Skip to content
← Isaiah

Chapter 63 · Amharic

Isaiah

1ይህ፡ከኤዶምያስ፥ልብሱም፡የቀላ፡ከባሶራ፡የሚመጣ፥አለባበሱ፡ያማረ፥በጕልበቱ፡ጽናት፡የሚራመድ፡ ማን፡ነው፧በጽድቅ፡የምናገር፡ለማዳንም፡የምበረታ፡እኔ፡ነኝ።

2ቀሚስኽ፡ስለ፡ምን፡ቀላ፧ልብስኽስ፡በወይን፡መጥመቂያ፡እንደሚረግጥ፡ሰው፡ልብስ፡ስለ፡ምን፡መሰለ፧

3መጥመቂያውን፡ብቻዬን፡ረግጫለኹ፥ከአሕዛብም፡አንድ፡ሰው፡ከእኔ፡ጋራ፡አልነበረም፤በቍጣዬ፡ ረገጥዃቸው፡በመዓቴም፡ቀጠቀጥዃቸው፤ደማቸውም፡በልብሴ፡ላይ፡ተረጭቷል፥ልብሴንም፡ዅሉ፡ አሳድፌያለኹ።

4የምበቀልበት፡ቀን፡በልቤ፡ነውና፥የምቤዥበትም፡ዓመት፡ደርሷልና።

5ተመለከትኹ፥የሚረዳም፡አልተገኘም፤የሚያግዝም፡አልነበረምና፡ተደነቅኹ፤ስለዚህ፥የገዛ፡ክንዴ፡ መድኀኒት፡አመጣልኝ፥ቍጣዬም፡ርሱ፡አገዘኝ።

6በቍጣዬም፡አሕዛብን፡ረገጥኹ፡በመዓቴም፡ቀጠቀጥዃቸው፥ደማቸውንም፡ወደ፡ምድር፡አፈሰስኹት። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

7እግዚአብሔር፡እንደ፡ሰጠን፡ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡ቸርነትና፡የእግዚአብሔርን፡ምስጋና፥እንደ፡ምሕረቱና፡ እንደ፡ቸርነቱም፡ብዛት፡ለእስራኤል፡ቤት፡የሰጠውን፡ትልቅ፡በጎነት፡አሳስባለኹ።

8ርሱም፦በእውነት፡ሕዝቤ፥ሐሰትን፡የማያደርጉ፡ልጆች፥ናቸው፡አለ፤መድኀኒትም፡ኾነላቸው።

9በጭንቃቸው፡ዅሉ፡ርሱ፡ተጨነቀ፥የፊቱም፡መልአክ፡አዳናቸው፤በፍቅሩና፡በርኅራኄውም፡ ተቤዣቸው፥በቀደመውም፡ዘመን፡ዅሉ፡አንሥቶ፡ተሸከማቸው።

10እነርሱ፡ግን፡ዐመፁ፡ቅዱስ፡መንፈሱንም፡አስመረሩ፤ስለዚህ፥ተመልሶ፡ጠላት፡ኾናቸው፥ርሱም፡ ተዋጋቸው።

11ርሱም፡እንዲህ፡ብሎ፡የቀደመውን፡ዘመን፡ዐሰበ።የበጎቹን፡እረኛ፡ከባሕሩ፡ያወጣው፡ወዴት፡ነው፡ ያለ፧ቅዱስ፡መንፈሱንም፡በመካከላቸው፡ያኖረ፡ወዴት፡ነው፡ያለ፧

12የከበረውንም፡ክንድ፡በሙሴ፡ቀኝ፡ያስኼደ፥ለራሱም፡የዘለዓለምን፡ስም፡ያደርግ፡ዘንድ፡ውሃውን፡ በፊታቸው፡የከፈለ፥

13በምድረ፡በዳም፡እንደሚያልፍ፡ፈረስ፥በቀላይ፡ውስጥ፡ያለዕንቅፋት፡ያሳለፋቸው፡ወዴት፡ነው፡ያለ፧

14ወደ፡ሸለቆ፡እንደሚወርዱ፡ከብቶች፥እንዲሁ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡ወደ፡ዕረፍት፡ አመጣቸው፤እንዲሁም፡ለራስኽ፡የከበረ፡ስም፡ታደርግ፡ዘንድ፡ሕዝብን፡መራኽ።

15ከሰማይ፡ተመልከት፥ከቅዱስነትኽና፡ከክብርኽም፡ማደሪያ፡ጐብኝ፤ቅንአትኽና፡ኀይልኽስ፡ወዴት፡ ነው፧ለኔም፡የኾነው፡የልብኽ፡ናፍቆትና፡ርኅራኄኽ፡ተከለከለ።

16አብርሃም፡ባያውቀን፡እስራኤልም፡ባይገነዘበን፡አንተ፡አባታችን፡ነኽ፤አቤቱ፥አንተ፡አባታችን፡ ነኽ፥ስምኽም፡ከዘለዓለም፡ታዳጊያችን፡ነው።

17አቤቱ፥ከመንገድኽ፡ለምን፡አሳትኸን፧እንዳንፈራኽም፡ልባችንን፡ለምን፡አጸናኽብን፧ስለ፡ባሪያዎችኽ፡ ስለ፡ርስትኽ፡ነገዶች፡ተመለስ።

18የተቀደሰው፡ሕዝብኽ፡መቅደስኽን፡ጥቂት፡ጊዜ፡ወረሱት፤ጠላቶቻችንም፡ረግጠውታል።

19ከዘለዓለም፡እንዳልገዛኸን፡በስምኽም፡እንዳልተጠራን፡ኾነናል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source