1እግዚአብሔር፡ለቀባኹት፥አሕዛብንም፡በፊቱ፡አስገዛ፡ዘንድ፡የነገሥታትንም፡ወገብ፡እፈታ፡ ዘንድ፥በሮቹም፡እንዳይዘጉ፡መዝጊያዎቹን፡በፊቱ፡እከፍት፡ዘንድ፥ቀኝ፡እጁን፡ለያዝኹት፡ለቂሮስ፡እንዲህ፡ ይላል፦
2በፊትኽ፡እኼዳለኹ፡ተራራዎችንም፡ትክክል፡አደርጋለኹ፥የናሱንም፡ደጆች፡እሰብራለኹ፡የብረቱንም፡ መወርወሪያዎች፡እቈርጣለኹ፤
3በስምኽም፡የምጠራኽ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እኔ፡እንደ፡ኾንኹ፡ታውቅ፡ዘንድ፡በጨለማ፡ የነበረችውን፡መዝገብ፡በስውርም፡የተደበቀችውን፡ሀብት፡እሰጥኻለኹ።
4ስለ፡ባሪያዬ፡ስለ፡ያዕቆብ፥ስለ፡መረጥኹትም፡ስለ፡እስራኤል፡ብዬ፡በስምኽ፡ጠርቼኻለኹ፤በቍልምጫ፡ ስምኽ፡ጠራኹኽ፥አንተ፡ግን፡አላወቅኸኝም።
6እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፡ከእኔም፡ሌላ፡ማንም፡የለም፤ከእኔም፡በቀር፡አምላክ፡የለም፤በፀሓይ፡ መውጫና፡በምዕራብ፡ያሉ፡ከእኔ፡በቀር፡ማንም፡ሌላ፡እንደሌለ፡ያውቁ፡ዘንድ፡አስታጠቅኹኽ፥አንተ፡ግን፡ አላወቅኸኝም፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፥ከእኔም፡ሌላ፡ማንም፡የለም።
7ብርሃንን፡ሠራኹ፥ጨለማውንም፡ፈጠርኹ፤ደኅንነትን፡እሠራለኹ፥ክፋትንም፡እፈጥራለኹ፤እነዚህን፡ዅሉ፡ ያደረግኹ፡እግዚአብሔር፡እኔ፡ነኝ።
8እናንተ፡ሰማያት፡ከላይ፡አንጠባጥቡ፥ደመናትም፡ጽድቅን፡ያዝንቡ፤ምድርም፡ትከፈት፥መድኀኒትንም፡ ታብቅል፥ጽድቅም፡በአንድነት፡ይብቀል፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ፈጥሬዋለኹ።
9ከሠሪው፡ጋራ፡ለሚታገል፡ወዮለት! በምድር፡ሸክላዎች፡መካከል፡ያለ፡ሸክላ፡ነው።ጭቃ፡ ሠሪውን፦ምን፡ትሠራለኽ፧ወይስ፡ሥራኽ፦እጅ፡የለውም፡ይላልን፧
10አባትን፦ምን፡ወልደኻል፧ወይም፡ሴትን፦ምን፡አማጥሽ፧ለሚል፡ወዮ!
11የእስራኤል፡ቅዱስ፡ሠሪውም፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ስለሚመጣው፡ነገር፡ጠይቁኝ፥ስለ፡ ልጆቼና፡ስለእጄ፡ሥራም፡እዘዙኝ።
12እኔ፡ምድርን፡ሠርቻለኹ፡ሰውንም፡በርሷ፡ላይ፡ፈጥሬያለኹ፤እኔ፡በእጄ፡ሰማያትን፡ ዘርግቻለኹ፥ሰራዊታቸውንም፡ዅሉ፡አዝዣለኹ።
13እኔ፡በጽድቅ፡አስነሥቼዋለኹ፥መንገዱንም፡ዅሉ፡አቀናለኹ፤ርሱ፡ከተማዬን፡ይሠራል፥በዋጋም፡ወይም፡ በደመ፡ወዝ፡ሳይኾን፡ምርኮኛዎቼን፡ያወጣል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
14እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡ይላል፦የግብጽ፡ድካምና፡የኢትዮጵያ፡ንግድ፡ቁመተ፡ረዥሞችም፡የሳባ፡ ሰዎች፡ወዳንተ፡ያልፋሉ፤ለአንተም፡ይኾናሉ፡እጆቻቸውም፡ታስረው፡ይከተሉኻል፤በፊትኽም፡ ያልፋሉ፥ለአንተም፡እየሰገዱ፦በእውነት፡እግዚአብሔር፡ባንተ፡አለ፥ከርሱም፡ሌላ፡አምላክ፡የለም፡ብለው፡ ይለምኑኻል።
15የእስራኤል፡አምላክ፡መድኀኒት፡ሆይ፥በእውነት፡አንተ፡ራስኽን፡የምትሰውር፡አምላክ፡ነኽ።
16ዅሉም፡ያፍራሉ፡ይዋረዱማል፥ጣዖታትንም፡የሚሠሩ፡በአንድነት፡ወደ፡ውርደት፡ይኼዳሉ።
17እግዚአብሔር፡ግን፡እስራኤልን፡በዘላለማዊ፡መድኀኒት፡ያድነዋል፥እናንተም፡ለዘለዓለም፡አታፍሩምና፡ አትዋረዱም።
18ሰማያትን፡የፈጠረ፡እግዚአብሔር፥ርሱም፡ምድርን፡የሠራና፡ያደረገ፡ያጸናትም፥መኖሪያም፡ልትኾን፡ እንጂ፡ለከንቱ፡እንድትኾን፡ያልፈጠራት፡አምላክ፥እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፡ከእኔም፡በቀር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ሌላ፡የለም።
19በስውር፡ወይም፡በጨለማ፡ምድር፡ስፍራ፡አልተናገርኹም፤ለያዕቆብ፡ዘር፦በከንቱ፡ፈልጉኝ፡ አላልኹም፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ጽድቅን፡እናገራለኹ፡ቅንንም፡አወራለኹ።
20እናንተ፡ከአሕዛብ፡ወገን፡ኾናችኹ፡ያመለጣችኹ፥ተሰብስባችኹ፡ኑ፡በአንድነትም፡ቅረቡ፤የተቀረጸውን፡ የምስላቸውን፡ዕንጨት፡የሚሸከሙና፡ያድን፡ዘንድ፡ወደማይችል፡አምላክ፡የሚጸልዩ፡ዕውቀት፡የላቸውም።
21ይናገሩ፡ይቅረቡም፡በአንድነትም፡ይማከሩ፤ከጥንቱ፡ይህን፡ያሳየ፡ከቀድሞስ፡የተናገረ፡ማን፡ ነው፧ያሳየኹም፡የተናገርኹም፡እኔ፡እግዚአብሔር፡አይደለኹምን፧ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡አምላክ፡የለም፤እኔ፡ ጻድቅ፡አምላክና፡መድኀኒት፡ነኝ፥ከእኔም፡በቀር፡ማንም፡የለም።
22እናንተ፡የምድር፡ዳርቻ፡ዅሉ፥እኔ፡አምላክ፡ነኝና፥ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡የለምና፡ወደ፡እኔ፡ዘወር፡በሉ፡ ትድኑማላችኹ።
23ቃሌ፡ከአፌ፡በጽድቅ፡ወጥታለች፥አትመለስም።ጕልበት፡ዅሉ፡ለእኔ፡ይንበረከካል፥ምላስም፡ዅሉ፡በእኔ፡ ይምላል፡ብዬ፡በራሴ፡ምያለኹ።
24ስለ፡እኔም፦በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ብቻ፡ጽድቅና፡ኀይል፡አለ፥ወደ፡ርሱም፡ሰዎች፡ ይመጣሉ፥በርሱም፡ላይ፡የተቈጡ፡ዅሉ፡ያፍራሉ።
25የእስራኤልም፡ዘር፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ይጸድቃሉ፥ይመካሉም፡ይባላል።