Skip to content
← Isaiah

Chapter 25 · Amharic

Isaiah

1አቤቱ፥አንተ፡አምላኬ፡ነኽ፤ድንቅን፡ነገር፡የዱሮ፡ምክርን፡በታማኝነትና፡በእውነት፡አድርገኻልና፥ከፍ፡ ከፍ፡አደርግኻለኹ፥ስምኽንም፡አመሰግናለኹ።

2ከተማዪቱን፡የድንጋይ፡ክምር፥የተመሸገችውን፡ከተማ፡ውድማ፡እንድትኾን፥የኃጥኣንንም፡አዳራሽ፡ ከተማ፡እንዳትኾን፡አድርገኻል፤ከቶ፡አትሠራም።

3ስለዚህ፥ኀያላኑ፡ወገኖች፡ያከብሩኻል፥የጨካኞች፡አሕዛብ፡ከተማም፡ትፈራኻለች።

4የጨካኞችም፡ቍጣ፡እስትንፋስ፡ቅጥርን፡እንደሚመታ፡ዐውሎ፡ነፋስ፡በኾነ፡ጊዜ፥ለድኻው፡ መጠጊያ፥ለችግረኛው፡በጭንቁ፡ጊዜ፡መጠጊያ፥ከውሽንፍር፡መሸሸጊያ፡ከሙቀትም፡ጥላ፡ኾነኻል።

5እንደ፡ሙቀት፡በደረቅ፡ስፍራ፡የኃጥኣንን፡ጩኸት፡ዝም፡ታሠኛለኽ፤ሙቀትም፡በደመና፡ጥላ፡ እንዲበርድ፡እንዲሁ፡የጨካኞች፡ዝማሬ፡ይዋረዳል።

6የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ለሕዝብ፡ዅሉ፡በዚህ፡ተራራ፡ላይ፡ታላቅ፡የሰባ፡ግብዣ፥ያረጀ፡የወይን፡ ጠጅ፥ቅልጥም፡የሞላባቸው፡የሰቡ፡ነገሮች፥የጥሩና፡ያረጀ፡የወይን፡ጠጅ፡ግብዣ፡ያደርጋል።

7በዚህም፡ተራራ፡ላይ፡በወገኖች፡ዅሉ፡ላይ፡የተጣለውን፡መጋረጃ፥በአሕዛብም፡ዅሉ፡ላይ፡የተዘረጋውን፡ መሸፈኛ፡ያጠፋል።

8ሞትን፡ለዘለዓለም፡ይውጣል፥ጌታ፡እግዚአብሔርም፡ከፊት፡ዅሉ፡እንባን፡ያብሳል፥የሕዝቡን፡ስድብ፡ ከምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ያስወግዳል፤እግዚአብሔር፡ተናግሯልና።

9በዚያም፡ቀን፦እንሆ፥አምላካችን፡ይህ፡ነው፤ተስፋ፡አድርገነዋል፥ያድነንማል፤እግዚአብሔር፡ይህ፡ ነው፤ጠብቀነዋል፤በማዳኑ፡ደስ፡ይለናል፡ሐሤትም፡እናደርጋለን፡ይባላል።

10የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በዚህ፡ተራራ፡ላይ፡ታርፋለች፥ጭድም፡በጭቃ፡ውስጥ፡እንደሚረገጥ፡እንዲሁ፡ ሞዐብ፡በስፍራው፡ይረገጣል።

11ዋናተኛም፡ሲዋኝ፡እጁን፡እንደሚዘረጋ፥እንዲሁ፡በመካከሉ፡እጁን፡ይዘረጋል፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ ትዕቢቱን፡ከእጁ፡ተንኰል፡ጋራ፡ያዋርዳል።

12የተመሸገውንም፡ከፍ፡ከፍ፡ያለውንም፡ቅጥርኽን፡ዝቅ፡ያደርገዋል፥ያዋርደውማል፥ወደ፡መሬትም፡ እስከ፡ዐፈር፡ድረስ፡ይጥለዋል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source