1በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ፈጣኑን፡እባብ፡ሌዋታንን፡ጠማማውንም፡እባብ፡ሌዋታንን፡በጠንካራ፡ በታላቅም፡በብርቱም፡ሰይፍ፡ይቀጣል፥በባሕርም፡ውስጥ፡ያለውን፡ዘንዶ፡ይገድላል።
2በዚያም፡ቀን፡ለተወደደው፡የወይን፡ቦታ፡ተቀኙለት።
3እኔ፡እግዚአብሔር፡ጠባቂው፡ነኝ፤ዅልጊዜ፡አጠጣዋለኹ፤ማንም፡እንዳይጐዳው፡በሌሊትና፡በቀን፡ እጠብቀዋለኹ።
4አልቈጣም፤ሾኽና፡ኵርንችት፡በእኔ፡ላይ፡ምነው፡በሰልፍ፡በነበሩ! በእነርሱ፡ላይ፡ተራምጄ፡በአንድነት፡ ባቃጠልዃቸው፡ነበር።
5ወይም፡ጕልበቴን፡ይያዝ፥ከእኔ፡ጋራ፡ሰላም፡ያድርግ፤ከእኔ፡ጋራ፡ሰላም፡ያድርግ።
6በሚመጣው፡ዘመን፡ያዕቆብ፡ሥር፡ይሰዳ፟ል፥እስራኤልም፡ያብባል፡ይጨበጭብማል፤በፍሬያቸውም፡ የዓለሙን፡ፊት፡ይሞላሉ።
7በእውኑ፡የመቱትን፡እንደ፡መታ፡እንዲሁ፡ርሱን፡መታውን፧ወይስ፡እነርሱ፡እንደ፡ተገደሉበት፡መገደል፡ ርሱ፡ተገድሏልን፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
8ነዳቸው፡ሰደዳቸው፡ቀሠፋቸው፤የምሥራቅ፡ነፋስ፡እንደሚነፍስበት፡ቀን፡በጠንካራ፡ዐውሎ፡አስወገዳቸው።
9ስለዚህም፡የማምለኪያ፡ዐጸዶችና፡የፀሓይ፡ምስሎች፡ዳግመኛ፡እንዳይነሡ፡የመሠዊያውን፡ድንጋይ፡ዅሉ፡ እንደ፡ደቀቀ፡እንደ፡ኖራ፡ድንጋይ፡ባደረገ፡ጊዜ፥እንዲሁ፡የያዕቆብ፡በደል፡ይሰረያል፥ይህም፡ኀጢአትን፡ የማስወገድ፡ፍሬ፡ዅሉ፡ነው።
10የተመሸገችው፡ከተማ፡ብቻዋን፡ኾነች፤እንደ፡ምድረ፡በዳ፡ኾና፡የተፈታችና፡የተተወች፡መኖሪያ፡ ናት፤በዚያም፡ጥጃ፡ይሰማራል፡በዚያም፡ይተኛል፡ቅርንጫፏንም፡ይበላል።
11ጫፎቿ፡በደረቁ፡ጊዜ፡ይሰበራሉ፥ሴቶችም፡መጥተው፡ያቃጥሏቸዋል፤የማያስተውል፡ሕዝብ፡ ነውና፥ስለዚህ፡ፈጣሪው፡አይራራለትም፡ሠሪውም፡ምሕረት፡አያደርግለትም።
12በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤እግዚአብሔር፡ከወንዝ፡ፈሳሽ፡ዠምሮ፡እስከግብጽ፡ወንዝ፡ድረስ፡ እኽሉን፡ይወቃል፥እናንተም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥አንድ፡ባንድ፡ትሰበሰባላችኹ።
13በዚያም፡ቀን፡እንዲህ፡ይኾናል፤ታላቅ፡መለከት፡ይነፋል፥በአሶርም፡የጠፉ፥በግብጽ፡ምድርም፡የተሰደዱ፡ ይመጣሉ፥በተቀደሰውም፡ተራራ፡በኢየሩሳሌም፡ለእግዚአብሔር፡ይሰግዳሉ።