Skip to content
← Isaiah

Chapter 33 · Amharic

Isaiah

1አንተ፡ሳትጠፋ፡የምታጠፋ፥ባንተም፡ላይ፡ወንጀል፡ሳይደረግ፡ወንጀል፡የምታደርግ፡ወዮልኽ! ማጥፋትን፡ በተውኽ፡ጊዜ፡ትጠፋለኽ፤መወንጀልንም፡በተውኽ፡ጊዜ፡ይወነጅሉኻል።

2አቤቱ፥ማረን፤አንተን፡ተማምነናል፤ጧት፡ጧት፡ክንድ፡በመከራም፡ጊዜ፡ማዳን፡ኹነን።

3ከፍጅት፡ድምፅ፡ወገኖች፡ሸሹ፥በመነሣትኽም፡አሕዛብ፡ተበተኑ።

4አንበጣ፡እንደሚሰበስብ፡ምርኳችኹ፡ትሰበሰባለች፥ኵብኵባም፡እንደሚዘል፟፡ሰዎች፡ይዘሉ፟በታል።

5እግዚአብሔር፡በአርያም፡ተቀምጧልና፥ከፍ፡ከፍ፡አለ፤ጽዮንን፡በፍርድና፡በጽድቅ፡ሞላት።

6የዘመንኽም፡ጸጥታ፥የመድኀኒት፡ብዛት፥ጥበብና፡ዕውቀት፡ይኾናል፤እግዚአብሔርን፡መፍራት፡መዝገቡ፡ ነው።

7እንሆ፥ኀይለኛዎቻቸው፡በሜዳ፡ይጮኻሉ፤የሰላም፡መልእክተኛዎች፡መራራ፡ልቅሶ፡ያለቅሳሉ።

8መንገዶች፡ባድማ፡ኾኑ፥ተላላፊም፡ቀረ፤ርሱም፡ቃል፡ኪዳንን፡አፈረሰ፡ከተማዎችንም፡ናቀ፡ሰውንም፡ አልተመለከተም።

9ምድሪቱ፡አለቀሰች፡ከሳችም፤ሊባኖስ፡ዐፈረ፡ጠወለገም፤ሳሮን፡እንደ፡ምድረ፡በዳ፡ኾነ፤ባሳንና፡ ቀርሜሎስ፡ቅጠላቸውን፡አረገፉ።

10አኹን፡እነሣለኹ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤አኹን፡እከበራለኹ፤አኹን፡ከፍ፡ከፍ፡እላለኹ።

11ገለባን፡ትፀንሳላችኹ፥እብቅንም፡ትወልዳላችኹ፤እስትንፋሳችኹ፡የምትበላችኹ፡እሳት፡ናት።

12አሕዛብም፡እንደ፡ተቃጠለ፡ኖራ፥ተቈርጦም፡በእሳት፡እንደ፡ተቃጠለ፡ሾኽ፡ይኾናሉ።

13እናንተ፡በሩቅ፡ያላችኹ፡የሠራኹትን፡ስሙ፥እናንተም፡በቅርብ፡ያላችኹ፡ኀይሌን፡ዕወቁ።

14በጽዮን፡ያሉ፡ኀጢአተኛዎች፡ፈሩ፤መንቀጥቀጥ፡ዝንጉዎቹን፡ያዘ፤ከምትበላ፡እሳት፡ጋራ፡መኖርን፡ የሚችል፡ከእኛ፡ማን፡አለ፧ለዘለዓለምም፡ከምትነድ፟፡እሳት፡ጋራ፡መኖርን፡የሚችል፡ከእኛ፡ማን፡አለ፧

15በጽድቅ፡የሚኼድ፡ቅን፡ነገርንም፡የሚናገር፥በሽንገላ፡የሚገኝ፡ትርፍን፡የሚንቅ፥መማለጃን፡ ከመጨበጥ፡እጁን፡የሚያራግፍ፥ደም፡ማፍሰስን፡ከመስማት፡ዦሮዎቹን፡የሚያደነቍር፥ክፋትንም፡ከማየት፡ ዐይኖቹን፡የሚጨፍን፡ነው።

16ርሱ፡ከፍ፡ባለ፡ስፍራ፡ይቀመጣል፤ጠንካራ፡ዐምባ፡መጠጊያው፡ይኾናል፤እንጀራም፡ ይሰጠዋል፥ውሃውም፡የታመነች፡ትኾናለች።

17ዐይኖችኽ፡ንጉሥን፡በውበቱ፡ያዩታል፤እነርሱም፡በሩቅ፡ያለች፡ምድርን፡ያይዋታል።

18ልብኽም፦ጸሓፊ፡ወዴት፡አለ፧መዛኝስ፡ወዴት፡አለ፧ግንቦቹንስ፡የቈጠረ፡ወዴት፡አለ፧ብሎ፡ የሚያስፈራ፡ነገር፡ያስባል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

19ጨካኝን፡ሕዝብ፥ቋንቋው፡ለማስተዋል፡ጥልቅ፡የኾነውንና፡አንደበቱ፡ለማስተዋል፡ጸያፍ፡የኾነውን፡ ሕዝብ፥አታይም።

20የበዓላችንን፡ከተማ፡ጽዮንን፡ተመልከት፤ዐይኖችኽ፡የሰላም፡ማደሪያ፥ካስማውም፡ለዘለዓለም፡የማይነቀል፡ አውታሩም፡ዅሉ፡የማይበጠስ፥የማይወገድ፡ድንኳን፡የኾነውን፡ኢየሩሳሌምን፡ያያሉ።

21እግዚአብሔር፡በዚያ፡የሰፉ፡ወንዞችና፡የመስኖች፡ስፍራ፡ኾኖ፡ከእኛ፡ጋራ፡በግርማ፡ይኾናል፤የሚቀዘፉ፡ መርከቦች፡አይገቡባትም፥ታላላቆችም፡መርከቦች፡አያልፉባትም።

22እግዚአብሔር፡ፈራጃችን፡ነው፥እግዚአብሔር፡ሕግን፡ሰጪያችን፡ነው፥እግዚአብሔር፡ንጉሣችን፡ ነው፤ርሱ፡ያድነናል።

23ገመዶችኽ፡ላልተዋል፥ደቀላቸውንም፡አላጸኑም፥ሸራውንም፡መዘርጋት፡አልቻሉም።በዚያም፡ጊዜ፡የብዙ፡ ምርኮ፡ብዝበዛ፡ተከፈለ፤ዐንካሳዎች፡እንኳ፡ብዝበዛውን፡በዘበዙ።

24በዚያም፡የሚቀመጥ፦ታምሜያለኹ፡አይልም፥በርሷም፡ለሚቀመጡ፡ሰዎች፡በደላቸው፡ይቅር፡ ይባልላቸዋል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source