1እንዲህም፡ኾነ፤ንጉሡ፡ሕዝቅያስ፡ይህን፡በሰማ፡ጊዜ፡ልብሱን፡ቀደደ፥ማቅም፡ለበሰ፥ወደእግዚአብሔርም፡ ቤት፡ገባ።
2የቤቱንም፡አዛዥ፡ኤልያቄምን፡ጸሓፊውንም፡ሳምናስን፡የካህናቱንም፡ሽማግሌዎች፡ማቅ፡ለብሰው፡ወደ፡ ነቢዩ፡ወደዓሞጽ፡ልጅ፡ወደ፡ኢሳይያስ፡ይኼዱ፡ዘንድ፡ላካቸው።
3እነርሱም፦ሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ቀን፡የመከራና፡የተግሣጽ፡የዘለፋም፡ቀን፡ነው፤ልጆች፡ የሚወለዱበት፡ጊዜ፡ደርሷል፡ለመውለድም፡ኀይል፡የለም።
4ምናልባት፡በሕያው፡አምላክ፡ላይ፡ይገዳደር፡ዘንድ፡ጌታው፡የአሶር፡ንጉሥ፡የላከውን፡የራፋስቂስን፡ቃል፡ አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ይሰማ፡እንደ፡ኾነ፥አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ስለሰማው፡ቃል፡ይገሥጸው፡እንደ፡ ኾነ፥ስለዚህ፡ለቀረው፡ቅሬታ፡ጸልይ፡አሉት።
5እንዲሁ፡የንጉሡ፡የሕዝቅያስ፡ባሪያዎች፡ወደ፡ኢሳይያስ፡መጡ።
6ኢሳይያስም፦ለጌታችኹ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአሶር፡ንጉሥ፡ባሪያዎች፡ስለ፡ ሰደቡኝ፥ስለሰማኸው፡ቃል፡አትፍራ።
7እንሆ፥በላዩ፡መንፈስን፡እሰዳ፟ለኹ፥ወሬንም፡ይሰማል፥ወደ፡ምድሩም፡ይመለሳል፤በምድሩም፡በሰይፍ፡ እንዲወድቅ፡አደርጋለኹ፡በሉት፡አላቸው።
8የአሶርም፡ንጉሥ፡ከለኪሶ፡እንደ፡ራቀ፡ሰምቶ፡ነበርና፥ራፋስቂስ፡ተመልሶ፡በልብና፡ሲዋጋ፡አገኘው።
9ርሱም፦የኢትዮጵያ፡ንጉሥ፡ቲርሐቅ፡ሊዋጋኽ፡መጥቷል፡የሚል፡ወሬ፡ሰማ።በሰማም፡ጊዜ፡ወደ፡ ሕዝቅያስ፡መልእክተኛዎችን፡ላከ፥
10እንዲህ፡ሲል፦ለይሁዳ፡ንጉሠ፡ለሕዝቅያስ፡እንዲህ፡ብላችኹ፡ንገሩት፦ኢየሩሳሌም፡በአሶር፡ንጉሥ፡ እጅ፡አትሰጥም፡ብሎ፡የምትታመንበት፡አምላክኽ፡አያታል፟ኽ።
11እንሆ፥የአሶር፡ነገሥታት፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ያደረጉትን፥እንዴትስ፡እንዳጠፏቸው፡ሰምተኻል፤አንተስ፡ ትድናለኽን፧
12አባቶቼ፡ያጠፏቸውን፡ጎዛንን፥ካራንን፥ራፊስን፥በተላሳር፡የነበሩትንም፡የዔዴንን፡ልጆች፡የአሕዛብ፡ አማልክት፡አዳኗቸውን፧
13የሐማት፡ንጉሥ፥የአርፋድ፡ንጉሥ፥የሴፈርዋይም፡ከተማ፡ንጉሥ፥የሄናና፡የዒዋ፡ንጉሥ፡ወዴት፡አሉ፧
14ሕዝቅያስም፡ደብዳቤውን፡ከመልእክተኛዎች፡እጅ፡ተቀብሎ፡አነበበው፤ሕዝቅያስም፡ወደእግዚአብሔር፡ ቤት፡ወጥቶ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዘረጋው።
15ሕዝቅያስም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ብሎ፡ጸለየ።
16አቤቱ፥በኪሩቤል፡ላይ፡የምትቀመጥ፡የእስራኤል፡አምላክ፡የሰራዊት፡ጌታ፡ሆይ፥አንተ፡ብቻኽን፡የምድር፡ መንግሥታት፡ዅሉ፡አምላክ፡ነኽ፤ሰማይንና፡ምድርን፡ፈጥረኻል።
17አቤቱ፥ዦሮኽን፡አዘንብልና፡ስማ፤አቤቱ፥ዐይንኽን፡ክፈትና፡እይ፤በሕያው፡አምላክ፡ላይ፡ይገዳደር፡ ዘንድ፡የላከውን፡የሰናክሬም፡ቃል፡ስማ።
18አቤቱ፥በእውነት፡የአሶር፡ነገሥታት፡ዓለሙን፡ዅሉ፡አገሮቻቸውንም፡አፍርሰዋል፥
19አማልክታቸውንም፡በእሳት፡ላይ፡ጥለዋል፤የዕንጨትና፡የድንጋይ፡የሰው፡እጅ፡ሥራ፡ነበሩ፡እንጂ፡ አማልክት፡አልነበሩምና፡ስለዚህ፡አጥፍተዋቸዋል።
20እንግዲህም፡አምላካችን፡አቤቱ፥የምድር፡መንግሥታት፡ዅሉ፡አንተ፡ብቻ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኾንኽ፡ ያውቁ፡ዘንድ፡ከእጁ፡አድነን። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
21የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡እንዲህ፡ብሎ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡ላከ፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ እንዲህ፡ይላል፦ስለአሶር፡ንጉሥ፡ስለ፡ሰናክሬም፡ወደ፡እኔ፡ለምነኻልና፥
22እግዚአብሔር፡ስለ፡ርሱ፡የተናገረው፡ቃል፡ይህ፡ነው፦ድንግሊቱ፡የጽዮን፡ልጅ፡ቀላል፡ አድርጋኻለች፥በንቀትም፡ሥቃብኻለች፤የኢየሩሳሌም፡ልጅ፡ራሷን፡ነቅንቃብኻለች።
23የተገዳደርኸው፡የሰደብኸውስ፡ማን፡ነው፧ቃልኽንስ፡ከፍ፡ከፍ፡ያደረግኽበት፡ዐይንኽንስ፡ወደ፡ላይ፡ ያነሣኽበት፡ማን፡ነው፧በእስራኤል፡ቅዱስ፡ላይ፡ነው።
24አንተም፦በሠረገላዬ፡ብዛት፡ወደተራራዎች፡ከፍታ፥ወደሊባኖስ፡ጥግ፡ላይ፡ወጥቻለኹ፤ረዣዥሞቹንም፡ ዝግባዎች፡የተመረጡትንም፡ጥዶች፡እቈርጣለኹ፥ወደከፍታውም፡ዳርቻ፡ወደቀርሜሎስ፡ዱር፡እገባለኹ።
25ቈፈርኹም፡ውሃም፡ጠጣኹ፡የግብጽንም፡ወንዞች፡ዅሉ፡በእግሬ፡ጫማ፡አደርቃለኹ፡ብለኽ፡ በባሪያዎችኽ፡እጅ፡በጌታ፡ላይ፡ተገዳደርኽ።
26እኔ፡ጥንቱን፡እንደ፡ሠራኹት፥ቀድሞውንም፡እንዳደረግኹት፡አልሰማኽምን፧አኹንም፡የተመሸጉትን፡ ከተማዎች፡የፍርስራሽ፡ክምር፡እስኪኾኑ፡ድረስ፡እንድታፈርስ፡አደረግኹኽ።
27ስለዚህ፥የሚኖሩባቸው፡ሰዎች፡እጃቸው፡ዝሏል፥ደንግጠውም፡ታውከዋል፤እንደ፡ምድረ፡በዳ፡ ሣር፥እንደ፡ለመለመም፡ቡቃያ፥በሰገነትም፡ላይ፡እንዳለ፡ሣር፥ሳይሸት፡ዋግ፡እንደ፡መታው፡እኽል፡ ኾነዋል።
28እኔ፡ግን፡መቀመጫኽንና፡መውጫኽን፡መግቢያኽንም፡በእኔም፡ላይ፡የተቈጣኸውን፡ቍጣ፡ ዐውቄያለኹ።
29ቍጣኽና፡ትዕቢትኽ፡ወደ፡ዦሮዬ፡ደርሷልና፥ስለዚህ፡ስናጋዬን፡በአፍንጫኽ፡ልጓሜንም፡በከንፈርኽ፡ አደርጋለኹ፥በመጣኽበትም፡መንገድ፡እመልስኻለኹ።
30ይህም፡ምልክት፡ይኾንኻል፤በዚህ፡ዓመት፡የገቦውን፥በኹለተኛውም፡ዓመት፡ከገቦው፡የበቀለውን፡ ትበላላችኹ፤በሦስተኛውም፡ዓመት፡ትዘራላችኹ፡ታጭዱማላችኹ፥ወይንም፡ትተክላላችኹ፡ፍሬውንም፡ ትበላላችኹ።
31ያመለጠው፡የይሁዳ፡ቤት፡ቅሬታ፡ሥሩን፡ወደ፡ታች፡ይሰዳ፟ል፥ወደ፡ላይም፡ያፈራል።
32ከኢየሩሳሌም፡ቅሬታ፡ከጽዮንም፡ተራራ፡ያመለጡት፡ይወጣሉና፤የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡ቅንአት፡ ይህን፡ያደርጋል።
33ስለዚህም፡እግዚአብሔር፡ስለአሶር፡ንጉሥ፡እንዲህ፡ይላል፦ወደዚች፡ከተማ፡አይመጣም፥ፍላጻንም፡ አይወረውርባትም፥በጋሻም፡አይመጣባትም፥የዐፈርንም፡ድልድል፡አይደለድልባትም።
34በመጣበት፡መንገድ፡በዚያው፡ይመለሳል፥ወደዚችም፡ከተማ፡አይመጣም፡ይላል፡እግዚአብሔር።
35ስለ፡እኔም፡ስለ፡ባሪያዬም፡ስለ፡ዳዊት፡ይህችን፡ከተማ፡አድናት፡ዘንድ፡እጋርዳታለኹ።
36የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ወጣ፥ከአሶራውያንም፡ሰፈር፡መቶ፡ሰማንያ፡ዐምስት፡ሺሕ፡ገደለ፤ማለዳም፡ በተነሡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ዅሉ፡በድኖች፡ነበሩ።
37የአሶርም፡ንጉሥ፡ሰናክሬም፡ተነሥቶ፡ኼደ፥ተመልሶም፡በነነዌ፡ተቀመጠ።
38በአምላኩም፡በናሳራክ፡ቤት፡ሲሰግድ፡ልጆቹ፡አድራሜሌክና፡ሳራሳር፡በሰይፍ፡ገደሉት፤ወደአራራትም፡ አገር፡ኰበለሉ።ልጁም፡አስራዶን፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።