Skip to content
← Isaiah

Chapter 28 · Amharic

Isaiah

1ለኤፍሬም፡ሰካሮች፡ትዕቢት፡አክሊል፥በወይን፡ጠጅ፡ለተሸነፉ፡በወፍራም፡ሸለቋቸው፡ራስ፡ላይ፡ላለችም፡ ለረገፈች፡ለክብሩ፡ጌጥ፡አበባ፡ወዮ!

2እንሆ፥በጌታ፡ዘንድ፡ኀያል፡ብርቱ፡የኾነ፡አለ።እንደ፡በረዶ፡ወጨፎ፥እንደሚያጠፋም፡ዐውሎ፡ ነፋስ፥እንደሚያጥለቀልቅም፡እንደ፡ታላቅ፡ውሃ፡ፈሳሽ፡በጠነከረ፡እጅ፡ወደ፡ምድር፡ይጥላል።

3የኤፍሬም፡ሰካሮች፡ትዕቢት፡አክሊል፡በእግር፡ይረገጣል፤

4በወፍራሙ፡ሸለቆ፡ራስ፡ላይ፡ያለች፡የረገፈች፡የክብሩ፡ጌጥ፡አበባ፡ከመከር፡በፊት፡አስቀድማ፡ እንደምትበስል፡በለስ፡ትኾናለች፤ሰው፡ባያት፡ጊዜ፡በእጁ፡እንዳለች፡ይበላታል።

5በዚያ፡ቀን፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ለቀሩት፡ሕዝቡ፡የክብር፡ዘውድና፡የጌጥ፡አክሊል፡ይኾናል፤

6በፍርድ፡ወንበር፡ላይ፡ለሚቀመጥም፡የፍርድ፡መንፈስ፥ሰልፉን፡ወደ፡በር፡ለሚመልሱም፡ኀይል፡ይኾናል።

7እነዚህም፡ደግሞ፡ከወይን፡ጠጅ፡የተነሣ፡ይስታሉ፥ከሚያሰክርም፡መጠጥ፡የተነሣ፡ይፋንናሉ፤ካህኑና፡ ነቢዩ፡ከሚያሰክር፡መጠጥ፡የተነሣ፡ይስታሉ፥በወይን፡ጠጅም፡ይዋጣሉ፥ከሚያሰክርም፡መጠጥ፡የተነሣ፡ ይፋንናሉ፤በራእይ፡ይስታሉ፥በፍርድም፡ይሰናከላሉ።

8ማእዱ፡ዅሉ፡ትፋትንና፡ርኵሰትን፡ተሞልቷታል፤ንጹሕ፡ስፍራ፡እንኳ፡የለም።

9ዕውቀትን፡ለማን፡ያስተምረዋል፧ወይስ፡ወሬ፡ማስተዋልን፡ለማን፡ይሰጣል፧ወተትን፡ለተዉ፡ወይስ፡ ጡትን፡ለጣሉ፡ነውን፧

10ትእዛዝ፡በትእዛዝ፥ትእዛዝ፡በትእዛዝ፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ጥቂት፡በዚህ፡ጥቂት፡ በዚያ፡ነው።

11በባዕድ፡አፍ፡በልዩም፡ልሳን፡ለዚህ፡ሕዝብ፡ይናገራል፤ርሱም፦ዕረፍት፡ይህች፡ናት፥

12የደከመውን፡አሳርፉ፤ይህችም፡ማረፊያ፡ናት፡አላቸው፤እነርሱ፡ግን፡መስማትን፡እንቢ፡አሉ።

13ስለዚህ፥ኼደው፡ወደ፡ዃላ፡እንዲወድቁ፥እንዲሰበሩም፥ተጠምደውም፡እንዲያ፟ዙ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ ትእዛዝ፡በትእዛዝ፥ትእዛዝ፡በትእዛዝ፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ሥርዐት፡በሥርዐት፥ጥቂት፡በዚህ፡ጥቂት፡በዚያ፡ ይኾንላቸዋል።

14ስለዚህ፥በኢየሩሳሌም፡ያለውን፡ሕዝብ፡የምትገዙ፡ፌዘኛዎች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

15እናንተም፦ከሞት፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አድርገናል፥ከሲኦልም፡ጋራ፡ተማምለናል፤ሐሰትን፡መሸሸጊያችን፡ አድርገናልና፥በሐሰትም፡ተሰውረናልና፥የሚትረፈረፍ፡መቅሠፍት፡ባለፈ፡ጊዜ፡አይደርስብንም፡ስላላችኹ፥

16ስለዚህ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በጽዮን፡ድንጋይን፡ለመሠረት፡ አስቀምጣለኹ፤የተፈተነውን፥የከበረውን፥መሠረቱ፡የጸናውን፡የማእዘን፡ድንጋይ፤የሚያምን፡አያፍርም።

17ለገመድ፡ፍርድን፡ለቱንቢም፡ጽድቅን፡አደርጋለኹ፤በረዶውም፡የሐሰትን፡መሸሸጊያ፡ ይጠርጋል፥ውሃዎችም፡መሰወሪያውን፡ያሰጥማሉ።

18ከሞትም፡ጋራ፡ያደረጋችኹት፡ቃል፡ኪዳን፡ይፈርሳል፥ከሲኦልም፡ጋራ፡የተማማላችኹት፡መሐላ፡ አይጸናም፤የሚትረፈረፍ፡መቅሠፍት፡ባለፈ፡ጊዜ፡ትረገጡበታላችኹ።

19ባለፈም፡ጊዜ፡ይወስዳችዃል፤ማለዳ፡ማለዳ፡ቀንና፡ሌሊት፡ያልፋል፤ወሬውንም፡ማስተዋል፡ድንጋጤ፡ ይኾናል።

20ሰው፡በርሱ፡ላይ፡ተዘርግቶ፡ቢተኛ፡ዐልጋው፡ዐጪር፡ነው፤ሰውም፡ሰውነቱን፡መሸፈን፡ቢወድ፟፡ መጐናጸፊያ፡ጠባብ፡ነው።

21እግዚአብሔርም፡ሥራውን፡ማለት፡እንግዳ፡ሥራውን፡ይሠራ፡ዘንድ፥አድራጎቱንም፡ማለት፡ያልታወቀውን፡ አድራጎቱን፡ያደርግ፡ዘንድ፡በፐራሲም፡ተራራ፡እንደ፡ነበረ፡ይነሣል፥በገባዖንም፡ሸለቆ፡እንደ፡ነበረ፡ይቈጣል።

22አኹንም፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡የሚጸናውን፡የጥፋት፡ትእዛዝ፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ ሰምቻለኹና፥እስራት፡እንዳይጸናባችኹ፡አታፊዙ።

23አድምጡ፥ድምፄንም፡ስሙ፤ልብ፡አድርጉ፥ንግግሬንም፡ስሙ።

24በእውኑ፡ገበሬ፡ሊዘራ፡ዅልጊዜ፡ያርሳልን፧ወይስ፡ዅልጊዜ፡ዕርሻውን፡ይገለግላልን፧

25ጓሉንስ፡ይከሰክሳልን፧ዕርሻውን፡ባስተካከለ፡ጊዜ፡ጥቍሩን፡አዝሙድ፥ከሙኑንም፥ስንዴውንም፡ በተርታ፥ገብሱንም፡በስፍራው፥ዐጃንም፡በደረጃው፡የሚዘራ፡አይደለምን፧

26ይህንም፡ብልኀት፡አምላኩ፡ያስታውቀዋል፡ያስተምረውማል።

27ጥቍሩ፡አዝሙድ፡በተሳለች፡መኼጃ፡አያኼድም፥የሠረገላም፡መንኰራኵር፡በከሙን፡ላይ፡ አይዞርም፤ነገር፡ግን፥ጥቍሩ፡አዝሙድ፡በሽመል፥ከሙኑም፡በበትር፡ይወቃል።

28የእንጀራ፡እኽል፡ይደቃ፟ልን፧ለዘለዓለም፡አያኼደውም፤የሠረገላውን፡መንኰራኵርና፡ፈረሶቹን፡ምንም፡ ቢያስኬድበት፡አያደቀ፟ውም።

29ይህም፡ደግሞ፡ድንቅ፡ምክር፡ከሚመክር፡በግብሩም፡ማለፊያ፡ከኾነው፡ከሰራዊት፡ጌታ፡ከእግዚአብሔር፡ ወጥቷል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source