1እናንተ፡በእስራኤል፡ስም፡የተጠራችኹ፡ከይሁዳም፡ውሃዎች፡የወጣችኹ፥በእግዚአብሔር፡ስም፡ የምትምሉ፥በእውነት፡ሳይኾን፡በጽድቅም፡ሳይኾን፡የእስራኤልን፡አምላክ፡የምትጠሩ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
2በቅድስት፡ከተማ፡ስም፡የተጠራችኹ፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡በሚባል፡በእስራኤል፡ አምላክ፡የምትደገፉ፥የያዕቆብ፡ቤት፡ሆይ፥ይህን፡ስሙ።
3የቀድሞውን፡ነገር፡ከጥንት፡ተናግሬያለኹ፥ከአፌም፡ወጥቷል፡አሳይቼውማለኹ፤ድንገት፡አድርጌዋለኹ፡ ተፈጽሞማል።
4አንተ፡እልከኛ፥ዐንገትኽም፡የብረት፡ዥማት፥ግንባርኽም፡ናስ፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቄያለኹ፤
5ስለዚህ፥አንተ፦ጣዖቴ፡ይህን፡አድርጓል፥የተቀረጸው፡ምስሌና፡ቀልጦ፡የተሠራው፡ምስሌ፡ይህን፡አዘዙኝ፡ እንዳትል፥አስቀድሜ፡ነግሬኽ፡ነበር፡ሳይኾንም፡አሳይቼኽ፡ነበር።
6ሰምተኻል፤ይህን፡ዅሉ፡ተመልከት፤እናንተም፡የምትናገሩት፡አይደላችኹምን፧የተሰወሩትን፡ ያላወቅኻቸውንም፡ዐዲሶች፡ነገሮችን፡ከዚህ፡ዠምሬ፡አሳይቼኻለኹ።
7እነርሱም፡አኹን፡እንጂ፡ከጥንት፡አልተፈጠሩም፤አንተም፦እንሆ፥ዐውቄያቸዋለኹ፡እንዳትል፡ከዛሬ፡ በፊት፡አልሰማኻቸውም።
8አልሰማኽም፥አላወቅኽም፥ዦሮኽ፡ከጥንት፡አልተከፈተችም፤አንተ፡ፈጽሞ፡ወንጀለኛ፡እንደ፡ኾንኽ፡ ከማሕፀንም፡ዠምረኽ፡ተላላፊ፡ተብለኽ፡አንደ፡ተጠራኽ፡ዐውቄያለኹና።
9ስለ፡ስሜ፡ቍጣዬን፡አዘገያለኹ፥እንዳላጠፋኽም፡ስለ፡ምስጋናዬ፡እታገሣለኹ።
10እንሆ፥አንጥሬኻለኹ፥ነገር፡ግን፥እንደ፡ብር፡አይደለም፤በመከራም፡እቶን፡ፈትኜኻለኹ።
11ስለ፡እኔ፥ስለ፡ራሴ፡አደርገዋለኹ፡ስሜ፡ተነቅፏልና፤ክብሬንም፡ለሌላ፡አልሰጥም።
12ያዕቆብ፡ሆይ፥የጠራኹኽም፡እስራኤል፡ሆይ፥ስማኝ፤እኔ፡ነኝ፤እኔ፡ፊተኛው፡ነኝ፡እኔም፡ዃለኛው፡ ነኝ።
13እጄም፡ምድርን፡መሥርታለች፡ቀኜም፡ሰማያትን፡ዘርግታለች፤በጠራዃቸው፡ጊዜ፡በአንድነት፡ይቆማሉ።
14እናንተ፡ዅሉ፥በአንድነት፡ተሰብስባችኹ፡ስሙ፤ከነርሱ፡ይህን፡የተናገረ፡ማን፡ነው፧እግዚአብሔር፡ የወደደው፡ፈቃዱን፡በባቢሎን፡ላይ፡ያደርጋል፥ክንዱም፡በከለዳውያን፡ላይ፡ይኾናል።
15እኔ፡ራሴ፡ተናግሬያለኹ፤እኔ፡ጠርቼዋለኹ፤አምጥቼዋለኹ፥መንገዱም፡ትከናወንለታለች።
16ወደ፡እኔ፡ቅረቡ፡ይህንም፡ስሙ፤እኔ፡ከጥንት፡ዠምሬ፡በስውር፡አልተናገርኹም፤ከኾነበት፡ዘመን፡ ዠምሮ፡እኔ፡በዚያ፡ነበርኹ፥አኹንም፡ጌታ፡እግዚአብሔርና፡መንፈሱ፡ልከውኛል።
17ታዳጊኽ፥የእስራኤል፡ቅዱስ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡የሚረባኽን፡ነገር፡የማስተምርኽ፡ በምትኼድባትም፡መንገድ፡የምመራኽ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ነኝ።
18ትእዛዜን፡ብትሰማ፡ኖሮ፥ሰላምኽ፡እንደ፡ወንዝ፡ጽድቅኽም፡እንደ፡ባሕር፡ሞገድ፡በኾነ፡ነበር፤
19ዘርኽም፡እንደ፡አሸዋ፡የሆድኽም፡ትውልድ፡እንደምድር፡ትቢያ፡በኾነ፡ነበር፥ስሙም፡ከፊቴ፡ባልጠፋና፡ ባልፈረሰ፡ነበር።
20ከባቢሎን፡ውጡ፡ከከለዳውያንም፡ኰብልሉ፤በእልልታ፡ድምፅ፡ተናገሩ፡ይህንም፡ንገሩ፡እስከምድርም፡ ዳርቻ፡ድረስ፡አውሩና፦እግዚአብሔር፡ባሪያውን፡ያዕቆብን፡ታድጎታል፡በሉ።
21በምድረ፡በዳ፡በኩል፡በመራቸው፡ጊዜ፡አልተጠሙም፤ውሃንም፡ከአለቱ፡ውስጥ፡ አፈለቀላቸው፥አለቱንም፡ሰነጠቀ፡ውሃውም፡ፈሰሰ።
22ለክፉዎች፡ሰላም፡የላቸውም፡ይላል፡እግዚአብሔር።