1እናንተ፡የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡በእናንተ፡ላይ፡የተናገረውን፡ቃል፡ስሙ።
2እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የአሕዛብን፡መንገድ፡አትማሩ፡ከሰማይ፡ምልክትም፡አትፍሩ፤አሕዛብ፡ ይፈሩታልና።
3የአሕዛብ፡ልማድ፡ከንቱ፡ነውና፤ዛፍ፡ከዱር፡ይቈረጣል፥በሠራተኛም፡እንጅ፡በመጥረቢያ፡ይሠራል።
4በብርና፡በወርቅ፡ያስጌጡታል፥እንዳይናወጥም፡በችንካርና፡በመዶሻ፡ይቸነክሩታል።
5እንደ፡ተቀረጸ፡ዐምድ፡ናቸው፥እነርሱም፡አይናገሩም፤መራመድም፡አይቻላቸውምና፥ይሸከሟቸዋል።ክፉ፡ መሥራትም፡አይቻላቸውምና፥ደግሞም፡መልካም፡ይሠሩ፡ዘንድ፡አይችሉምና፡አትፍሯቸው።
6አቤቱ፥እንደ፡አንተ፡ያለ፡የለም፤አንተ፡ታላቅ፡ነኽ፥ስምኽም፡በኀይል፡ታላቅ፡ነው።
7የአሕዛብ፡ንጉሥ፡ሆይ፥በአሕዛብ፡ጥበበኛዎች፡ዅሉ፡መካከል፡በመንግሥታቸውም፡ዅሉ፡እንደ፡አንተ፡ ያለ፡ስለሌለ፥አንተን፡መፍራት፡ይገ፟ባ፟ልና፥አንተን፡የማይፈራ፡ማን፡ነው፧
8ባንድ፡ጊዜ፡ሰንፈዋል፥ደንቍረውማል፤ጣዖታት፡የሚያስተምሩት፡የዕንጨት፡ነገር፡ብቻ፡ነው።
9የሠራተኛና፡የአንጥረኛ፡እጅ፡ሥራ፡የኾነ፡ከተርሴስ፡ጥፍጥፍ፡ብር፡ከአፌዝም፡ወርቅ፡ ይመጣል፤ልብሳቸውም፡ሰማያዊና፡ቀይ፡ግምጃ፡ነው፥ዅሉም፡የብልኀተኛዎች፡ሥራ፡ናቸው።
10እግዚአብሔር፡ግን፡እውነተኛ፡አምላክ፡ነው፤ርሱም፡ሕያው፡አምላክና፡የዘለዓለም፡ንጉሥ፡ ነው፤ከቍጣው፡የተነሣ፡ምድር፡ትንቀጠቀጣለች፤አሕዛብም፡መዓቱን፡አይችሉም።
11እናንተም፦ሰማይንና፡ምድርን፡ያልፈጠሩ፡እነዚህ፡አማልክት፡ከምድር፡ላይ፡ከሰማይም፡በታች፡ይጠፋሉ፡ ትሏቸዋላችኹ።
12ምድርን፡በኀይሉ፡የፈጠረ፥ዓለሙን፡በጥበቡ፡የመሠረተ፡ሰማያትንም፡በማስተዋሉ፡የዘረጋ፡ርሱ፡ነው።
13ድምፁን፡ባሰማ፡ጊዜ፡ውሃዎች፡በሰማይ፡ይሰበሰባሉ፥ከምድርም፡ዳር፡ደመናትን፡ከፍ፡ ያደርጋል፤ለዝናቡም፡መብረቅን፡ያደርጋል፥ነፋስንም፡ከቤተ፡መዛግብቱ፡ያወጣል።
14ሰው፡ዅሉ፡ዕውቀት፡ዐጥቶ፡ሰንፏል፥አንጥረኛም፡ዅሉ፡ከቀረጸው፡ምስል፡የተነሣ፡አፍሯል፤ቀልጦ፡ የተሠራ፡ምስሉ፡ውሸት፡ነውና፥እስትንፋስም፡የላቸውምና።
15እነርሱ፡ምናምንቴና፡የቀልድ፡ሥራ፡ናቸው፤በተጐበኙ፡ጊዜ፡ይጠፋሉ።
16የያዕቆብ፡ዕድል፡ፈንታ፡እንደ፡እነዚህ፡አይደለም፤ርሱ፡የዅሉ፡ፈጣሪ፡ነውና፤እስራኤልም፡የርስቱ፡ ነገድ፡ነውና፤ስሙ፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ነው።
17በምሽግ፡ውስጥ፡የተቀመጥሽ፡ሆይ፥ዕቃሽን፡ከመሬት፡ሰብስቢ፤
18እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦እንሆ፥በምድሪቱ፡የሚኖሩትን፡እስኪሰማቸው፡ድረስ፡በዚህ፡ጊዜ፡ እወነጭፋቸዋለኹ፥አስጨንቃቸውማለኹ።
19ስለ፡ስብራቴ፡ወዮልኝ! ቍስሌም፡ክፉ፡ነው፥እኔ፡ግን፦በእውነት፡የመከራ፡ቍስሌ፡ነው፥ርሱንም፡ መሸከም፡ይገ፟ባ፟ኛል፡አልኹ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20ድንኳኔ፡ተበዘበዘ፡አውታሬም፡ዅሉ፡ተቈረጠ፤ልጆቼም፡ከእኔ፡ወጥተው፡አይገኙም፤ድንኳኔንም፡ ከእንግዲህ፡ወዲህ፡የሚዘረጋ፡መጋረጃዎችንም፡የሚያነሣ፡የለም።
21እረኛዎች፡ሰንፈዋልና፥እግዚአብሔርን፡አልጠየቁትምና፡አልተከናወነላቸውም፥መንጋዎቻቸውም፡ዅሉ፡ ተበትነዋል።
22የወሬን፡ድምፅ፡ስሙ፤እንሆም፥የይሁዳን፡ከተማዎች፡ባድማና፡የቀበሮ፡ማደሪያ፡ያደርጋቸው፡ዘንድ፡ ከሰሜን፡ምድር፡ጽኑ፡ሽብር፡መጥቷል።
23አቤቱ፥የሰው፡መንገድ፡ከራሱ፡እንዳይደለ፡ዐውቃለኹ፥አካኼዱንም፡ለማቅናት፡ከሚራመድ፡ሰው፡ አይደለም።
24አቤቱ፥ቅጣኝ፤ነገር፡ግን፥እንዳታዋርደኝ፡በመጠን፡ይኹን፡እንጂ፡በቍጣ፡አይኹን።
25ያዕቆብን፡በልተውታልና፥ውጠውትማልና፥አጥፍተውትማልና፥ማደሪያውንም፡አፍርሰዋልና፥በማያውቁኽ፡ አሕዛብ፡ስምኽንም፡በማይጠሩ፡ወገኖች፡ላይ፡መዓትኽን፡አፍስ፟።