Skip to content
← Isaiah

Chapter 62 · Amharic

Isaiah

1ስለ፡ጽዮን፡ዝም፡አልልም፥ስለ፡ኢየሩሳሌምም፡ጸጥ፡አልልም፥ጽድቋ፡እንደ፡ጸዳል፡መዳኗም፡ እንደሚበራ፡ፋና፡እስኪወጣ፡ድረስ።

2አሕዛብም፡ጽድቅሽን፡ነገሥታትም፡ዅሉ፡ክብርሽን፡ያያሉ፤የእግዚአብሔርም፡አፍ፡በሚጠራበት፡በዐዲሱ፡ ስም፡ትጠሪያለሽ።

3በእግዚአብሔር፡እጅ፡የክብር፡አክሊል፥በአምላክሽም፡እጅ፡የመንግሥት፡ዘውድ፡ትኾኛለሽ።

4ከእንግዲህ፡ወዲህ።የተተወች፡አትባዪም፤ምድርሽም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ።ውድማ፡አትባልም፤ነገር፡ ግን፥እግዚአብሔር፡ባንቺ፡ደስ፡ብሎታልና፥ምድርሽም፡ባል፡ታገባለችና፡አንቺ።ደስታዬ፡የሚኖርባት፡ ትባያለሽ፡ምድርሽም፦ባል፡ያገባች፡ትባላለች።

5ጕልማሳም፡ድንግሊቱን፡እንደሚያገባ፥እንዲሁ፡ልጆችሽ፡ያገቡሻል፤ሙሽራም፡በሙሽራዪቱ፡ደስ፡ እንደሚለው፥እንዲሁ፡አምላክሽ፡ባንቺ፡ደስ፡ይለዋል።

7ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ጕበኛዎችን፡በቅጥርሽ፡ላይ፡አቁሜያለኹ፤ቀንና፡ሌሊት፡ከቶ፡ዝም፡ አይሉም፤እናንተ፡እግዚአብሔርን፡የምታሳስቡ፥ኢየሩሳሌምን፡እስኪያጸና፡በምድርም፡ላይ፡ምስጋና፡ እስኪያደርጋት፡ድረስ፡አትረፉ፡ለርሱም፡ዕረፍት፡አትስጡ።

8እግዚአብሔር፦ከእንግዲህ፡ወዲህ፡በርግጥ፡ለጠላቶችሽ፡መብል፡ይኾን፡ዘንድ፡እኽልሽን፡ አልሰጥም፥መጻተኛዎችም፡የደከምሽበትን፡ወይንሽን፡አይጠጡም፤

9ነገር፡ግን፥የሰበሰቡት፡ይበሉታል፡እግዚአብሔርንም፡ያመሰግናሉ፥ያከማቹትም፡በመቅደሴ፡አደባባይ፡ላይ፡ ይጠጡታል፡ብሎ፡በቀኙና፡በኀይሉ፡ክንድ፡ምሏል።

10ዕለፉ፥በበሮች፡በኩል፡ዕለፉ፤የሕዝቡንም፡መንገድ፡ጥረጉ፤አዘጋጁ፥ጐዳናውን፡አዘጋጁ፥ድንጋዮቹንም፡ አስወግዱ፤ለአሕዛብም፡ዓላማ፡አንሡ።

11እንሆ፥እግዚአብሔር፡ለምድር፡ዳርቻ፡ዐዋጅ፡እንዲህ፡ብሎ፡ነግሯል፦ለጽዮን፡ ልጅ፦እንሆ፥መድኀኒትሽ፡ይመጣል፤እንሆ፥ዋጋው፡ከርሱ፡ጋራ፡ሥራውም፡በፊቱ፡አለ፡በሏት።

12እግዚአብሔር፦የተቤዣቸው፥የተቀደሰ፡ሕዝብ፡ብለው፡ይጠሯቸዋል፤አንቺም፦የተፈለገች፡ ያልተተወችም፡ከተማ፡ትባያለሽ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source