Skip to content
← Isaiah

Chapter 46 · Amharic

Isaiah

1ቤል፡ተዋረደ፥ናባው፡ተሰባበረ፤ጣዖቶቻቸው፡በእንስሳና፡በከብት፡ላይ፡ተጭነዋል፤ሸክሞቻችኹ፡ለደካማ፡ እንስሳ፡ከባድ፡ጭነት፡ኾነዋል።

2ተጐነበሱ፡በአንድነትም፡ተዋረዱ፤ሸክሙን፡ለማዳን፡አልቻሉም፥ራሳቸው፡ግን፡ተማረኩ።

3እናንተ፡የያዕቆብ፡ቤት፡ሆይ፥የእስራኤልም፡ቤት፡ቅሬታ፡ዅሉ፥ከሆድ፡ያነሣዃችኹ፡ከማሕፀንም፡ የተሸከምዃችኹ፥ስሙኝ።

4እስከ፡ሽምግልና፡ድረስ፡እኔ፡ነኝ፥እስከ፡ሽበትም፡ድረስ፡እሸከማችዃለኹ፤እኔ፡ሠርቻለኹ፡እኔም፡ አነሣለኹ፤እኔ፡እሸከማለኹ፡እኔም፡አድናለኹ።

5በማን፡ትመስሉኛላችኹ፧ከማንስ፡ጋራ፡ታስተካክሉኛላችኹ፧እንመሳሰል፡ዘንድ፡ከማን፡ጋራ፡ ታስተያዩኛላችኹ፧

6ወርቁን፡ከኰረጆ፡የሚያፈሱ፟፥ብሩንም፡በሚዛን፡የሚመዝኑ፡እነርሱ፡አንጥረኛውን፡ይቀጥራሉ፥ርሱም፡ አምላክ፡አድርጎ፡ይሠራ፡ዋል፤ለዚያም፡ይጐ፟ነበሱለታል፥ይሰግዱለትማል።

7በጫንቃቸው፡ላይ፡አንሥተው፡ይሸከሙታል፡በስፍራውም፡ያደርጉታል፥በዚያም፡ይቆማል፥ከስፍራውም፡ ፈቀቅ፡አይልም፤ሰውም፡ወደ፡ርሱ፡ቢጮኽ፡አይሰማውም፡ከመከራውም፡አያድነውም።

8ይህን፡ዐስቡና፡አልቅሱ፤ተላላፊዎች፡ሆይ፥ንስሓ፡ግቡ፥ልባችኹንም፡መልሱ።

9እኔ፡አምላክ፡ነኝና፥ሌላም፡የለምና፡የቀድሞውን፡የጥንቱን፡ነገር፡ዐስቡ፤እኔ፡እግዚአብሔር፡ነኝ፡እንደ፡ እኔም፡ያለ፡ማንም፡የለም።

10በመዠመሪያ፡መጨረሻውን፥ከጥንትም፡ያልተደረገውን፡እነግራለኹ፤ምክሬ፡ትጸናለች፡ፈቃዴንም፡ዅሉ፡ እፈጽማለኹ፡እላለኹ።

11ከምሥራቅ፡ነጣቂ፡ወፍን፥ከሩቅም፡አገር፡ምክሬን፡የሚያደርገውን፡ሰው፡ እጠራዋለኹ።ተናግሬያለኹ፤እፈጽማለኹ፤ዐስቤያለኹ፡አደርግማለኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

12እናንተ፡ከጽድቅ፡የራቃችኹ፡እልከኛዎች፥ስሙኝ፤

13ጽድቄን፡አቀርባለኹ፥አይርቅም፡መድኀኒቴም፡አይዘገይም፤ከጽዮን፡ለክብር፡እንዲኾን፡መድኀኒትን፡ ለእስራኤል፡ሰጥቻለኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source