Skip to content
← Isaiah

Chapter 40 · Amharic

Isaiah

1አጽናኑ፥ሕዝቤን፡አጽናኑ፡ይላል፡አምላካችኹ።

2ለኢየሩሳሌም፡ልብ፡ተናገሩ፡የተቀጠረችበት፡ወራት፡እንደ፡ተፈጸመ፥ኀጢአቷም፡እንደ፡ ተሰረየ፥ከእግዚአብሔርም፡እጅ፡ስለ፡ኀጢአቷ፡ዅሉ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡እንደ፡ተቀበለች፡ወደ፡ርሷ፡ጩኹ።

3የዐዋጅ፡ነጋሪ፡ቃል።የእግዚአብሔርን፡መንገድ፡በምድረ፡በዳ፡ጥረጉ፥ለአምላካችንም፡ጐዳና፡በበረሓ፡ አስተካከሉ።

4ሸለቆው፡ዅሉ፡ከፍ፡ይላል፥ተራራውና፡ኰረብታውም፡ዅሉ፡ዝቅ፡ይላል፤ጠማማውም፡ ይቃናል፥ስርጓጕጡም፡ሜዳ፡ይኾናል፤

5የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ይገለጣል፥ሥጋ፡ለባሹም፡ዅሉ፡በአንድነት፡ያየዋል፥የእግዚአብሔር፡አፍ፡ ይህን፡ተናግሯልና።

6ጩኽ፡የሚል፡ሰው፡ቃል፤ምን፡ብዬ፡ልጩኽ፧አልኹ።ሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ሣር፡ነው፥ክብሩም፡ዅሉ፡ እንደ፡ምድረ፡በዳ፡አበባ፡ነው።

7የእግዚአብሔር፡እስትንፋስ፡ይነፍስበታልና፥ሣሩ፡ይደርቃል፡አበባውም፡ይረግፋል፤በእውነት፡ሕዝቡ፡ሣር፡ ነው።

8ሣሩ፡ይደርቃል፡አበባውም፡ይረግፋል፥የአምላካችን፡ቃል፡ግን፡ለዘለዓለም፡ጸንታ፡ትኖራለች።

9የምሥራች፡የምትነግሪ፡ጽዮን፡ሆይ፥ከፍ፡ወዳለው፡ተራራ፡ውጪ፡የምሥራች፡የምትነግሪ፡ኢየሩሳሌም፡ ሆይ፥ድምፅሽን፡በኀይል፡አንሺ፤አንሺ፥አትፍሪ፤ለይሁዳም፡ከተማዎች፦እንሆ፥አምላካችኹ! ብለሽ፡ንገሪ።

10እንሆ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ኀያል፡ይመጣል፡ክንዱም፡ስለ፡ርሱ፡ይገዛል፤እንሆ፥ዋጋው፡ከርሱ፡ ጋራ፡ደመ፡ወዙም፡በፊቱ፡ነው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11መንጋውን፡እንደ፡እረኛ፡ያሰማራል፥ጠቦቶቹን፡በክንዱ፡ሰብስቦ፡በብብቱ፡ይሸከማል፥የሚያጠቡትንም፡ በቀስታ፡ይመራል።

12ውሃዎችን፡በዕፍኙ፡የሰፈረ፥ሰማይንም፡በስንዝር፡የለካ፥የምድርንም፡ዐፈር፡በመስፈሪያ፡ሰብስቦ፡ የያዘ፥ተራራዎችን፡በሚዛን፡ኰረብታዎችንም፡በሚዛኖች፡የመዘነ፡ማን፡ነው፧

13የእግዚአብሔርን፡መንፈስ፡ያዘዘ፥ወይስ፡አማካሪ፡ኾኖ፡ያስተማረው፡ማን፡ነው፧

14ወይስ፡ከማን፡ጋራ፡ተመካከረ፧ወይስ፡ማን፡መከረው፧የፍርድንም፡መንገድ፡ማን፡ አስተማረው፧ዕውቀትንስ፡ማን፡አስተማረው፧የማስተዋልንስ፡መንገድ፡ማን፡አሳየው፧

15እንሆ፥አሕዛብ፡በገንቦ፡እንዳለች፡ጠብታ፡ናቸው፥በሚዛንም፡እንዳለ፡ትንሽ፡ትቢያ፡ ተቈጥረዋል፤እንሆ፥ደሴቶችን፡እንደ፡ቀላል፡ነገር፡ያነሣል።

16ሊባኖስ፡ለማንደጃ፡እንስሳዎቿም፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አይበቁም።

17አሕዛብ፡ዅሉ፡በፊቱ፡እንዳልነበሩ፡ናቸው፤ከምናምን፡እንደሚያንሱ፥እንደ፡ከንቱ፡ነገርም፡ይቈጥራቸዋል።

18እንግዲህ፡እግዚአብሔርን፡በማን፡ትመስሉታላችኹ፧ወይስ፡በምን፡ምሳሌ፡ታስተያዩታላችኹ፧

19የተቀረጸውንስ፡ምስል፡ሠራተኛ፡ሠርቶታል፥አንጥረኛም፡በወርቅ፡ለብጦታል፥የብሩንም፡ሰንሰለት፡ አፍሶ፟ለታል።

20ለዚህ፡መባዕ፡ገንዘቡ፡ያልበቃው፡ድኻ፡የማይነቅዘውን፡ዕንጨት፡ይመርጣል፤ምስሉም፡እንዳይናወጥ፡ ያቆመው፡ዘንድ፡ብልኅ፡ሠራተኛን፡ይፈልጋል።

21አላወቃችኹምን፧ወይስ፡አልሰማችኹምን፧ከጥንትስ፡አልተወራላችኹምን፧ወይስ፡ምድር፡ከተመሠረተች፡ ዠምሮ፡አላስተዋላችኹምን፧

22ርሱ፡በምድር፡ክበብ፡ላይ፡ይቀምጣል፥በርሷም፡የሚኖሩት፡እንደ፡አንበጣ፡ናቸው፤ሰማያትን፡እንደ፡ መጋረጃ፡የሚዘረጋቸው፡እንደ፡ድንኳንም፡ለመኖሪያ፡የሚዘረጋቸው፥

23አለቃዎችንም፡እንዳልነበሩ፥የምድርንም፡ፈራጆች፡እንደ፡ከንቱ፡ነገር፡የሚያደርጋቸው፡ርሱ፡ነው።

24ገና፡እንደ፡ተተከሉና፡እንደ፡ተዘሩ፥በምድርም፡ሥር፡ገና፡እንደ፡ሰደዱ፡ወዲያውኑ፡ ነፈሰባቸው፥እነርሱም፡ደረቁ፥ዐውሎ፡ነፋስም፡እንደ፡እብቅ፡ጠረጋቸው።

25እንግዲህ፡እተካከለው፡ዘንድ፡በማን፡መሰላችኹኝ፧ይላል፡ቅዱሱ።

26ዐይናችኹን፡ወደ፡ላይ፡አንሥታችኹ፡ተመልከቱ፤እነዚህን፡የፈጠረ፡ማን፡ነው፧ሰራዊታቸውን፡በቍጥር፡ የሚያወጣ፡ርሱ፡ነው፥ዅሉንም፡በየስማቸው፡ይጠራቸዋል፤በኀይሉ፡ብዛትና፡በችሎቱ፡ብርታት፡አንድስ፡ እንኳ፡አይታጣውም።

27ያዕቆብ፡ሆይ፥እስራኤልም፡ሆይ፦መንገዴ፡ከእግዚአብሔር፡ተሰውራለች፡ፍርዴም፡ከአምላኬ፡ዐልፋለች፡ ለምን፡ትላለኽ፧ለምንስ፡እንዲህ፡ትናገራለኽ፧

28አላወቅኽምን፧አልሰማኽምን፧እግዚአብሔር፡የዘለዓለም፡አምላክ፥የምድርም፡ዳርቻ፡ፈጣሪ፡ ነው፤አይደክምም፥አይታክትም፥ማስተዋሉም፡አይመረመርም።

29ለደካማ፡ኀይልን፡ይሰጣል፥ጕልበት፡ለሌለውም፡ብርታትን፡ይጨምራል።

30ብላቴናዎች፡ይደክማሉ፡ይታክቱማል፥ጐበዛዝቱም፡ፈጽሞ፡ይወድቃሉ፤

31እግዚአብሔርን፡በመተማመን፡የሚጠባበቁ፡ግን፡ኀይላቸውን፡ያድሳሉ፤እንደ፡ንስር፡በክንፍ፡ ይወጣሉ፤ይሮጣሉ፥አይታክቱም፤ይኼዳሉ፥አይደክሙም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source