Skip to content
← Isaiah

Chapter 22 · Amharic

Isaiah

1ስለራእይ፡ሸለቆ፡የተነገረ፡ሸክም።እናንተ፡ዅላችኹ፡ወደ፡ሰገነት፡መውጣታችኹ፡ምን፡ኾናችዃል፧

2ጩኸትና፡ፍጅት፡የተሞላብሽ፡ከተማ፥ደስታ፡ያለሽ፡ከተማ፡ሆይ፥ባንቺ፡ውስጥ፡የተገደሉት፡በሰይፍ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የተገደሉ፡አይደሉም፥በሰልፍም፡የሞቱ፡አይደሉም።

3አለቃዎችሽ፡ዅሉ፡በአንድነት፡ሸሹ፥ያለቀስትም፡ተማረኩ፤ከሩቅ፡ሸሽተው፡ከአንቺ፡ዘንድ፡የተገኙት፡ ዅሉ፡በአንድነት፡ታሰሩ።

4ስለዚህ፦ፊታችኹን፡ከእኔ፡ዘንድ፡አርቁ፤መራራ፡ልቅሶ፡አለቅሳለኹ፤ስለ፡ሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ጥፋት፡ ታጽናኑኝ፡ዘንድ፡አትድከሙ፡አልኹ።

5ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የድንጋጤና፡የመረገጥ፡የድብልቅልቅም፡ቀን፥የቅጥርም፡መፍረስ፡ ወደ፡ተራራም፡መጮኽ፡በራእይ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ኾኗል።

6ዔላምም፡ከሠረገለኛዎችና፡ከፈረሰኛዎች፡ጋራ፡ኾኖ፡አፎቱን፡ተሸከመ፥ቂርም፡ጋሻውን፡ገለጠ።

7መልካሞቹንም፡ሸለቆዎችሽን፡ሠረገላዎች፡ሞሉባቸው፥ፈረሰኛዎችም፡መቆሚያቸውን፡በበር፡ላይ፡አደረጉ።

8የይሁዳንም፡መጋረጃ፡ገለጠ፤በዚያም፡ቀን፡በዱር፡ቤት፡የነበረውን፡የጦር፡ዕቃ፡ተመለከትኽ፥

9የዳዊትም፡ከተማ፡ፍራሾች፡እንደ፡በዙ፡አይታችዃል፥የታችኛውንም፡ኵሬ፡ውሃ፡አከማችታችዃል፥

10የኢየሩሳሌምን፡ቤቶች፡ቈጠራችኹ፡ቅጥሩንም፡ለማጥናት፡ቤቶችን፡አፈረሳችኹ።

11በአሮጌው፡ኵሬ፡ላለው፡ውሃ፡በኹለቱ፡ቅጥር፡መካከል፡መከማቻ፡ሠራችኹ፤ይህን፡ያደረገውን፡ግን፡ አልተመለከታችኹም፥ቀድሞ፡የሠራውንም፡አላያችኹም።

12በዚያም፡ቀን፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ልቅሶና፡ወደ፡ዋይታ፡ራስን፡ወደ፡መንጨትና፡ ማቅንም፡ወደ፡መልበስ፡ጠራ።

13እንሆም፥ሐሜትና፡ደስታ፡በሬውንና፡በጉንም፡ማረድ፡ሥጋንም፡መብላት፡የወይን፡ጠጅንም፡መጠጣት፡ ኾነዋል፤እናንተ፦ነገ፡እንሞታለንና፡እንብላ፡እንጠጣ፡ብላችዃል።

14ይህም፡ነገር፡በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ዦሮ፡ተሰማ፦እስክትሞቱ፡ድረስ፡ይህ፡በደል፡በእውነት፡ አይሰረይላችኹም፡ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

15የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በቤቱ፡ውስጥ፡ወደ፡ተሾመው፡ወደዚህ፡አዛዥ፡ወደ፡ ሳምናስ፡ኺድ፥እንዲህም፡በለው፦

16መቃብር፡በዚህ፡ያስወቀርኽ፥ከፍ፡ባለው፡ስፍራ፡መቃብር፡ያሠ፟ራኽ፥በድንጋይም፡ውስጥ፡ለራስኽ፡ መኖሪያ፡ያሳነጽኽ፥በዚህ፡ምን፡አለኽ፧በዚህስ፡ባንተ፡ዘንድ፡ማን፡አለ፧

17እንሆ፥እግዚአብሔር፡በኀይል፡ወርውሮ፡ይጥልኻል፥አጠንክሮም፡ይጨብጥኻል።

18ጠቅሎ፟ም፡ያንከባልልኻል፥ወደ፡ሰፊዪቱም፡ምድር፡እንደ፡ኳስ፡ይጥልኻል፤አንተ፡የጌታኽ፡ቤት፡ዕፍረት! በዚያ፡ትሞታለኽ፥በዚያም፡የክብርኽ፡ሠረገላዎች፡ይኾናሉ።

19ከአዛዥነት፡ሥራኽ፡አሳድድኻለኹ፥ከሹመትኽም፡ትሻራለኽ።

20በዚያም፡ቀን፡ባሪያዬን፡የኬልቅያስን፡ልጅ፡ኤልያቄምን፡እጠራለኹ፥

21መጐናጸፊያኽንም፡አለብሰዋለኹ፥በመታጠቂያኽም፡አስታጥቀዋለኹ፥ሹመትኽንም፡በእጁ፡አሳልፌ፡ እሰጠዋለኹ፤በኢየሩሳሌምም፡ለሚኖሩ፡ለይሁዳም፡ቤት፡አባት፡ይኾናል።

22የዳዊትንም፡ቤት፡መክፈቻ፡በጫንቃው፡ላይ፡አኖራለኹ፤ርሱም፡ይከፍታል፡የሚዘጋም፡የለም፡ርሱም፡ ይዘጋል፡የሚከፍትም፡የለም።

23በታመነም፡ስፍራ፡እንደ፡ችንካር፡እተክለዋለኹ፥ለአባቱም፡ቤት፡የክብር፡ዙፋን፡ይኾናል።

24የአባቱንም፡ቤት፡ክብር፡ዅሉ፡ልጆቹንም፡የልጅ፡ልጆቹንም፥ከጽዋ፡ዕቃ፡ዠምሮ፡እስከማድጋ፡ዕቃ፡ ድረስ፥ታናናሹን፡ዕቃ፡ዅሉ፡ይሰቅሉበታል።

25በዚያ፡ቀን፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥በታመነው፡ስፍራ፡የተከለው፡ችንካር፡ይወልቃል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ተሰብሮም፡ይወድቃል፥በርሱም፡ላይ፡የተሰቀለው፡ሸክም፡ይጠፋል፡እግዚአብሔር፡ተናግሯልና።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source