1እናንተ፡አሕዛብ፡ሆይ፥ቅረቡ፥ስሙ፤እናንተ፡ወገኖች፡ሆይ፥አድምጡ፤ምድርና፡መላ፟ዋ፥ዓለምና፡ከርሷ፡ የሚወጣ፡ዅሉ፡ይስሙ።
2የእግዚአብሔር፡ቍጣ፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ላይ፡መዓቱም፡በሰራዊታቸው፡ዅሉ፡ላይ፡ነው፤ፈጽሞ፡ አጠፋቸው፥ለመታረድም፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።
3ከነርሱም፡የተገደሉት፡ይጣላሉ፥የሬሳቸውም፡ግማት፡ይሸታል፥ተራራዎችም፡ከደማቸው፡የተነሣ፡ይርሳሉ።
4የሰማይም፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ይበሰብሳሉ፥ሰማያትም፡እንደ፡መጽሐፍ፡ጥቅል፟፡ይጠቀለላሉ፥ከወይንና፡ ከበለስም፡ቅጠል፡እንደሚረግፍ፡ሰራዊታቸው፡ዅሉ፡ይረግፋል።
5ሰይፌ፡በሰማይ፡ኾና፡እስክትረካ፡ድረስ፡ጠጥታለች፤እንሆ፥በኤዶምያስና፡በረገምኹት፡ሕዝብ፡ላይ፡ ለፍርድ፡ትወርዳለች።
6እግዚአብሔር፡መሥዋዕት፡በባሶራ፥ታላቅም፡ዕርድ፡በኤዶምያስ፡ምድር፡አለውና፡የእግዚአብሔር፡ሰይፍ፡ በደም፡ተሞልታለች፥በስብም፥በበግ፡ጠቦትና፡በፍየል፡ደምም፥በአውራም፡በግ፡ኵላሊት፡ስብ፡ወፍራለች።
7ጐሽ፡ከነርሱ፡ጋራ፥ወይፈኖችም፡ከኰርማዎች፡ጋራ፡ይወድቃሉ፤ምድራቸውም፡በደም፡ ትረካለች፥ዐፈራቸውም፡በስብ፡ትወፍራለች።
8የእግዚአብሔር፡የበቀሉ፡ቀን፥ስለጽዮንም፡ክርክር፡የብድራት፡ዓመት፡ነው።
9የኤዶምያስም፡ፈሳሾች፡ዝፍት፡ኾነው፡ይለወጣሉ፥ዐፈሯም፡ዲን፡ይኾናል፥መሬቷም፡የሚቃጠል፡ዝፍት፡ ትኾናለች።
10በሌሊትና፡በቀንም፡አትጠፋም፥ጢሷም፡ለዘለዓለም፡ይወጣል፤ከትውልድ፡እስከ፡ትውልድም፡ድረስ፡ ባድማ፡ኾና፡ትኖራለች፤ለዘለዓለም፡ዓለም፡ማንም፡አያልፍባትም።
11ጭልፊትና፡ዣርት፡ግን፡ይወርሷታል፤ጕጕትና፡ቍራም፡ይኖሩባታል፤በላይዋም፡የመፍረስ፡ገመድና፡ የባዶነት፡ቱንቢ፡ይዘረጋባታል።
12መሳፍንቷን፡ወደ፡መንግሥት፡ይጠራሉ፥ነገር፡ግን፥ማንም፡አይገኝባትም፤አለቃዎቿም፡ዅሉ፡ምናምኖች፡ ይኾናሉ።
13በአዳራሾቿም፡ሾኽ፡በቅጥሮቿም፡ሳማን፡አሜከላ፡ይበቅሉባታል፤የቀበሮም፡ማደሪያና፡የሰጐን፡ስፍራ፡ ትኾናለች። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
14የምድረ፡በዳም፡አራዊት፡ከተኵላዎች፡ጋራ፡ይገናኛሉ፥አጋንንትም፡ርስ፡በርሳቸው፡ይጠራራሉ፤ጅን ም፡ በዚያ፡ትኖራለች፥ለርሷም፡ማረፊያ፡ታገኛለች።
15በዚያም፡ዋሊያ፡ቤቷን፡ትሠራለች፡ዕንቍላልም፡ትጥላለች፡ትቀፈቅፈውማለች፡ልጆቿንም፡በጥላዋ፡ ትሰበስባለች፤በዚያም፡ደግሞ፡አሞራዎች፡እያንዳንዳቸው፡ከባልንጀራዎቻቸው፡ጋራ፡ይሰበሰባሉ።
16በእግዚአብሔር፡መጽሐፍ፡ፈልጉ፥አንቡ፟ም፤አፌ፡አዟ፟ልና፥መንፈሱም፡ሰብስቧቸዋልና፥ከነዚህ፡አንዲት፡ አትጠፋም፥ባልንጀራውንም፡የሚያጣ፡የለም።
17ርሱም፡ዕጣ፡ጣለባቸው፥እጁም፡በገመድ፡ከፈለችላቸው፤ለዘለዓለም፡ይገዟታል፥ከትውልድም፡እስከ፡ ትውልድ፡ድረስ፡ይቀመጡባታል።