Skip to content
← Isaiah

Chapter 31 · Amharic

Isaiah

1ስለ፡ርዳታ፡ወደ፡ግብጽ፡ለሚወርዱ፡በፈረሶችም፡ለሚደገፉ፥ስለ፡ብዛታቸውም፡በሠረገላዎች፥እጅግ፡ ብርቱዎችም፡ስለ፡ኾኑ፡በፈረሰኛዎች፡ለሚታመኑ፥ወደእስራኤልም፡ቅዱስ፡ለማይመለከቱ፡እግዚአብሔርንም፡ ለማይፈልጉ፡ወዮላቸው!

2ርሱ፡ግን፡ደግሞ፡ጠቢብ፡ነው፥ክፉንም፡ነገር፡ያመጣል፥ቃሉንም፡አይመልስም፥በክፉም፡አድራጊዎች፡ ቤት፡ላይ፡በደልንም፡በሚሠሩ፡ረዳት፡ላይ፡ይነሣል።

3ግብጻውያን፡ሰዎች፡እንጂ፡አምላክ፡አይደሉም፥ፈረሶቻቸውም፡ሥጋ፡እንጂ፡መንፈስ፡ አይደሉም፤እግዚአብሔርም፡እጁን፡በዘረጋ፡ጊዜ፥ረጂው፡ይሰናከላል፡ተረጂውም፡ይወድቃል፥ዅሉም፡ባንድ፡ ላይ፡ይጠፋሉ።

4እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይለኛልና፦አንበሳ፡ወይም፡የአንበሳ፡ደቦል፡በንጥቂያው፡ላይ፡ሲያገሣ፥ብዙ፡ እረኛዎች፡ቢከማቹበት፡ከቃላቸው፡እንደማይፈራ፡ከድምፃቸውም፡እንደማይዋረድ፥እንዲሁ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እግዚአብሔር፡በጽዮን፡ተራራና፡በኰረብታዋ፡ላይ፡ይዋጋ፡ዘንድ፡ይወርዳል።

5እንደሚበር፟፡ወፍ፡እንዲሁ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ኢየሩሳሌምን፡ ይጋርዳታል፤ይከልላታል፥ይታደጋታል፥ዐልፎም፡ያድናታል።

6እናንተ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥አጥብቃችኹ፡ወደዐመፃችኹበት፡ተመለሱ።

7በዚያም፡ቀን፡እያንዳንዳቸው፡እጆቻቸው፡ለኀጢአት፡የሠሩላቸውን፡የብሩንና፡የወርቁን፡ጣዖቶቻቸውን፡ ይጥላሉ።

8አሶርም፡የሰው፡ባልኾነ፡ሰይፍ፡ይወድቃል፥የሰውም፡ያልኾነ፡ሰይፍ፡ይበላዋል፤ከሰይፍም፡ይሸሻሉ፡ ጐበዛዝቱም፡ገባሮች፡ይኾናሉ።

9ዐምባው፡ከፍርሀት፡የተነሣ፡ያልፋል፥መሳፍንቱም፡ከዐላማው፡የተነሣ፡ይደነግጣሉ፥ይላል፡እሳቱ፡በጽዮን፡ እቶኑም፡በኢየሩሳሌም፡የኾነ፡እግዚአብሔር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source