1ተወግተው፡ስለ፡ሞቱ፡ስለሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ሰዎች፡ሌሊትና፡ቀን፡አለቅስ፡ዘንድ፡ራሴ፡ውሃ፥ዐይኔም፡ የእንባ፡ምንጭ፡በኾነልኝ!
2ዅሉም፡አመንዝራዎች፥የአታላዮች፡ጉባኤ፡ናቸውና፥ሕዝቤን፡እተዋቸው፡ዘንድ፡ከነርሱም፡እለይ፡ዘንድ፡ በምድረ፡በዳ፡የመንገደኛዎች፡ማደሪያን፡ማን፡በሰጠኝ፧
3ምላሳቸውን፡ስለ፡ሐሰት፡እንደ፡ቀስት፡ገተሩ፤በምድር፡በረቱ፥ነገር፡ግን፥ለእውነት፡አይደለም፤ከክፋት፡ ወደ፡ክፋት፡ይኼዳሉና፡እኔንም፡አላወቁምና፥ይላል፡እግዚአብሔር።
4ወንድምም፡ዅሉ፡ያሰናክላልና፥ባልንጀራም፡ዅሉ፡ያማልና፥እናንተ፡ዅሉ፡ከባልንጀራዎቻችኹ፡ ተጠንቀቁ፥በወንድሞቻችኹም፡አትታመኑ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
5ሰውም፡ዅሉ፡ባልንጀራውን፡ያታልላል፥በእውነትም፡አይናገርም፤ሐሰትን፡መናገርንም፡ምላሳቸው፡ ተምሯል፥ክፉንም፡ለማድረግ፡ይደክማሉ።
6ማደሪያኽ፡በሽንገላ፡መካከል፡ነው፥ከሽንገላም፡የተነሣ፡እኔን፡ያውቁኝ፡ዘንድ፡እንቢ፡ብለዋል፥ይላል፡ እግዚአብሔር።
7ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥አቀልጣቸዋለኹ፡እፈትናቸውማለኹ፤ስለሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ ክፋት፡ከዚህ፡ሌላ፡የማደርገው፡ምንድር፡ነው፧
8ምላሳቸው፡የተሳለ፡ፍላጻ፡ነው፤ሽንገላን፡ይናገራሉ፡ሰው፡ከባልንጀራው፡ጋራ፡በሰላም፡ይናገራል፥በልቡ፡ ግን፡ያደባበታል።
9በእውኑ፡ስለዚህ፡ነገር፡አልቀሥፍምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ነፍሴስ፡እንደዚህ፡ባለ፡ሕዝብ፡ላይ፡ አትበቀልምን፧
10ለተራራዎች፡ልቅሶን፡ለምድረ፡በዳ፡ማሰማሪያዎችም፡ዋይታን፡አነሣለኹ፥ሰው፡እንዳያልፍባቸው፡በእሳት፡ ተቃጥለዋልና።ሰዎችም፡የከብቱን፡ድምፅ፡አይሰሙም፤ከሰማይ፡ወፎች፡ዠምሮ፡እስከ፡እንስሳ፡ድረስ፡ ሸሽተው፡ኼደዋል።
11ኢየሩሳሌምንም፡የፍርስራሽ፡ክምር፡የቀበሮም፡ማደሪያ፡አደርጋታለኹ፥የይሁዳንም፡ከተማዎች፡ሰው፡ የማይቀመጥባት፡ባድማ፡አደርጋቸዋለኹ።
12ይህን፡የሚያስተውል፡ጠቢብ፡ሰው፡ማን፡ነው፧ያወራስ፡ዘንድ፡የእግዚአብሔር፡አፍ፡ለማን፡ ተናገረ፧ሰው፡እንዳያልፍባት፡ምድርስ፡ስለ፡ምን፡ጠፋች፥እንደ፡ምድረ፡በዳስ፡ስለ፡ምን፡ተቃጠለች፧
13እግዚአብሔርም፡እንዲህ፡አለ፦የሰጠዃቸውን፡ሕጌን፡ትተዋልና፥ቃሌንም፡አልሰሙምና፥
14ነገር፡ግን፥የልባቸውን፡ምኞትና፡አባቶቻቸው፡ያስተማሯቸውን፡በዓሊምን፡ተከትለዋልና፥
15ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ይህን፡ሕዝብ፡ሬትን፡አበላዋለኹ፡ የሐሞትንም፡ውሃ፡አጠጣዋለኹ።
16እነርሱና፡አባቶቻቸውም፡ባላወቋቸው፡አሕዛብ፡መካከል፡እበትናቸዋለኹ፥እስካጠፋቸውም፡ድረስ፡ በስተዃላቸው፡ሰይፍን፡እሰድ፟ባቸዋለኹ።
17እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲመጡ፡አልቃሾች፡ሴቶችን፡ጥሩ፤እንዲመጡም፡ወደ፡ብልኀተኛዎች፡ ሴቶች፡ላኩ፤
18ዐይኖቻችንም፡እንባ፡እንዲያፈሱ፟፡የዐይናችንም፡ሽፋሽፍቶች፡ውሃን፡እንዲያፈልቁ፡ፈጥነው፡ለእኛ፡ ልቅሶውን፡ይያዙ።
19በጽዮን፦እንዴት፡ተበዘበዝን! ምድርንም፡ትተናልና፥ቤቶቻችንንም፡አፍርሰዋልና፥እንዴት፡ዐፈርን! የሚል፡ የልቅሶ፡ድምፅ፡ተሰምቷል።
20እናንተ፡ሴቶች፡ሆይ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ፥ዦሯችኹም፡የአፉን፡ቃል፡ትቀበል፥ለሴቶች፡ ልጆቻችኹም፡ልቅሶውን፥እያንዳንዳችኹም፡ለባልንጀራዎቻችኹ፡ዋይታውን፡አስተምሩ።
21ሕፃናቱን፡ከመንገድ፡ጕልማሳዎቹንም፡ከአደባባይ፡ያጠፉ፡ዘንድ፡ሞት፡ወደ፡መስኮታችን፡ደርሷል፡ወደ፡ አዳራሻችንም፡ውስጥ፡ገብቷል።
22የሰውም፡ሬሳ፡እንደ፡ጕድፍ፡በዕርሻ፡ላይ፥ማንምም፡እንደማይሰበስበው፡ከዐጫጆች፡በዃላ፡እንደሚቀር፡ ቃርሚያ፡ይወድቃል።
23እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ጠቢብ፡በጥበቡ፡አይመካ፥ኀያልም፡በኀይሉ፡አይመካ፥ባለጠጋም፡ በብልጥግናው፡አይመካ፤
24ነገር፡ግን፥የሚመካው።ምሕረትንና፡ፍርድን፡ጽድቅንም፡በምድር፡ላይ፡የማደርግ፡እኔ፡እግዚአብሔር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መኾኔን፡በማወቁና፡በማስተዋሉ፡በዚህ፡ይመካ፤ደስ፡የሚያሠኙኝ፡እነዚህ፡ናቸውና፥ይላል፡እግዚአብሔር። 25-
26አሕዛብ፡ዅሉ፡ያልተገረዙ፡ናቸውና፥የእስራኤልም፡ቤት፡ዅሉ፡ልባቸው፡ያልተገረዘ፡ ነውና፥የተገረዙትን፡ዅሉ፥ግብጽንና፡ይሁዳን፡ኤዶምያስንም፡የዐሞንንም፡ልጆች፡ሞዐብንም፡በምድረ፡በዳም፡ የተቀመጡትን፡ጠጕራቸውን፡በዙሪያ፡የተላጩትን፡ዅሉ፥ባለመገረዛቸው፡እነርሱን፡የምቀጣበት፡ ዘመን፥እንሆ፥ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።