Skip to content
← Isaiah

Chapter 38 · Amharic

Isaiah

1በዚያም፡ወራት፡ሕዝቅያስ፡ለሞት፡እስኪደርስ፡ታመመ።ነቢዩም፡የዓሞጽ፡ልጅ፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ርሱ፡ መጥቶ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ትሞታለኽ፡እንጂ፡በሕይወት፡አትኖርምና፡ቤትኽን፡አስተካክል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አለው።

2ሕዝቅያስም፡ፊቱን፡ወደ፡ግድግዳው፡መልሶ፡እንዲህ፡ሲል፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጸለየ፦

3አቤቱ፥በፊትኽ፡በእውነትና፡በፍጹም፡ልብ፡እንደ፡ኼድኹ፡ደስ፡የሚያሠኝኽንም፡እንዳደረግኹ፡ታስብ፡ ዘንድ፡እለምንኻለኹ።ሕዝቅያስም፡እጅግ፡አድርጎ፡አለቀሰ።

4የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡ኢሳይያስ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦

5ኺድ፥ሕዝቅያስን፡እንዲህ፡በለው፦የአባትኽ፡የዳዊት፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦ጸሎትኽን፡ሰምቻለኹ፥እንባኽንም፡አይቻለኹ፤እንሆ፥በዕድሜኽ፡ላይ፡ዐሥራ፡ዐምስት፡ዓመት፡ እጨምራለኹ።

6አንተንና፡ይህችንም፡ከተማ፡ከአሶር፡ንጉሥ፡እጅ፡እታደጋለኹ፥ይህችንም፡ከተማ፡እጋርዳታለኹ።

7እግዚአብሔርም፡የተገረውን፡ነገር፡እንዲፈጽመው፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምልክቱ፡ይህ፡ይኾንልኻል።

8እንሆ፥በአካዝ፡የጥላ፡ስፍረ፡ሰዓት፡ላይ፡ከፀሓይ፡ጋራ፡የወረደውን፡በደረጃዎች፡ያለውን፡ጥላ፡ዐሥር፡ ደረጃ፡ወደ፡ዃላ፡እንዲመለስ፡አደርጋለኹ።ፀሓይም፡በጥላ፡ስፍረ፡ሰዓት፡ላይ፡የወረደበት፡ዐሥር፡ደረጃ፡ ወደ፡ዃላ፡ተመለሰ።

9የይሁዳ፡ንጉሥ፡ሕዝቅያስ፡ታሞ፟፡ከደዌው፡በተፈወሰ፡ጊዜ፡የጻፈው፡ጽሕፈት፡ይህ፡ነው፦

10እኔ፦በሕይወት፡ዘመኔ፡መካከል፡ወደሲኦል፡በሮች፡እገባለኹ፤የቀረው፡ዘመኔ፡ጐደለብኝ፡አልኹ።

11ደግሞም፦በሕያዋን፡ምድር፡እግዚአብሔርን፡አላይም፤በዓለምም፡ከሚኖሩ፡ጋራ፡ሰውን፡እንግዲህ፡ አልመለከትም፡አልኹ።

12ማደሪያዬ፡ተነቀለች፥እንደ፡እረኛ፡ድንኳንም፡ከእኔ፡ዘንድ፡ተወገደች፤ሕይወቴንም፡እንደ፡ሸማኔ፡ ጠቀለልኹ፥ርሱም፡ከመጠቅለያው፡ይቈርጠኛል፤ከማለዳም፡ዠምሮ፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡ታጠፋኛለኽ።

13እስኪነጋ፡ድረስ፡ቈይቼ፡ነበር፤ርሱ፡እንደ፡አንበሳ፡ዐጥንቴን፡ዅሉ፡ሰበረ፤ከማለዳ፡ዠምሮ፡እስከ፡ማታ፡ ድረስ፡ታጠፋኛለኽ።

14እንደ፡ጨረባና፡እንደ፡ሽመላ፡ተንጫጫኹ፥እንደ፡ርግብም፡አጕረመረምኹ፤ዐይኖቼ፡ወደ፡ላይ፡ ከማየት፡ደከሙ፦ጌታ፡ሆይ፥ተጨንቄያለኹና፡መከታ፡ኹነኝ።

15ምን፡እላለኹ፧ርሱ፡ተናግሮኛል፥ርሱ፡ራሱም፡ይህን፡አድርጓል፤በዘመኔ፡ዅሉ፡ስለነፍሴ፡ምሬት፡ቀስ፡ ብዬ፡እኼዳለኹ።

16ጌታ፡ሆይ፥በዚህ፡ነገር፡ሰዎች፡በሕይወት፡ይኖራሉ፥በዚህም፡ዅሉ፡የመንፈሴ፡ሕይወት፡ነው፤አንተም፡ ፈወስኸኝ፡ወደ፡ሕይወትም፡መለስኸኝ።

17እንሆ፥ታላቅ፡ምሬት፡ለደኅንነቴ፡ኾነ፤አንተም፡ነፍሴን፡ከጥፋት፡ጕድጓድ፡አዳንኻት፥ኀጢአቴንም፡ ዅሉ፡ወደ፡ዃላኽ፡ጣልኽ።

18ሲኦል፡አያመሰግንኽምና፥ሞትም፡አያከብርኽምና፤ወደ፡ጕድጓዱ፡የሚወርዱ፡እውነትኽን፡ተስፋ፡ አያደርጉም።

19እኔ፡ዛሬ፡እንደማደርግ፡ሕያዋን፡እነርሱ፡ያመሰግኑኻል፤አባት፡ለልጆች፡እውነትኽን፡ያስታውቃል።

20እግዚአብሔር፡ያድነኛል፤ስለዚህ፥በዕድሜያችን፡ዘመን፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡ቅኔዎችን፡አውታር፡ ባለው፡ዕቃ፡እንዘምራለን።

21ኢሳይያስም፦የበለስ፡ጥፍጥፍ፡አምጥተው፡በዕባጩ፡ላይ፡ይለብጡት፥ርሱም፡ይፈወሳል፡ብሎ፡ነበር።

22ሕዝቅያስም፦ወደእግዚአብሔር፡ቤት፡እወጣ፡ዘንድ፡ምልክቱ፡ምንድር፡ነው፧ብሎ፡ነበር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source