1በዚያም፡ወራት፡የባቢሎን፡ንጉሥ፡የባልዳን፡ልጅ፡መሮዳክ፡ባልዳን፡ሕዝቅያስ፡ታሞ፟፡እንደ፡ተፈወሰ፡ ሰምቶ፡ነበርና፥ደብዳቤና፡እጅ፡መንሻ፡ላከለት።
2ሕዝቅያስም፡ደስ፡አለው፥ግምጃ፡ቤቱንም፥ብሩንና፡ወርቁንም፥ቅመሙንና፡የከበረውንም፡ ዘይት፥መሣሪያም፡ያለበትን፡ቤት፡ዅሉ፥በቤተ፡መዛግብቱም፡የተገኘውን፡ዅሉ፡አሳያቸው፤በቤቱና፡በግዛቱ፡ ዅሉ፡ካለው፡ሕዝቅያስ፡ያላሳያቸው፡የለም።
3ነቢዩም፡ኢሳይያስ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ሕዝቅያስ፡መጥቶ፦እነዚህ፡ሰዎች፡ምን፡አሉ፧ከወዴትስ፡ መጡልኽ፧አለው።ሕዝቅያስም፦ከሩቅ፡አገር፡ከባቢሎን፡መጡልኝ፡አለው።
4ርሱም፦በቤትኽ፡ያዩት፡ምንድር፡ነው፧አለው፤ሕዝቅያስም፦በቤቴ፡ያለውን፡ዅሉ፡አይተዋል፤በቤተ፡ መዛግብቴ፡ካለው፡ያላሳየዃቸው፡የለም፡አለው።
5ኢሳይያስም፡ሕዝቅያስን፦የሰራዊትን፡ጌታ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስማ።
6እንሆ፥በቤትኽ፡ያለው፡ዅሉ፥አባቶችኽም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያከማቹት፡ዅሉ፡ወደ፡ባቢሎን፡ የሚፈልስበት፡ወራት፡ይመጣል፤ምንም፡አይቀርም፥ይላል፡እግዚአብሔር።
7ከአንተም፡ከሚወጡት፡ከምትወልዳቸው፡ልጆችኽ፡ማርከው፡ይወስዳሉ፤በባቢሎንም፡ንጉሥ፡ቤት፡ውስጥ፡ ጃን፡ደረባዎች፡ይኾናሉ፡አለው።
8ሕዝቅያስም፡ኢሳይያስን፦የተናገርኸው፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡መልካም፡ነው፡አለው።ደግሞም፦በዘመኔ፡ ሰላምና፡እውነት፡ይኹን፡አለ።