1የሰማነውን፡ነገር፡ማን፡አምኗል፧የእግዚአብሔርስ፡ክንድ፡ለማን፡ተገልጧል፧
2በፊቱ፡እንደ፡ቡቃያ፡ከደረቅም፡መሬት፡እንደ፡ሥር፡አድጓል።መልክና፡ውበት፡የለውም፥ባየነውም፡ጊዜ፡ እንወደ፟ው፡ዘንድ፡ደም፡ግባት፡የለውም።
3የተናቀ፡ከሰውም፡የተጠላ፥የሕማም፡ሰው፡ደዌንም፡የሚያውቅ፡ነው፤ሰውም፡ፊቱን፡እንደሚሰውርበት፡ የተናቀ፡ነው፥እኛም፡አላከበርነውም።
4በእውነት፡ደዌያችንን፡ተቀበለ፡ሕመማችንንም፡ተሸክሟል፤እኛ፡ግን፡እንደ፡ተመታ፡በእግዚአብሔርም፡ እንደ፡ተቀሠፈ፡እንደ፡ተቸገረም፡ቈጠርነው።
5ርሱ፡ግን፡ስለ፡መተላለፋችን፡ቈሰለ፥ስለ፡በደላችንም፡ደቀቀ፤የደኅንነታችንም፡ተግሣጽ፡በርሱ፡ላይ፡ ነበረ፥በርሱም፡ቍስል፡እኛ፡ተፈወስን።
6እኛ፡ዅላችን፡እንደ፡በጎች፡ተቅበዝብዘን፡ጠፋን፤ከእኛ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ገዛ፡መንገዱ፡ አዘነበለ፤እግዚአብሔርም፡የዅላችንን፡በደል፡በርሱ፡ላይ፡አኖረ።
7ተጨነቀ፡ተሣቀየም፡አፉንም፡አልከፈተም፤ለመታረድ፡እንደሚነዳ፡ጠቦት፥በሸላቾቹም፡ፊት፡ዝም፡ እንደሚል፡በግ፥እንዲሁ፡አፉን፡አልከፈተም።
8በማስጨነቅና፡በፍርድ፡ተወሰደ፤ስለሕዝቤ፡ኀጢአት፡ተመቶ፟፡ከሕያዋን፡ምድር፡እንደ፡ተወገደ፡ ከትውልዱ፡ማን፡አስተዋለ፧
9ከክፉዎችም፡ጋራ፡መቃብሩን፡አደረጉ፥ከባለጠጋዎችም፡ጋራ፡በሞቱ፡ኾኖም፡ግፍን፡አላደረገም፡ ነበር፥በአፉም፡ተንኰል፡አልተገንበትም፡ነበር።
10እግዚአብሔርም፡በደዌ፡ያደቀ፟ው፡ዘንድ፡ፈቀደ፤ነፍሱን፡ስለ፡ኀጢአት፡መሥዋዕት፡ካደረገ፡በዃላ፡ዘሩን፡ ያያል፥ዕድሜውም፡ይረዝማል፥የእግዚአብሔርም፡ፈቃድ፡በእጁ፡ይከናወናል።
11ከነፍሱ፡ድካም፡ብርሃን፡ያያል፡ደስም፡ይለዋል፤ጻድቅ፡ባሪያዬም፡በዕውቀቱ፡ብዙ፡ሰዎችን፡ ያጸድቃል፥ኀጢአታቸውን፡ይሰከማል።
12ስለዚህም፡ርሱ፡ብዙዎችን፡ይወርሳል፥ከኀያላንም፡ጋራ፡ምርኮን፡ይከፋፈላል፤ነፍሱን፡ለሞት፡አሳልፎ፡ ሰጥቷልና፥ከዐመፀኛዎችም፡ጋራ፡ተቈጥሯልና፤ርሱ፡ግን፡የብዙ፡ሰዎችን፡ኀጢአት፡ተሸከመ፥ስለ፡ ዐመፀኛዎችም፡ማለደ።