1አኹንም፡ያዕቆብ፡ሆይ፥የፈጠረኽ፥እስራኤልም፡ሆይ፥የሠራኽ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ ይላል፦ተቤዥቼኻለኹና፡አትፍራ፤በስምኽም፡ጠርቼኻለኹ፥አንተ፡የእኔ፡ነኽ።
2በውሃ፡ውስጥ፡ባለፍኽ፡ጊዜ፡ከአንተ፡ጋራ፡እኾናለኹ፥በወንዞችም፡ውስጥ፡ባለፍኽ፡ጊዜ፡ አያሰጥሙኽም፤በእሳትም፡ውስጥ፡በኼድኽ፡ጊዜ፡አትቃጠልም፥ነበልባሉም፡አይፈጅኽም።
3እኔ፡የእስራኤል፡ቅዱስ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡መድኀኒትኽ፡ነኝ፤ግብጽን፡ለአንተ፡ቤዛ፡ አድርጌ፥ኢትዮጵያንና፡ሳባንም፡ለአንተ፡ፋንታ፡ሰጥቻለኹ።
4በዐይኔ፡ፊት፡የከበርኽና፡የተመሰገንኽ፡ነኽና፥እኔም፡ወድጄኻለኹና፡ስለዚህ፡ሰዎችን፡ለአንተ፡አሕዛብንም፡ ለነፍስኽ፡እሰጣለኹ።
5እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነኝና፡አትፍራ፤ዘርኽንም፡ከምሥራቅ፡አመጣዋለኹ፥ከምዕራብም፡እሰበስብኻለኹ።
7ሰሜንን፦መልሰኽ፡አምጣ፥ደቡብንም፦አትከልክል፤ወንዶች፡ልጆቼን፡ከሩቅ፡ሴቶች፡ልጆቼንም፡ ከምድር፡ዳርቻ፥በስሜ፡የተጠራውን፡ለክብሬም፡የፈጠርኹትን፥የሠራኹትንና፡ያደረግኹትን፡ዅሉ፡አምጣ፡ እለዋለኹ።
8ዐይኖች፡ያሏቸውን፡ዕውሮችን፡ሕዝብ፥ዦሮዎችም፡ያሏቸውን፡ደንቈሮዎቹን፡አውጣ።
9አሕዛብ፡ዅሉ፡በአንድነት፡ይሰብሰቡ፡ወገኖችም፡ይከማቹ፤ከመካከላቸው፤ይህን፡የሚናገር፥የቀድሞውንስ፡ ነገር፡የሚያሳየን፡ማን፡ነው፧ይጸድቁ፡ዘንድ፡ምስክሮቻቸውን፡ያምጡ፥ሰምተውም፡እውነት፡ነው፡ይበሉ።
10ታውቁና፡ታምኑብኝ፡ዘንድ፡እኔም፡እንደኾንኹ፡ታስተውሉ፡ዘንድ፥እናንተ፡የመረጥኹትም፡ባሪያዬ፡ ምስክሮቼ፡ናችኹ፡ይላል፡እግዚአብሔር፤ከእኔ፡በፊት፡አምላክ፡አልተሠራም፡ከእኔም፡በዃላ፡አይኾንም።
11እኔ፥እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፥ከእኔ፡ሌላም፡የሚያድን፡የለም።
12ተናግሬያለኹ፡አድኜማለኹ፡አሳይቼማለኹ፥በእናንተም፡ዘንድ፡ባዕድ፡አምላክ፡ አልነበረም፤ስለዚህ፥እናንተ፡ምስክሮቼ፡ናችኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥እኔም፡አምላክ፡ነኝ።
13ከጥንት፡ዠምሮ፡እኔ፡ነኝ፡ከእጄም፡የሚያመልጥ፡የለም፤እሠራለኹ፥የሚከለክልስ፡ማን፡ነው፧ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
14የእስራኤል፡ቅዱስ፥የሚቤዣችኹ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለ፡እናንተ፡ወደ፡ባቢሎን፡ ሰድጃለኹ፥ከለዳውያንንም፡ዅሉ፡ስደተኛዎች፡አድርጌ፡በሚመኩባቸው፡መርከቦች፡አዋርዳቸዋለኹ።
15ቅዱሳችኹ፥የእስራኤል፡ፈጣሪ፥ንጉሣችኹ፥እግዚአብሔር፡እኔ፡ነኝ።
16እግዚአብሔር፡በባሕር፡ውስጥ፡መንገድን፡በኀይለኛም፡ውሃ፡ውስጥ፡መተላለፊያን፡ያደርጋል፤
17እግዚአብሔር፡ሠረገላውንና፡ፈረሱን፡ሰራዊቱንና፡ዐርበኛውን፡ያወጣል፤እነርሱ፡ግን፡በአንድነት፡ ተኝተዋል፥አይነሡም፤ቀርተዋል፥እንደ፡ጧፍ፡ኵስታሪም፡ጠፍተዋል፤እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦
18የፊተኛውን፡ነገር፡አታስተውሉ፥የጥንቱንም፡ነገር፡አታስቡ።
19እንሆ፥ዐዲስ፡ነገርን፡አደርጋለኹ፤ርሱም፡አኹን፡ይበቅላል፥እናንተም፡አታውቁትምን፧በምድረ፡በዳም፡ መንገድን፥በበረሓም፡ወንዞችን፡አደርጋለኹ።
21ምስጋናዬን፡እንዲናገሩ፡ለእኔ፡የፈጠርኹት፡ሕዝብ፥የመረጥኹትን፡ሕዝቤን፡አጠጣ፡ ዘንድ፥በምድረ፡በዳ፡ውሃን፡በበረሓም፡ወንዞችን፡ሰጥቻለኹና፥የምድረ፡በዳ፡አራዊት፥ቀበሮዎችና፡ ሰጐኖች፥ያከብሩኛል።
22ያዕቆብ፡ሆይ፥አንተ፡ግን፡አልጠራኸኝም፥አንተም፡እስራኤል፡ሆይ፥በእኔ፡ዘንድ፡ደክመኻል።
23ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡በጎችኽን፡አላቀረብኽልኝም፡በሌላም፡መሥዋዕትኽ፡አላከበርኸኝም፤በእኽልም፡ ቍርባን፡አላስቸገርኹኽም፡በዕጣንም፡አላደከምኹኽም።
24ዕጣንም፡በገንዘብ፡አልገዛኽልኝም፡በመሥዋዕትኽም፡ስብ፡አላጠገብኸኝም፤ነገር፡ግን፥በኀጢአትኽ፡ አስቸገርኸኝ፥በበደልኽም፡አደከምኸኝ።
25መተላለፍኽን፦ስለ፡እኔ፡ስል፡የምደመስስ፡እኔ፡ነኝ፤ኀጢአትኽንም፡አላስብም።
26አሳስበኝ፥በአንድነትም፡ኾነን፡እንፋረድ፤እንድትጸድቅ፡ነገርኽን፡ተናገር።
27ፊተኛው፡አባትኽ፡ኀጢአት፡ሠርቷል፥መምህሮችኽም፡በድለውኛል።
28ስለዚህ፥የመቅደሱን፡አለቃዎች፡አረከስኹ፥ያዕቆብንም፡ርግማን፥እስራኤልንም፡ስድብ፡አደረግኹ።