1እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እናታችኹን፡የፈታኹበት፡የፍቿ፡ጽሕፈት፡የት፡አለ፧ወይስ፡እናንተን፡ የሸጥኹ፡ከአበዳሪዎች፡ለየትኛው፡ነው፧እንሆ፥ስለ፡ኀጢአታችኹ፡ተሽጣችዃል፥ስለ፡በደላችኹም፡ እናታችኹ፡ተፈታ፟ለች።
2በመጣኹስ፡ጊዜ፡ሰው፡ስለ፡ምን፡አልነበረም፧በጠራኹስ፡ጊዜ፡የሚመልስ፡ስለ፡ምን፡ አልነበረም፧መታደግ፡እንዳትችል፡እጄ፡ዐጪር፡ኾናለችን፧ወይስ፡ለማዳን፡ኀይል፡ የለኝምን፧እንሆ፥በገሠጽኹ፡ጊዜ፡ባሕርን፡አደርቃለኹ፥ወንዞችንም፡ምድረ፡በዳ፡አደርጋቸዋለኹ፤ውሃም፡ በማጣት፡ዓሣዎቻቸው፡ይገማሉ፡በጥማትም፡ይሞታሉ።
3ሰማያትን፡ጥቍረት፡አለብሳቸዋለኹ፥መጋረጃቸውንም፡ማቅ፡አደርጋለኹ።
4የደከመውን፡በቃል፡እንዴት፡እንደምደግፍ፡ዐውቅ፡ዘንድ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡የተማሩትን፡ምላስ፡ ሰጥቶኛል፡ማለዳ፡ማለዳ፡ያነቃኛል፥እንደ፡ተማሪዎችም፡ትሰማ፡ዘንድ፡ዦሮዬን፡ያነቃቃል።
5ጌታ፡እግዚአብሔር፡ዦሮዬን፡ከፍቷል፥እኔም፡ዐመፀኛ፡አልነበርኹም፡ወደ፡ዃላዬም፡አልተመለስኹም።
6ዠርባዬን፡ለገራፊዎች፡ጕንጬንም፡ለጠጕር፡ነጪዎች፡ሰጠኹ፥ፊቴንም፡ከውርደትና፡ከትፋት፡ አልመለስኹም።
7ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይረዳኛልና፥ስለዚህ፡አልታወክኹም፤ስለዚህም፡ፊቴን፡እንደ፡ባልጩት፡ድንጋይ፡ አድርጌዋለኹ፥እንዳላፍርም፡ዐውቃለኹ።
8የሚያጸድቀኝ፡ቅርብ፡ነው፤ከእኔስ፡ጋራ፡የሚከራከር፡ማን፡ነው፧በአንድነት፡እንቁም፤የሚከራከረኝ፡ማን፡ ነው፧ወደ፡እኔ፡ይቅረብ።
9እንሆ፥ጌታ፡እግዚአብሔር፡ይረዳኛል፤ማን፡ይፈርድብኛል፧እንሆ፥ዅሉ፡እንደ፡ልብስ፡ያረጃሉ፡ብልም፡ ይበላቸዋል።
10ከእናንተ፡እግዚአብሔርን፡የሚፈራ፥የባሪያውንም፡ቃል፡የሚሰማ፥በጨለማም፡የሚኼድ፥ብርሃንም፡ የሌለው፥ነገር፡ግን፥በእግዚአብሔር፡ስም፡የሚታመን፥በአምላኩም፡የሚደገፍ፡ማን፡ነው፧
11እንሆ፥እሳት፡የምታነዱ፟፡የእሳትንም፡ወላፈን፡የምትታጠቁ፡ዅላችኹ፥በእሳታችኹ፡ነበልባል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ባነደዳችኹትም፡ወላፈን፡ኺዱ፤ይህ፡ከእጄ፡ይኾንባችዃል፤በሐዘን፡ትተኛላችኹ።