፡ሆይ፥ቀኑን፡ዅሉ፡ዘወትር፡በማማ፡ላይ፡ቆሜያለኹ፥ሌሊቱንም፡ዅሉ፡በመጠበቂያዬ፡ ላይ፡ተተክያለኹ፥

9እንሆም፥በፈረሶች፡የሚቀመጡ፥ኹለት፡ኹለት፡ኹነው፡የሚኼዱ፡ፈረሰኛዎች፡ይመጣሉ፡ብሎ፡ ጮኸ፤ርሱም፡መልሶ፦ባቢሎን፡ወደቀች፡ወደቀች፥የተቀረጹም፡የአማልክቷ፡ምስሎች፡ዅሉ፡በምድር፡ላይ፡ ተጥለው፡ደቀቁ፡አለ።

10እናንተ፡በዐውድማዬ፡ላይ፡የተወቃችኹ፡የዐውድማዬ፡ልጆች፡ሆይ፥ከእስራኤል፡አምላክ፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፡የሰማኹትን፡ነገርዃችኹ።

11ስለ፡ኤዶምያስ፡የተነገረ፡ሸክም።አንዱ፡ከሴይር።ጕበኛ፡ሆይ፥ሌሊቱ፡ምን፡ያኽል፡ነው፧ጕበኛ፡ ሆይ፥ሌሊቱ፡ምን፡ያኽል፡ነው፧ብሎ፡ጠራኝ።

12ጕበኛውም፦ይነጋል፡ድግሞም፡ይመሻል፤ትጠይቁ፡ዘንድ፡ብትወዱ፡ጠይቁ፤ተመልሳችኹም፡ኑ፡አለ።

13ስለ፡ዐረብ፡የተነገረ፡ሸክም።የድዳናውያን፡ነጋዴዎች፡ሆይ፥በዐረብ፡ዱር፡ውስጥ፡ታድራላችኹ።

14በቴማን፡የምትኖሩ፡ሆይ፥ወደተጠሙት፡ሰዎች፡ውሃ፡አምጡ፡እንጀራ፡ይዛችኹ፡የሸሹትን፡ሰዎች፡ ተቀበሏቸው።

15ከሰይፍ፥ከተመዘዘው፡ሰይፍ፥ከተለጠጠውም፡ቀስት፡ከጽኑም፡ሰልፍ፡ሸሽተዋልና።

16ጌታ፡እንዲህ፡ብሎኛልና፦እንደ፡ምንደኛ፡ዓመት፡ባንድ፡ዓመት፡ውስጥ፡የቄዳር፡ክብር፡ዅሉ፡ ይጠፋል፤

17ከቀስተኛዎች፡ቍጥር፡የቀሩት፥የቄዳር፡ልጆች፡ኀያላን፥ያንሳሉ፤የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ ተናግሯልና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source