1አንቺ፡ያልወለድሽ፡መካን፡ሆይ፥ዘምሪ፤አንቺ፡ያላማጥሽ፡ሆይ፥እልል፡በዪ፥ጩኺም፤ባል፡ካላት፡ ይልቅ፡ፈት፡የኾነቺቱ፡ልጆች፡በዝተዋልና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
2የድንኳንሽን፡ስፍራ፡አስፊ፥መጋረጃዎችሽንም፡ይዘርጉ፤አትቈጥቢ፤አውታሮችሽን፡አስረዝሚ፡ ካስማዎችሽንም፡አጽኚ።
3በቀኝና፡በግራ፡ትሰፋፊያለሽና፥ዘርሽም፡አሕዛብን፡ይወርሳልና፥የፈረሱትንም፡ከተማዎች፡መኖሪያ፡ ያደርጋልና።
4አታፍሪምና፡አትፍሪ፤አትዋረጂምና፡አትደንግጪ፤የሕፃንነትሽንም፡ዕፍረት፡ትረሺዋለሽ፥የመበለትነትሽንም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ስድብ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አታስቢም።
5ፈጣሪሽ፡ባልሽ፡ነው፥ስሙም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው፤የእስራኤልም፡ቅዱስ፡ታዳጊሽ፡ ነው፥ርሱም፡የምድር፡ዅሉ፡አምላክ፡ይባላል።
6እግዚአብሔር፡እንደ፡ተተወችና፡እንደ፡ተበሳጨች፡በልጅነቷም፡እንደ፡ተጣለች፡ሚስት፡ጠርቶሻል፥ይላል፡ አምላክሽ።
7ጥቂት፡ጊዜ፡ተውኹሽ፥በታላቅም፡ምሕረት፡እሰበስብሻለኹ።
8በጥቂት፡ቍጣ፡ለቅጽበት፡ዐይን፡ፊቴን፡ከአንቺ፡ሰወርኹ፥በዘለዓለምም፡ቸርነት፡እምርሻለኹ፥ይላል፡ ታዳጊሽ፡እግዚአብሔር።
9ይህ፡ለእኔ፡እንደ፡ኖኅ፡ውሃ፡ነው፤የኖኅ፡ውሃ፡ደግሞ፡በምድር፡ላይ፡እንዳያልፍ፡እንደ፡ ማልኹ፥እንዲሁ፡አንቺን፡እንዳልቈጣ፡እንዳልዘልፍሽም፡ምያለኹ።
10ተራራዎች፡ይፈልሳሉ፥ኰረብታዎችም፡ይወገዳሉ፤ቸርነቴ፡ግን፡ከአንቺ፡ዘንድ፡አይፈልስም፡የሰላሜም፡ ቃል፡ኪዳን፡አይወገድም፥ይላል፡መሓሪሽ፡እግዚአብሔር።
11አንቺ፡የተቸገርሽ፡በዐውል፡ነፋስም፡የተናወጥሽ፡ያልተጽናናሽም፥እንሆ፥ድንጋዮችሽን፡ሸላልሜ፡ እገነባለኹ፥በሰንፔርም፡እመሠርትሻለኹ።
12የግንብሽንም፡ጕልላት፡በቀይ፡ዕንቍ፥በሮችሽንም፡በሚያብረቀርቅ፡ዕንቍ፥ዳርቻሽንም፡ዅሉ፡በከበሩ፡ ድንጋዮች፡እሠራለኹ።
13ልጆችሽም፡ዅሉ፡ከእግዚአብሔር፡የተማሩ፡ይኾናሉ፥የልጆችሽም፡ሰላም፡ብዙ፡ይኾናል።
14በጽድቅ፡ትታነጺ᎗ያለሽ፤ከግፍ፡ራቂ፥አትፈሪምም፥ድንጋጤም፡ወደ፡አንቺ፡አትቀርብም።
15እንሆ፥ይሰበሰባሉ፥ነገር፡ግን፥ከእኔ፡ዘንድ፡አይኾንም፤ባንቺም፡ላይ፡የሚሰበሰቡ፡ዅሉ፡ከአንቺ፡የተነሣ፡ ይወድቃሉ።
16እንሆ፥ፍሙን፡በወናፍ፡የሚያናፋ፡ለሥራውም፡መሣሪያ፡የሚያወጣ፡ብረት፡ሠሪን፡እኔ፡ ፈጥሬያለኹ፤የሚያፈርሰውንም፡እንዲያጠፋ፡ፈጥሬያለኹ።
17ባንቺ፡ላይ፡የተሠራ፡መሣሪያ፡ዅሉ፡አይከናወንም፤በፍርድም፡በሚነሣብሽ፡ምላስ፡ዅሉ፡ ትፈርጂበታለሽ።የእግዚአብሔር፡ባሪያዎች፡ርስት፡ይህ፡ነው፥ጽድቃቸውም፡ከእኔ፡ዘንድ፡ነው፥ይላል፡ እግዚአብሔር።