Skip to content
← Isaiah

Chapter 61 · Amharic

Isaiah

1የጌታ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በእኔ፡ላይ፡ነው፥ለድኻዎች፡የምሥራችን፡እሰብክ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ ቀብቶኛልና፤ልባቸው፡የተሰበረውን፡እጠግን፡ዘንድ፥ለተማረኩትም፡ነጻነትን፡ለታሰሩትም፡መፈታትን፡እናገር፡ ዘንድ፡ልኮኛል።

2የተወደደችውን፡የእግዚአብሔርን፡ዓመት፡አምላካችንም፡የሚበቀልበትን፡ቀን፡እናገር፡ ዘንድ፥የሚያለቅሱትንም፡ዅሉ፡አጽናና፡ዘንድ፤

3እግዚአብሔር፡ለክብሩ፡የተከላቸው፡የጽድቅ፡ዛፎች፡እንዲባሉ፡ለጽዮን፡አልቃሾች፡ኣደርግላቸው፡ ዘንድ፥በዐመድ፡ፋንታ፡አክሊልን፥በልቅሶም፡ፋንታ፡የደስታን፡ዘይት፥በሐዘንም፡መንፈስ፡ፋንታ፡የምስጋናን፡ መጐናጸፊያ፡እሰጣቸው፡ዘንድ፡ልኮኛል።

4ከጥንትም፡ዠምሮ፡ባድማ፡የነበሩትን፡ይሠራሉ፡ከቀድሞ፡የፈረሱትንም፡ያቆማሉ፤ባድማ፡የነበሩትንና፡ ከብዙ፡ትውልድ፡በፊት፡የፈረሱትን፡ከተማዎች፡እንደ፡ገና፡ይሠራሉ።

5መጻተኛዎችም፡ቆመው፡በጎቻችኹን፡ያሰማራሉ፥ሌላዎች፡ወገኖችም፡ዐራሾችና፡ወይም፡ጠባቂዎች፡ ይኾኑላችዃል።

6እናንተ፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ካህናት፡ትባላላችኹ፥ሰዎቹም፡የአምላካችን፡አገልጋዮች፡ብለው፡ ይጠሯችዃል፤የአሕዛብን፡ሀብት፡ትበላላችኹ፥በክብራቸውም፡ትመካላችኹ።

7በዕፍረታችኹ፡ፋንታ፡ኹለት፡ዕጥፍ፡ይኾንላችዃል፥በውርደታችኹም፡ፋንታ፡ዕድል፡ፈንታችኹ፡ደስ፡ ይላቸዋል፤ስለዚህ፥በምድራቸው፡ዅሉ፡ዕጥፍ፡ይገዛሉ፥የዘለዓለምም፡ደስታ፡ይኾንላቸዋል።

8እኔ፡እግዚአብሔር፡ፍርድን፡የምወድ፟፡ስርቆትንና፡በደልን፡የምጠላ፡ነኝ፤ፍዳቸውንም፡በእውነት፡ እሰጣቸዋለኹ፥ከነርሱም፡ጋራ፡የዘለዓለም፡ቃል፡ኪዳን፡አደርጋለኹ።

9ዘራቸውም፡በአሕዛብ፡መካከል፥ልጆቻቸውም፡በወገኖች፡መካከል፡የታወቁ፡ይኾናሉ፤ያያቸው፡ዅሉ፡ እግዚአብሔር፡የባረካቸው፡ዘር፡እንደ፡ኾኑ፡ይገነዘባል።

10አክሊልን፡እንደ፡ለበሰ፡ሙሽራ፥በጌጥ፡ሽልማቷም፡እንዳጌጠች፡ሙሽራ፥የማዳንን፡ልብስ፡ አልብሶኛልና፥የጽድቅንም፡መጐናጸፊያ፡ደርቦልኛልና፥በእግዚአብሔር፡እጅግ፡ደስ፡ይለኛል፥ነፍሴም፡ በአምላኬ፡ሐሤት፡ታደርጋለች።

11ምድርም፡ቡቃያዋን፡እንደምታወጣ፥ገነትም፡ዘሩን፡እንደሚያበቅል፥እንዲሁ፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ ጽድቅንና፡ምስጋናን፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ፊት፡ያበቅላል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source