Skip to content
← Isaiah

Chapter 64 · Amharic

Isaiah

1ሰማዮችን፡ቀደ፟ኽ፡ምነው፡ብትወርድ! ተራራዎችም፡ምነው፡ቢናወጡ!

2እሳት፡ጭራሮውን፡እንደሚያቃጥል፥እሳትም፡ውሃውን፡እንደሚያፈላ፥ስምኽ፡ለጠላቶችኽ፡ይገለጥ፡ ዘንድ፥አሕዛብም፡በፊትኽ፡ይንቀጠቀጡ፡ዘንድ።

3ያልተጠባበቅነውን፡የክብርኽን፡ሥራ፡ባደረግኽ፡ጊዜ፥ወረድኽ፡ተራራዎችም፡በፊትኽ፡ተንቀጠቀጡ።

4ሰዎች፡ከጥንት፡ዠምሮ፡ለሚጠብቁኽ፥ከምትሠራላቸው፡ከአንተ፡በቀር፡ሌላ፡አምላክን፡ አልሰሙም፥በዦሯቸውም፡አልተቀበሉም፥ዐይንም፡አላየችም።

5ጽድቅን፡የሚያደርገውን፥በመንገዶችኽም፡የሚያስቡኽን፡ትገናኛቸዋለኽ።እንሆ፥አንተ፡ተቈጣኽ፥እኛም፡ ኀጢአት፡ሠራን፤ስለዚህም፡ተሳሳትን።

6ዅላችን፡እንደ፡ርኩስ፡ሰው፡ኾነናል፥ጽድቃችንም፡ዅሉ፡እንደ፡መርገም፡ጨርቅ፡ነው፤ዅላችንም፡ እንደ፡ቅጠል፡ረግፈናል፥በደላችንም፡እንደ፡ነፋስ፡ወስዶናል።

7ስምኽንም፡የሚጠራ፥አንተንም፡ሊይዝ፡የሚያስብ፡የለም፤ፊትኽንም፡ከእኛ፡ሰውረኻል፥በኀጢአታችንም፡ አጥፍተኸናል።

8አኹን፡ግን፥አቤቱ፥አንተ፡አባታችን፡ነኽ፤እኛ፡ጭቃ፡ነን፡አንተም፡ሠሪያችን፡ነኽ፥እኛም፡ዅላችን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org የእጅኽ፡ሥራ፡ነን።

9አቤቱ፥እጅግ፡አትቈጣ፥ለዘለዓለምም፡ኀጢአትን፡አታስብ፤እንሆ፥እባክኽ፥ተመልከት፥እኛ፡ዅላችን፡ ሕዝብኽ፡ነን።

10የተቀደሱ፡ከተማዎችኽ፡ምድረ፡በዳ፡ኾነዋል፤ጽዮን፡ምድረ፡በዳ፡ኢየሩሳሌምም፡ውድማ፡ኾናለች።

11አባቶቻችን፡አንተን፡ያመሰገኑበት፡የተቀደሰና፡የተዋበ፡ቤታችን፡በእሳት፡ተቃጥሏል፥ያማረውም፡ስፍራችን፡ ዅሉ፡ፈርሷል።

12አቤቱ፥በእውኑ፡በዚህ፡ነገር፡ትታገሣለኽን፧ዝምስ፡ትላለኽን፧አጥብቀኽስ፡ታስጨንቀናለኽን፧

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source