Skip to content
← Isaiah

Chapter 57 · Amharic

Isaiah

1ጻድቅ፡ይሞታል፥በልቡም፡ነገሩን፡የሚያኖር፡የለም፤ምሕረተኛዎችም፡ይወገዳሉ፥ጽድቅም፡ከክፋት፡ፊት፡ እንደ፡ተወገደ፡ማንም፡አያስተውልም።

2ወደ፡ሰላም፡ይገባል፤በቅንነት፡የኼደ፡በዐልጋው፡ላይ፡ያርፋል።

3እናንተ፡የአስማተኛዪቱ፡ልጆች፥የአመንዝራውና፡የጋለሞታዪቱ፡ዘር፥ወደዚህ፡ቅረቡ።

4በማን፡ታላግጣላችኹ፧በማንስ፡ላይ፡አፋችኹን፡ታላቅቃላችኹ፧ምላሳችኹንስ፡በማን፡ላይ፡ ታስረዝማላችኹ፧

5እናንተ፡በአድባር፡ዛፎች፡መካከል፡በለመለመም፡ዛፍ፡ዅሉ፡በታች፡በፍትወት፡የምትቃጠሉ፥እናንተም፡ በሸለቆዎች፡ውስጥ፡በአለትም፡ስንጣቂዎች፡በታች፡ሕፃናትን፡የምታርዱ፥የዐመፅ፡ልጆችና፡የሐሰት፡ዘር፡ አይደላችኹምን፧

6በሸለቆው፡ውስጥ፡ያሉ፡የለዘቡ፡ድንጋዮች፡ዕድል፡ፈንታሽ፡ናቸው፥እነርሱም፡ዕጣሽ፡ናቸው፤ለእነርሱም፡ የመጠጥ፡ቍርባን፡አፍሰ፟ሻል፥የእኽልንም፡ቍርባን፡አቅርበሻል።እንግዲህ፡በዚህ፡ነገር፡አልቈጣምን፧

7ከፍ፡ባለውም፡በረዘመውም፡ተራራ፡ላይ፡መኝታሽን፡አደረግሽ፥መሥዋዕትንም፡ትሠዊ፡ዘንድ፡ወደዚያ፡ ወጣሽ።

8ከመዝጊያውና፡ከመቃኑ፡በዃላ፡መታሰቢያሽን፡አደረግሽ፤እኔን፡ትተሽ፡ለሌላ፡ተገልጠሻል፥ወጥተሽ፡ መኝታሽን፡አስፍተሻል፤ቃል፡ኪዳንም፡ተጋባሻቸው፥ባየሽበትም፡ስፍራ፡ዅሉ፡መኝታቸውን፡ወደድሽ።

9ዘይትም፡ይዘሽ፡ወደ፡ንጉሡ፡ኼድሽ፥ሽቱሽንም፡አበዛሽ፥መልእክተኛዎችሽንም፡ወደ፡ሩቅ፡ላክሽ፥እስከ፡ ሲኦልም፡ድረስ፡ተዋረድሽ።

10በመንገድሽም፡ብዛት፡ደከምሽ፥ነገር፡ግን፦ተስፋ፡የለም፡አላልሽም፤የጕልበትን፡መታደስ፡ አገኘሽ፥ስለዚህም፡አልዛልሽም።

11ሐሰትን፡የተናገርሺው፡እኔንም፡ያላሰብሺው፡በልብሽም፡ነገሩን፡ያላኖርሺው፡ማንን፡ሠግተሽ፡ ነው፧ማንንስ፡ፈርተሽ፡ነው፧እኔ፡ብዙ፡ጊዜ፡ዝም፡አልኹ፥አንቺም፡አልፈራሽም።

12እኔ፡ጽድቅሽን፡እናገራለኹ፥ሥራሽም፡አይረባሽም።

13ወደ፡አንቺ፡የሰበሰብሻቸው፡በጮኽሽ፡ጊዜ፡ይታደጉሽ፤ነፋስ፡ግን፡ይወስዳቸዋል፡ሽውሽውታም፡ዅሉን፡ ያስወግዳቸዋል።በእኔ፡የታመነ፡ግን፡ምድሪቱን፡ይገዛል፥የተቀደሰውንም፡ተራራዬን፡ይወርሳል።

14ርሱም፦ጥረጉ፥መንገድን፡አዘጋጁ፥ከሕዝቤም፡መንገድ፡ዕንቅፋትን፡አውጡ፡ይላል።

15ለዘለዓለም፡የሚኖር፡ስሙም፡ቅዱስ፡የኾነ፥ከፍ፡ያለው፡ልዑል፡እንዲህ፡ይላል፦የተዋረዱትን፡ሰዎች፡ መንፈስ፡ሕያው፡ኣደርግ፡ዘንድ፥የተቀጠቀጠውንም፡ልብ፡ሕያው፡ኣደርግ፡ዘንድ፥የተቀጠቀጠና፡የተዋረደ፡ መንፈስ፡ካለው፡ጋራ፡በከፍታና፡በተቀደሰ፡ስፍራ፡እቀመጣለኹ።

16መንፈስም፡የፈጠርኹትም፡ነፍስ፡ከፊቴ፡እንዳይዝል፡ለዘለዓለም፡አልጣላም፥ዅልጊዜም፡አልቈጣም።

17ስለ፡ኀጢአቱ፡ጥቂት፡ጊዜ፡ተቈጥቼ፡ቀሠፍኹት፥ፊቴን፡ሰውሬ፡ተቈጣኹ፤ርሱም፡በልቡ፡መንገድ፡ እያፈገፈገ፡ኼደ።

18መንገዱን፡አይቻለኹ፡እፈውሰውማለኹ፥እመራውማለኹ፥ለርሱና፡ስለ፡ርሱም፡ለሚያለቅሱ፡መጽናናትን፡ እመልሳለኹ።

19የከንፈሮችን፡ፍሬ፡እፈጥራለኹ፤በሩቅም፡በቅርብም፡ላለው፡ሰላም፡ሰላም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይኹን፥እፈውሰውማለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

20ክፉዎች፡ግን፡እንደሚንቀሳቀስ፡ባሕር፡ናቸው፤ጸጥ፡ይል፡ዘንድ፡አይችልምና፥ውሃዎቹም፡ጭቃና፡ ጕድፍ፡ያወጣሉና።

21ለክፉዎች፡ሰላም፡የላቸውም፡ይላል፡አምላኬ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source