1እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ማዳኔ፡ሊመጣ፡ጽድቄም፡ሊገለጥ፡ቀርቧልና፥ፍርድን፡ጠብቁ፡ጽድቅንም፡ አድርጉ።
2ይህን፡የሚያደርግ፡ሰው፡ይህንንም፡የሚይዝ፡የሰው፡ልጅ፥እንዳያረክሰው፡ሰንበትንም፡የሚጠብቅ፡እጁንም፡ ክፋት፡ከማድረግ፡የሚጠብቅ፡ብፁዕ፡ነው።
3ወደ፡እግዚአብሔርም፡የተጠጋ፡መጻተኛ፦በእውነት፡እግዚአብሔር፡ከሕዝቡ፡ይለየኛል፡አይበል፤ጃን፡ ደረባም፦እንሆ፥እኔ፡ደረቅ፡ዛፍ፡ነኝ፡አይበል።
4እግዚአብሔር፡ሰንበቴን፡ስለሚጠብቁ፡ደስ፡የሚያሠኘኝንም፡ነገር፡ስለሚመርጡ፡ቃል፡ኪዳኔንም፡ ስለሚይዙ፡ጃን፡ደረባዎች፡እንዲህ፡ይላልና፦
5በቤቴና፡በቅጥሬ፡ውስጥ፡ከወንዶችና፡ከሴቶች፡ልጆች፡ይልቅ፡የሚበልጥ፡መታሰቢያና፡ስም፡ እሰጣቸዋለኹ፤የማይጠፋም፡የዘለዓለም፡ስም፡እሰጣቸዋለኹ።
6ያገለግሉት፡ዘንድ፡የእግዚአብሔርንም፡ስም፡ይወዱ፡ዘንድ፡ባሪያዎቹም፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ የሚጠጉትንም፡መጻተኛዎች፥እንዳያረክሱት፡ሰንበትን፡የሚጠብቁትን፡ቃል፡ኪዳኔንም፡የሚይዙትን፡ዅሉ፥
7ወደተቀደሰ፡ተራራዬ፡አመጣቸዋለኹ፥በጸሎቴም፡ቤት፡ደስ፡አሠኛቸዋለኹ፤ቤቴ፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡ የሚኾን፡የጸሎት፡ቤት፡ይባላልና፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታቸውንና፡ሌላ፡መሥዋዕታቸውን፡በመሠዊያዬ፡ላይ፡ እቀበላለኹ።
8ከእስራኤል፡የተበተኑትን፡የሚሰበስብ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፦ወደተሰበሰቡት፡ዘንድ፡ሌላዎችን፡ እሰበስብለታለኹ፡ይላል።
9እናንተ፡የምድረ፡በዳ፡አራዊት፡ዅሉ፥እናንተም፡የዱር፡አራዊት፡ዅሉ፥ትበሉ፡ዘንድ፡ቅረቡ።
10ጕበኛዎቹ፡ዕውሮች፡ናቸው፥ዅሉ፡ያለዕውቀት፡ናቸው፤ዅሉም፡ዲዳ፡የኾኑ፡ውሻዎች፡ናቸው፡ ይጮኹም፡ዘንድ፡አይችሉም፤ሕልምን፡ያልማሉ፤ይተኛሉ፤ማንቀላፋትንም፡ይወዳ፟ሉ።
11መብል፡ወዳጆች፡ከቶ፡የማይጠግቡ፡ውሻዎች፡ናቸው፥እነርሱም፡ያስተውሉ፡ዘንድ፡የማይችሉ፡እረኛዎች፡ ናቸው፤ዅሉ፡ወደ፡መንገዳቸው፥ከፊተኛው፡እስከ፡ዃለኛው፡ድረስ፡ዅሉ፥እያንዳንዳቸው፡ወደ፡ጥቅማቸው፡ ዘወር፡ብለዋል።
12ኑ፡የወይን፡ጠጅ፡እንውሰድ፥በሚያሰክርም፡መጠጥ፡እንርካ፤ዛሬም፡እንደ፡ኾነ፡እንዲሁ፡ነገ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይኾናል፥ከዛሬም፡ይልቅ፡እጅግ፡ይበልጣል፡ይላሉ።