1እንዲህም፡ኾነ፤በንጉሡ፡በሕዝቅያስ፡በዐሥራ፡አራተኛው፡ዓመት፡የአሶር፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ወደ፡ይሁዳ፡ ወደተመሸጉት፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወጥቶ፡ወሰዳቸው።
2የአሶርም፡ንጉሥ፡ራፋስቂስን፡ከብዙ፡ሰራዊት፡ጋራ፡ከለኪሶ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ላከ፥ርሱም፡በዐጣቢው፡ዕርሻ፡መንገድ፡ባለችው፡በላይኛዪቱ፡ኵሬ፡መስኖ፡አጠገብ፡ቆመ።
3የቤቱም፡አዛዥ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ጸሓፊውም፡ሳምናስ፡ታሪክ፡ጸሓፊም፡የአሣፍ፡ልጅ፡ዮአስ፡ ወደ፡ርሱ፡ወጡ። 260 ዕብ.፥ልይልይት፡(ሊሊት•የሌሊት፡ወፍ፥አለዚያም፡ጕጕት፤ግብረ፡አጋንንት፥ጥንቈላ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
4ራፋስቂስም፡አላቸው፦ለሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦ታላቁ፡የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ ይላል፦ይህ፡የምትታመንበት፡መተማመኛ፡ምንድር፡ነው፧
5እኔ፦ለሰልፍ፡የኾነው፡ምክርኽና፡ኀያልኽ፡ከንቱ፡ነገር፡ነው፡አልኹ፤አኹንም፡በእኔ፡ላይ፡ያመፅኸው፡ በማን፡ተማምነኽ፡ነው፧
6እንሆ፥በዚህ፡በተቀጠቀጠ፡በሸምበቆ፡በትር፡በግብጽ፡ትታመናለኽ፤ሰው፡ቢመረኰዘው፡ተሰብሮ፡በእጁ፡ ይገባል፥ያቈስለውማል፤የግብጽ፡ንጉሥ፡ፈርዖን፡ለሚታመኑበት፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ነው።
7አንተም፦በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡እንታመናለን፡ብትለኝ፥ሕዝቅያስ፡ይሁዳንና፡ኢየሩሳሌምን፦በዚህ፡ መሠዊያ፡ፊት፡ስገዱ፡ብሎ፡የኰረብታ፡መስገጃዎቹንና፡መሠዊያዎቹን፡ይስፈረሰ፡ይህ፡አይደለምን፧
8አኹን፡እንግዲህ፡ከጌታዬ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ጋራ፡ተወራረድ፥የሚቀመጡባቸውንም፡ሰዎች፡ማግኘት፡ ቢቻልኽ፡እኔ፡ኹለት፡ሺሕ፡ፈረሶች፡እሰጥኻለኹ።
9ስለ፡ሠረገላዎችና፡ስለ፡ፈረሰኛዎች፡በግብጽ፡ስትታመን፥ከጌታዬ፡ባሪያዎች፡የሚያንሰውን፡የአንዱን፡ አለቃ፡ፊት፡ትቃወም፡ዘንድ፡እንዴት፡ይቻልኻል፧
10አኹንም፡በእውኑ፡ያለእግዚአብሔር፡ትእዛዝ፡ይህን፡አገር፡አጠፋ፡ዘንድ፡ ወጥቻለኹን፧እግዚአብሔር፦ወደዚህ፡አገር፡ወጥተኽ፡አጥፋው፡አለኝ።
11ኤልያቄምና፡ሳምናስ፡ዮአስም፡ራፋስቂስን፦እኛ፡እንሰማለንና፡እባክኽ፥በሶርያ፡ቋንቋ፡ለባሪያዎችኽ፡ ተናገር፤በቅጥርም፡ላይ፡ባለው፡ሕዝብ፡ዦሮ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡አትናገረን፡አሉት።
12ራፋስቂስ፡ግን፦ጌታዬ፡ይህን፡ቃል፡እናገር፡ዘንድ፡ወዳንተና፡ወደ፡ጌታኽ፡ልኮኛልን፧ከእናንተ፡ጋራ፡ ኵሳቸውን፡ይበሉ፡ዘንድ፡ሽንታቸውንም፡ይጠጡ፡ዘንድ፡በቅጥር፡ላይ፡ወደተቀመጡት፡ሰዎች፡ አይደለምን፧አላቸው።
13ራፋስቂስም፡ቆሞ፡በታላቅ፡ድምፅ፡በአይሁድ፡ቋንቋ፡እንዲህ፡ብሎ፡ጮኸ።የታላቁን፡የአሶርን፡ንጉሥ፡ ቃል፡ስሙ።
14ንጉሡ፡እንዲህ፡ይላል፦ያድናችኹ፡ዘንድ፡አይችልምና፡ሕዝቅያስ፡አያታላ፟ችኹ፤
15ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር፡በርግጥ፡ያድነናል፡ይህችም፡ከተማ፡በአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አትሰጥም፡ብሎ፡ በእግዚአብሔር፡እንድትታመኑ፡አያድርጋችኹ።
16ሕዝቅያስንም፡አትስሙ፤የአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ከእኔ፡ጋራ፡ታረቁ፡ወደ፡እኔም፡ ውጡ፤እያንዳንዳችኹም፡ከወይናችኹና፡ከበለሳችኹ፡ብሉ፥ከጕድጓዳችኹም፡ውሃ፡ጠጡ፤
17ይህም፡መጥቼ፡ምድራችኹን፡ወደምትመስለው፡ምድር፥እኽልና፡የወይን፡ጠጅ፥እንጀራና፡ወይን፡ ወዳለበት፡ምድር፡እስካፈልሳችኹ፡ድረስ፡ነው።
18ሕዝቅያስም፦እግዚአብሔር፡ያድነናል፡ብሎ፡እንዳያታልላችኹ፡ተጠንቀቁ።በእውኑ፡የአሕዛብ፡አማልክት፡ አገሮቻቸውን፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡አድነዋቸዋልን፧
19የሐማትና፡የአርፋድ፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧የሴፈርዋይም፡አማልክት፡ወዴት፡አሉ፧ሰማርያን፡ከእጄ፡ አድነዋታልን፧
20እግዚአብሔር፡ኢየሩሳሌምን፡ከእጄ፡ያድን፡ዘንድ፡ከነዚህ፡አገሮች፡አማልክት፡ዅሉ፡አገሩን፡ከእጄ፡ ያዳነ፡ማን፡ነው፧
21እነርሱም፡ዝም፡አሉ፥አንዳችም፡አልመለሱለትም፤ንጉሡ፡እንዳይመልሱለት፡አዞ፟፡ነበርና።
22የቤቱ፡አዛዥ፡የኬልቅያስ፡ልጅ፡ኤልያቄም፡ጸሓፊውም፡ሳምናስ፡ታሪክ፡ጸሓፊም፡የአሣፍ፡ልጅ፡ዮአስ፡ ልብሳቸውን፡ቀደ፟ው፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጡ፥የራፋስቂስንም፡ቃል፡ነገሩት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org