1እናንተ፡የተጠማችኹ፡ዅሉ፥ወደ፡ውሃ፡ኑ፥ገንዘብም፡የሌላችኹ፡ኑና፡ግዙ፡ብሉም፤ኑ፡ያለገንዘብም፡ ያለዋጋም፡የወይን፡ጠጅና፡ወተት፡ግዙ።
2ገንዘብን፡እንጀራ፡ላይደለ፥የድካማችኹንም፡ዋጋ፡ለማያጠግብ፡ነገር፡ለምን፡ ትመዝናላችኹ፧አድምጡኝ፥በረከትንም፡ብሉ፥ሰውነታችኹም፡በጮማ፡ደስ፡ይበለው።
3ዦሯችኹን፡አዘንብሉ፡ወደ፡እኔም፡ቅረቡ፤ስሙ፡ሰውነታችኹም፡በሕይወት፡ትኖራለች፤የታመነችዪቱን፡ የዳዊትን፡ምሕረት፥የዘለዓለምን፡ቃል፡ኪዳን፡ከእናንተ፡ጋራ፡አደርጋለኹ።
4እንሆ፥ለአሕዛብ፡ምስክር፥ለወገኖችም፡አለቃና፡አዛዥ፡እንዲኾን፡ሰጥቼዋለኹ።
5እንሆ፥የማታውቀውን፡ሕዝብ፡ትጠራለኽ፥የእስራኤልም፡ቅዱስ፡አክብሮኻልና፥ስለ፡አምላክኽ፡ስለ፡ እግዚአብሔር፡የማያውቁኽ፡ሕዝብ፡ወዳንተ፡ይሮጣሉ።
6እግዚአብሔር፡በሚገኝበት፡ጊዜ፡ፈልጉት፥ቀርቦም፡ሳለ፡ጥሩት፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
7ክፉ፡ሰው፡መንገዱን፡በደለኛም፡ዐሳቡን፡ይተው፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡ይመለስ፡ርሱም፡ ይምረዋል፥ይቅርታውም፡ብዙ፡ነውና፥ወደ፡አምላካችን፡ይመለስ።
8ዐሳቤ፡እንደ፡ዐሳባችኹ፡መንገዳችኹም፡እንደ፡መንገዴ፡አይደለምና፡ይላል፡እግዚአብሔር።
9ሰማይ፡ከምድር፡ከፍ፡እንደሚል፥እንዲሁ፡መንገዴ፡ከመንገዳችኹ፡ዐሳቤም፡ከዐሳባችኹ፡ከፍ፡ያለ፡ነው።
10ዝናብና፡በረዶ፡ከሰማይ፡እንደሚወርድ፥ምድርን፡እንደሚያረካት፥ታበቅልና፡ታፈራም፡ዘንድ፡ እንደሚያደርጋት፥ዘርንም፡ለሚዘራ፡እንጀራንም፡ለሚበላ፡እንደሚሰጥ፡እንጂ፡ወደ፡ሰማይ፡እንደማይመለስ፥
11ከአፌ፡የሚወጣ፡ቃሌ፡እንዲሁ፡ይኾናል፤የምሻውን፡ያደርጋል፡የላክኹትንም፡ይፈጽማል፡እንጂ፡ወደ፡ እኔ፡በከንቱ፡አይመለስም።
12እናንተም፡በደስታ፡ትወጣላችኹ፡በሰላምም፡ትሸኛላችኹ፤ተራራዎችና፡ኰረብታዎች፡በፊታችኹ፡እልልታ፡ ያደርጋሉ፥የሜዳም፡ዛፎች፡ዅሉ፡ያጨበጭባሉ።
13በሾኽም፡ፋንታ፡ጥድ፡በኵርንችትም፡ፋንታ፡ባርሰነት፡ይበቅላል፤ለእግዚአብሔርም፡መታሰቢያን፡ ለዘለዓለምም፡የማይጠፋ፥ምልክት፡ይኾናል።