Skip to content
← Isaiah

Chapter 58 · Amharic

Isaiah

1በኀይልኽ፡ጩኽ፥አትቈጥብ፥ድምፅኽን፡እንደ፡መለከት፡አንሣ፥ለሕዝቤ፡መተላለፋቸውን፡ለያዕቆብ፡ ቤትም፡ኀጢአታቸውን፡ንገር።

2ነገር፡ግን፥ዕለት፡ዕለት፡ይሹኛል፡መንገዴንም፡ያውቁ፡ዘንድ፡ይወዳ፟ሉ፤ጽድቅን፡እንዳደረጉ፡ የአምላካቸውንም፡ፍርድ፡እንዳልተዉ፡ሕዝብ፡እውነተኛውን፡ፍርድ፡ይለምኑኛል፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡ ለመቅረብ፡ይወዳ፟ሉ።

3ስለ፡ምን፡ጾምን፥አንተም፡አልተመለከትኸንም፧ሰውነታችንንስ፡ስለ፡ምን፡አዋረድን፥አንተም፡ አላወቅኽም፧ይላሉ።እንሆ፥በጾማችኹ፡ቀን፡ፈቃዳችኹን፡ታደርጋላችኹ፥ሠራተኛዎቻችኹንም፡ዅሉ፡ ታስጨንቃላችኹ።

4እንሆ፥ለጥልና፡ለክርክር፡ትጾማላችኹ፡በግፍ፡ጡጫም፡ትማታላችኹ፤ድምፃችኹንም፡ወደ፡ላይ፡ታሰሙ፡ ዘንድ፡ዛሬ፡እንደምትጾሙት፡አትጾሙም።

5እኔ፡የመረጥኹት፡ጾም፡ይህ፡ነውን፧ሰውስ፡ነፍሱን፡የሚያዋርደው፡እንደዚህ፡ባለ፡ቀን፡ነውን፧በእውኑ፡ ራሱን፡እንደ፡እንግጫ፡ዝቅ፡ያደርግ፡ዘንድ፡ማቅንና፡ዐመድንም፡በበታቹ፡ያነጥፍ፡ዘንድ፡ነውን፧በእውኑ፡ ይህን፡ጾም፥በእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡የተወደደ፡ቀን፡ትለዋለኽን፧

6እኔስ፡የመረጥኹት፡ጾም፡ይህ፡አይደለምን፧የበደልን፡እስራት፡ትፈቱ፡ዘንድ፥የቀንበርንስ፡ጠፍር፡ትለቅቁ፡ ዘንድ፥የተገፉትንስ፡ሐራነት፡ትሰዱ፟፡ዘንድ፥ቀንበሩንስ፡ዅሉ፡ትሰብሩ፡ዘንድ፡አይደለምን፧

7እንጀራኽንስ፡ለተራበ፡ትቈርስ፡ዘንድ፥ስደተኛዎቹን፡ድኻዎች፡ወደ፡ቤትኽ፡ታገባ፡ዘንድ፥የተራቈተውንስ፡ ብታይ፡ታለብሰው፡ዘንድ፥ከሥጋ፡ዘመድኽ፡እንዳትሸሽግ፡አይደለምን፧

8የዚያን፡ጊዜ፡ብርሃንኽ፡እንደ፡ንጋት፡ይበራል፥ፈውስኽም፡ፈጥኖ፡ይበቅላል፥ጽድቅኽም፡በፊትኽ፡ ይኼዳል፥የእግዚአብሔርም፡ክብር፡በዃላኽ፡ኾኖ፡ይጠብቅኻል።

9የዚያን፡ጊዜ፡ትጠራለኽ፡እግዚአብሔርም፡ይሰማኻል፤ትጮኻለኽ፡ርሱም፦እንሆኝ፡ይላል።ከመካከልኽ፡ ቀንበርን፡ብታርቅ፥ጣትኽንም፡መጥቀስ፡ብትተው፥

10ባታንጐራጕርም፥ነፍስኽንም፡ለተራበ፡ብታፈስ፟፥የተጨነቀውንም፡ነፍስ፡ብታጠግብ፥ብርሃንኽ፡በጨለማ፡ ይወጣል፡ጨለማኽም፡እንደ፡ቀትር፡ይኾናል።

11እግዚአብሔርም፡ዅልጊዜ፡ይመራኻል፤ነፍስኽንም፡በመልካም፡ነገር፡ያጠግባል፡ዐጥንትኽንም፡ ያጠናል፤አንተም፡እንደሚጠጣ፡ገነት፥ውሃውም፡እንደማያቋርጥ፡ምንጭ፡ትኾናለኽ።

12ከዱሮ፡ዘመን፡የፈረሱት፡ስፍራዎች፡ይሠራሉ፥የብዙ፡ትውልድም፡መሠረት፡ ይታነጻል፤አንተም፦ሰባራውን፡ጠጋኝ፥የመኖሪያ፡መንገድን፡ዐዳሽ፡ትባላለኽ።

13ፈቃድኽን፡በተቀደሰው፡ቀኔ፡ከማድረግ፡እግርኽን፡ከሰንበት፡ብትመልስ፥ሰንበትንም፡ ደስታ፥እግዚአብሔርም፡የቀደሰውን፡ክቡር፡ብትለው፥የገዛ፡መንገድኽንም፡ከማድረግ፡ፈቃድኽንም፡ከማግኘት፡ ከንቱ፡ነገርንም፡ከመናገር፡ተከልክለኽ፡ብታከብረው፥

14በዚያን፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ደስ፡ይልኻል፥በምድርም፡ከፍታዎች፡ላይ፡አወጣኻለኹ፥የአባትኽንም፡ የያዕቆብን፡ርስት፡አበላኻለኹ፤የእግዚአብሔር፡አፍ፡ተናግሯልና። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source