1ደሴቶች፡ሆይ፥በፊቴ፡ዝም፡በሉ፤አሕዛብም፡ኀይላቸውን፡ያድሱ፤ይቅረቡም፡በዚያን፡ጊዜም፡ ይናገሩ፤ለፍርድ፡ለአንድነት፡እንቅረብ።
2ከምሥራቅ፡አንዱን፡ያስነሣ፡በጽድቅም፡ወደ፡እግሩ፡የተጠራው፡ማን፡ነው፧አሕዛብንም፡አሳልፎ፡በፊቱ፡ ሰጠው፥ነገሥታትንም፡አስገዛለት፤ለሰይፉ፡እንደ፡ትቢያ፡ለቀስቱም፡እንደ፡ተጠረገ፡እብቅ፡አድርጎ፡ሰጣቸው።
3አሳደዳቸው፥እግሮቹም፡አስቀድመው፡ባልኼዱባት፡መንገድ፡በደኅንነት፡ዐለፈ።
4ይህን፡የሠራና፡ያደረገ፥ትውልድንም፡ከጥንት፡የጠራ፡ማን፡ነው፧እኔ፡እግዚአብሔር፥ፊተኛው፡ በዃለኛዎችም፡ዘንድ፡የምኖር፡እኔ፡ነኝ።
5ደሴቶች፡አይተው፡ፈሩ፥የምድርም፡ዳርቻዎች፡ተንቀጠቀጡ፤ቀረቡም፡ደረሱም።
6ዅሉም፡እያንዳንዱ፡ባልንጀራውን፡ይረዳው፡ነበር፥ወንድሙንም፦አይዞኽ፡ይለው፡ነበር።
7ዐናጢውም፡አንጥረኛውን፥በመዶሻም፡የሚያሣሣውን፡መስፍ፡መችውን፡አጽናና፥ስለማጣበቅ፡ ሥራውም፦መልካም፡ነው፡አለ፤እንዳይንቀሳቀስም፡በችንካር፡አጋጠመው።
8ባሪያዬ፡እስራኤል፥የመረጥኹኽ፡ያዕቆብ፥የወዳጄ፡የአብርሃም፡ዘር፡ሆይ፥
9አንተ፡ከምድር፡ዳርቻ፡የያዝኹኽ፡ከማእዘኗም፡የጠራኹኽና፦አንተ፡ባሪያዬ፡ነኽ፥መርጬኻለኹ፡ አልጥልኽም፡ያልኹኽ፡ሆይ፥
10እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡አትፍራ፤እኔ፡አምላክኽ፡ነኝና፡ አትደንግጥ፤አበረታኻለኹ፥እረዳኽማለኹ፥በጽድቄም፡ቀኝ፡ደግፌ፡እይዝኻለኹ።
11እንሆ፥የሚቈጡኽ፡ዅሉ፡ያፍራሉ፥ይዋረዱማል፤የሚከራከሩኽም፡እንዳልነበሩ፡ይኾናሉ፥ይጠፉማል።
12የሚያጣሉኽንም፡ትሻቸዋለኽ፡አታገኛቸውምም፥የሚዋጉኽም፡እንዳልነበሩና፡እንደ፡ምናምን፡ይኾናሉ።
13እኔ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፦አትፍራ፥እረዳኻለኹ፡ብዬ፡ቀኝኽን፡እይዛለኹና።
14አንተ፡ትል፡ያዕቆብ፡የእስራኤልም፡ሰዎች፡ሆይ፥አትፍሩ፤እረዳኻለኹ፥ይላል፡ እግዚአብሔር፥የሚቤዥኽም፡የእስራኤል፡ቅዱስ፡ነው።
15እንሆ፥እንደ፡ተሳለች፡እንደ፡ዐዲስ፡ባለጥርስ፡ማኼጃ፡አድርጌኻለኹ፤ተራራዎችንም፡ታኼዳለኽ፡ ታደቃ፟ቸውማለኽ፥ኰረብታዎችንም፡እንደ፡ገለባ፡ታደርጋቸዋለኽ።
16ታበጥራቸዋለኽ፥ነፋስም፡ይጠርጋቸዋል፥ዐውሎ፡ነፋስም፡ይበትናቸዋል፤አንተም፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ ይልኻል፥በእስራኤልም፡ቅዱስ፡ትመካለኽ።
17ድኻዎችና፡ምስኪኖችም፡ውሃ፡ይሻሉ፡አያገኙምም፥ምላሳቸውም፡በጥማት፡ደርቋል፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ እሰማቸዋለኹ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እኔ፡አልተዋቸውም።
18በወናዎቹ፡ኰረብታዎች፡ላይ፡ወንዞችን፥በሸለቆዎችም፡መካከል፡ምንጮችን፡እከፍታለኹ፤ምድረ፡ በዳውን፡ለውሃ፡መቆሚያ፥የጥማትንም፡ምድር፡ለውሃ፡መፍለቂያ፡አደርጋለኹ።
20የእግዚአብሔር፡እጅ፡ይህን፡እንደ፡ሠራች፥የእስራኤልም፡ቅዱስ፡እንደ፡ፈጠረው፡ያዩ፡ዘንድ፡ ያውቁም፡ዘንድ፡ያስቡም፡ዘንድ፡በአንድነትም፡ያስተውሉ፡ዘንድ፥በምድረ፡በዳ፡ዝግባውንና፡ግራሩን፡ ባርሰነቱንና፡የዘይቱን፡ዛፍ፡አበቅላለኹ፥በበረሓውም፡ጥዱንና፡አስታውን፡ወይራውንም፡በአንድነት፡አኖራለኹ።
21ክርክራችኹን፡አቅርቡ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ማስረጃችኹን፡አምጡ፥ይላል፡የያዕቆብ፡ንጉሥ።
22ያምጡ፥የሚኾነውንም፡ይንገሩን፤ልብም፡እናደርግ፡ዘንድ፡ፍጻሜያቸውንም፡እናውቅ፡ዘንድ፥የቀደሙት፡ ነገሮች፡ምን፡እንደ፡ኾኑ፡ተናገሩ፥የሚመጡትንም፡አሳዩን።
23አማልክትም፡መኾናችኹን፡እናውቅ፡ዘንድ፡በዃላ፡የሚመጡትን፡ተናገሩ፤እንደነግጥም፡ዘንድ፡ በአንድነትም፡እናይ፡ዘንድ፡መልካሙን፡ወይም፡ክፉውን፡አድርጉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
24እንሆ፥እንዳልነበረ፡ናችኹ፥ሥራችኹም፡ከንቱ፡ነው፤የሚመርጣችኹም፡አስጸያፊ፡ነው።
25አንዱን፡ከሰሜን፡አነሣኹ፡መጥቷልም፤አንዱም፡ከፀሓይ፡መውጫ፡ስሜን፡የሚጠራ፡ይመጣል፤በጭቃ፡ ላይ፡እንደሚመጣ፡ሰው፡ዐፈርም፡እንደሚረግጥ፡ሸክለኛ፡በአለቃዎች፡ላይ፡ይመጣል።
26እናውቅ፡ዘንድ፡ከጥንት፡የተናገረው፦እውነት፡ነው፡እንልም፡ዘንድ፡ቀድሞ፡የተናገረው፡ማን፡ ነው፧የሚናገር፡የለም፥የሚገልጥም፡የለም፥ቃላችኹንም፡የሚሰማ፡የለም።
27በመዠመሪያ፡ለጽዮን፦እንሇቸው፡እላለኹ፤ለኢየሩሳሌምም፡የምሥራች፡ነጋሪን፡እሰጣለኹ።
28ብመለከት፡ማንም፡አልነበረም፤ብጠይቃቸውም፡የሚመልስልኝ፡አማካሪ፡በመካከላቸው፡የለም።
29እንሆ፥እነርሱ፡ዅሉ፡ከንቱዎች፡ናቸው፥ሥራቸውም፡ምንም፡ምን፡ናት፤ቀልጠው፡የተሠሩት፡ ምስሎቻቸውም፡ነፋስና፡ኢምንት፡ናቸው።