Skip to content
← Isaiah

Chapter 35 · Amharic

Isaiah

1ምድረ፡በዳውና፡ደረቁ፡ምድር፡ደስ፡ይላቸዋል፥በረሓውም፡ሐሤት፡ያደርጋል፡እንደ፡ጽጌ፡ረዳም፡ ያብባል።

2እጅግ፡ያብባል፡በደስታና፡በዝማሬ፡ሐሤትን፡ያደርጋል፤የሊባኖስ፡ክብር፥የቀርሜሎስና፡የሳሮን፡ግርማ፡ ይሰጠዋል፤የእግዚአብሔርንም፡ክብር፡የአምላካችንንም፡ግርማ፡ያያሉ።

3የደከሙትን፡እጆች፡አበርቱ፥የላሉትንም፡ጕልበቶች፡አጽኑ።

4ፈሪ፡ልብ፡ላላቸው፦እንሆ፥አምላካችኹ፡በበቀል፡በእግዚአብሔርም፡ብድራት፡ይመጣልና፥መጥቶም፡ ያድናችዃልና፥በርቱ፥አትፍሩ፡በሏቸው።

5በዚያን፡ጊዜም፡የዕውሮች፡ዐይን፡ይገለጣል፤የደንቈሮዎችም፡ዦሮ፡ይከፈታል።

6በዚያን፡ጊዜ፡ዐንካሳ፡እንደ፡ሚዳቋ፡ይዘላ፟ል፥የድዳም፡ምላስ፡ይዘምራል፤በምድረ፡በዳ፡ውሃ፥በበረሓም፡ ፈሳሽ፡ይፈልቃልና።

7ደረቂቱ፡ምድር፡ኵሬ፥የጥማት፡መሬት፡የውሃ፡ምንጭ፡ትኾናለች፤ቀበሮ፡የተኛበት፡መኖሪያ፡ልምላሜና፡ ሸምበቆ፡ደንገልም፡ይኾንበታል።

8በዚያም፡ጐዳናና፡መንገድ፡ይኾናል፡ርሱም፡የተቀደሰ፡መንገድ፡ይባላል፤ንጹሓንም፡ያልኾኑ፡ አያልፉበትም፥ለንጹሓን፡ግን፡ይኾናል፤ተላላፊዎችና፡ሰነፎች፡እንኳ፡አይስቱበትም።

9አንበሳም፡አይኖርበትም፥ነጣቂ፡አውሬም፡አይወጣበትም፥ከዚያም፡አይገኙም፤የዳኑት፡ግን፡በዚያ፡ ይኼዳሉ፤

10እግዚአብሔርም፡የተቤዣቸው፡ይመለሳሉ፡እየዘመሩም፡ወደ፡ጽዮን፡ይመጣሉ፤የዘለዓለም፡ደስታ፡ በራሳቸው፡ላይ፡ይኾናል፤ሐሤትንና፡ደስታን፡ያገኛሉ፥ሐዘንና፡ትካዜም፡ይሸሻሉ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source