Skip to content
← Isaiah

Chapter 32 · Amharic

Isaiah

1እንሆ፥ንጉሥ፡በጽድቅ፡ይነግሣል፥መሳፍንትም፡በፍርድ፡ይገዛሉ።

2ሰውም፡ከነፋስ፡እንደ፡መሸሸጊያ፡ከዐውሎ፡ነፋስም፡እንደ፡መጠጊያ፥በጥም፡ቦታም፡እንደ፡ወንዝ፡ ፈሳሽ፥በበረሓም፡አገር፡እንደ፡ትልቅ፡ድንጋይ፡ጥላ፡ይኾናል።

3የሚያዩትም፡ሰዎች፡ዐይኖች፡አይጨፈኑም፥የሚሰሙትም፡ዦሮዎች፡ያደምጣሉ።

4ጥንቃቄ፡የሌላቸው፡ሰዎች፡ልብ፡ዕውቀትን፡ታስተውላለች፥የተብታቦችም፡ምላስ፡ደኅና፡አድርጋ፡ ትናገራለች።

5ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ሰነፍ፡ከበርቴ፡ተብሎ፡አይጠራም፥ንፉግም፡ለጋስ፡አይባልም።

6ሰነፍ፡ግን፡ስንፍናን፡ይናገራል፥ልቡም፡ዝንጉነትን፡ይፈጽም፡ዘንድ፡በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ስሕተትን፡ ይናገር፡ዘንድ፡የተራበችውንም፡ሰውነት፡ባዶ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ከተጠማም፡ሰው፡መጠጥን፡ይቈርጥ፡ዘንድ፡ በደልን፡ይሠራል።

7የንፉግም፡ዕቃ፡ክፉ፡ናት፤ችግረኛ፡ቅን፡ነገርን፡በተናገረ፡ጊዜ፡እንኳ፡ርሱ፡በሐሰት፡ቃል፡ድኻውን፡ ያጠፋ፡ዘንድ፡ክፉን፡ዐሳብ፡ያስባል።

8ከበርቴ፡ሰው፡ግን፡ለመከበር፡ያስባል፥በመከበርም፡ጸንቶ፡ይኖራል።

9እናንተ፡ዓለመኛዎች፡ሴቶች፡ሆይ፥ተነሡ፡ድምፄንም፡ስሙ፤እናንተ፡ተማምናችኹ፡የምትቀመጡ፡ሴቶች፡ ልጆች፡ሆይ፥ንግግሬን፡አድምጡ።

10እናንተ፡ተማምናችኹ፡የምትቀመጡ፡ሴቶች፡ሆይ፥ወይንን፡መቍረጥ፡ይጠፋልና፥ፍሬም፡ማከማቸት፡ አይመጣምና፡ከዓመትና፡ከጥቂት፡ቀን፡በዃላ፡ትንቀጠቀጣላችኹ።

11እናንተ፡ዓለመኛዎች፡ሴቶች፡ሆይ፥ተጠንቀቁ፤ተማምናችኹም፡የምትቀመጡ፡ ሆይ፥ተንቀጥቀጡ፤ልብሳችኹን፡አውልቁ፥ዕራቍታችኹን፡ኹኑ፥ወገባችኹንም፡በማቅ፡ታጠቁ።

12ስለተወደደችውም፡ዕርሻ፡ስለሚያፈራውም፡ወይን፡ደረታችኹን፡ድቁ።

13በሕዝቤ፡ምድር፡ላይ፥በደስታ፡ከተማ፡ባሉት፡በደስታ፡ቤቶች፡ዅሉ፡ላይ፡ሾኽና፡ኵርንችት፡ ይወጣባቸዋል፤

14አዳራሹ፡ወና፡ትኾናለችና፥የብዙ፡ሰውም፡ከተማ፡ትለቀቃለችና፥ዐምባውና፡ግንቡም፡ለዘለዓለም፡ ዋሻ፥የምድረ፡በዳም፡አህያ፡ደስታ፥የመንጋዎችም፡ማሰማሪያ፡ይኾናልና።

15ይህም፥መንፈስ፡ከላይ፡እስኪፈስ፟ልን፥ምድረ፡በዳውም፡ፍሬያማ፡ዕርሻ፡እስኪኾን፥ፍሬያማውም፡ዕርሻ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ዱር፡ተብሎ፡እስኪቈጠር፡ድረስ፡ይኾናል።

16ከዚያ፡በዃላ፡ፍርድ፡በምድረ፡በዳ፡ይኖራል፥ጽድቅም፡በፍሬያማው፡ዕርሻ፡ያድራል።

17የጽድቅም፡ሥራ፡ሰላም፥የጽድቅም፡ፍሬ፡ለዘለዓለም፡ጸጥታና፡መታመን፡ይኾናል።

18ሕዝቤም፡በሰላም፡ማደሪያ፡በታመነም፡ቤት፡በጸጥተኛ፡ማረፊያ፡ይቀመጣል።

19በረዶ፡ግን፡በዱር፡ላይ፡ይወርዳል፥ከተማም፡ፈጽማ፡ትዋረዳለች።

20እናንተ፡የበሬና፡የአህያ፡እግር፡እየነዳችኹ፡በውሃ፡ዅሉ፡አጠገብ፡የምትዘሩ፡ብፁዓን፡ናችኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source