Skip to content
← Isaiah

Chapter 47 · Amharic

Isaiah

1አንቺ፡ድንግል፡የባቢሎን፡ልጅ፡ሆይ፥ውረጂ፡በትቢያም፡ላይ፡ተቀመጪ፤የከለዳውያን፡ሴት፡ልጅ፡ ሆይ፥ከዚህ፡በዃላ፡ቅልጣናምና፡ቅምጥል፡አትባይምና፥ያለዙፋን፡በመሬት፡ላይ፡ተቀመጪ።

2ወፍጮ፡ወስደሽ፡ዱቄትን፡ፍጪ፤መሸፈኛሽን፡አውጪ፡ረዥሙንም፡ልብስሽን፡አውልቀሽ፡ ጣዪው፤ባትሽን፡ግለጪ፥ወንዙን፡ተሻገሪ።

3ኀፍረተ፡ሥጋሽ፡ይገለጣል፡ዕፍረትሽም፡ይታያል፤እኔ፡እበቀላለኹ፥ለማንም፡አልራራም።

4ታዳጊያችን፥ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥የእስራኤል፡ቅዱስ፡ነው።

5የከለዳውያን፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ከዚህ፡በዃላ፦የመንግሥታት፡እመቤት፡አትባይምና፥ዝም፡ብለሽ፡ ተቀመጪ፥ወደ፡ጨለማም፡ውስጥ፡ግቢ።

6በሕዝቤ፡ላይ፡ተቈጥቼ፡ነበር፡ርስቴንም፡አረከስኹ፡በእጅሽም፡አሳልፌ፡ሰጠዃቸው፤ከነርሱ፡ጋራ፡ ምሕረት፡አላደረግሽም፥በሽማግሌዎቻቸው፡ላይ፡ቀንበርሽን፡እጅግ፡አክብደሻል።

7አንቺም፦እኔ፡ለዘለዓለም፡እመቤት፡እኾናለኹ፡ብለሻል፤ይህንም፡በልብሽ፡አላደረግሽም፡ፍጻሜውንም፡ አላሰብሽም።

8አኹንም፡አንቺ፡ቅምጥል፡ተዘልለሽ፡የምትቀመጪ፥በልብሽም፦እኔ፡ነኝ፡ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡ የለም፤መበለትም፡ኾኜ፡አልኖርም፡የወላድ፡መካንነትንም፡አላውቅም፡የምትዪ፡ይህን፡ስሚ፤

9አኹን፡ግን፡ባንድ፡ቀን፡እነዚህ፡ኹለት፡ነገሮች፥የወላድ፡መካንነትና፡መበለትነት፥በድንገት፡ ይመጡብሻል፤ስለ፡መተቶችሽ፡ብዛትና፡ስለ፡አስማቶችሽ፡ጽናት፡ፈጽመው፡ይመጡብሻል።

10በክፋትሽ፡ታምነሻል፤የሚያየኝ፡የለም፡ብለሻል፤ጥበብሽና፡ዕውቀትሽ፡አታለ፟ውሻል፥በልብሽም፦እኔ፡ ነኝ፡ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡የለም፡ብለሻል።

11ስለዚህ፡ምክንያት፡ክፉ፡ነገር፡ይመጣብሻል፥በሟርትሽም፡እንዴት፡እንደምታርቂው፡አታውቂም፤ጕዳት፡ ይወድቅብሻል፥ታስወግጂውም፡ዘንድ፡አይቻልሽም፤የማታውቂያትም፡ጕስቍልና፡ድንገት፡ትመጣብሻለች።

12ምናልባትም፡መጠቀም፡ትችዪ፡ወይም፡ታስደነግጪ፡እንደ፡ኾነ፥ከአስማቶችሽና፡ከሕፃንነትሽ፡ዠምረሽ፡ ከደከምሽበት፡ከመተቶችሽ፡ብዛት፡ጋራ፡ቁሚ።

13በምክርሽ፡ብዛት፡ደክመሻል፤አኹንም፡የሰማይን፡ከዋክብት፡የሚቈጥሩ፥ከዋክብትንም፡ የሚመለከቱ፥በየመባቻውም፡የሚመጣውን፡ነገር፡የሚናገሩ፡ተነሥተው፡ከሚመጣብሽ፡ነገር፡ያድኑሽ።

14እንሆ፥እንደ፡እብቅ፡ይኾናሉ፥እሳትም፡ያቃጥላቸዋል፡ሰውነታቸውንም፡ከነበልባል፡ኀይል፡ አያድኑም፤ርሱም፡ሰው፡እንደሚሞቀው፡ፍም፥ወይም፡በፊቱ፡ሰው፡እንደሚቀመጥበት፡እሳት፡ያለ፡አይደለም።

15የደከምሽባቸው፡ነገሮች፡እንዲህ፡ይኾኑብሻል፤ከሕፃንነትሽ፡ዠምረው፡ከአንቺ፡ጋራ፡ይነግዱ፡የነበሩ፡ እያንዳንዳቸው፡ወደ፡ስፍራቸው፡ይኼዳሉ፥የሚያድንሽም፡የለም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source