Skip to content
← Jeremiah

Chapter 8 · Amharic

Jeremiah

1በዚያን፡ዘመን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የይሁዳን፡ነገሥታት፡ዐጥንትና፡የመኳንንቶቹን፡ዐጥንት፥የካህናቱን፡ ዐጥንትና፡የነቢያቱን፡ዐጥንት፥የኢየሩሳሌምንም፡ሰዎች፡ዐጥንት፡ከመቃብራቸው፡ያወጣሉ።

2በወደዷቸውና፡ባመለኳቸው፥በተከተሏቸውና፡በፈለጓቸው፥በሰገዱላቸውም፡በፀሓይና፡በጨረቃ፡በሰማይም፡ ሰራዊት፡ዅሉ፡ፊት፡ይዘረጓቸዋል፤አያከማቿቸውም፡አይቀብሯቸውምም፥በምድርም፡ፊት፡ላይ፡እንደ፡ጕድፍ፡ ይኾናሉ።

3እኔም፡ባሳደድዃቸው፡ስፍራ፡ዅሉ፡የቀሩ፥ከዚች፡ክፉ፡ወገን፡የተረፉ፡ቅሬታዎች፡ዅሉ፥ከሕይወት፡ ይልቅ፡ሞትን፡ይመርጣሉ።

4እንዲህም፡ትላቸዋለኽ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የወደቁ፡አይነሡምን፧የሳተስ፡አይመለስምን፧

5እንግዲህ፡ይህ፡የኢየሩሳሌም፡ሕዝብ፡ዘወትር፡ስለ፡ምን፡ወደ፡ዃላው፡ይመለሳል፧ተንኰልን፡ይዟል፡ ሊመለስም፡እንቢ፡ብሏል።

6አደመጥኹ፡ሰማኹም፤ቅንን፡ነገር፡አልተናገሩም፤ማናቸውንም፦ምን፡አድርጌያለኹ፧ብሎ፡ከክፋቱ፡ ንስሓ፡የገባ፡የለም፤ወደ፡ሰልፍም፡እንደሚሮጥ፡ፈረስ፡እያንዳንዱ፡በየመንገዱ፡ይኼዳል።

7ሽመላ፡በሰማይ፡ጊዜዋን፡ዐውቃለች፤ዋኖስና፡ጨረባ፡ዋልያም፡የመምጣታቸውን፡ጊዜ፡ይጠብቃሉ፤ሕዝቤ፡ ግን፡የእግዚአብሔርን፡ፍርድ፡አላወቁም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

8እናንተስ።ጥበበኛዎች፡ነን፡የእግዚአብሔርም፡ሕግ፡ከእኛ፡ጋራ፡ነው፡እንዴት፡ትላላችኹ፧እንሆ፥የጸሓፊ፡ ብርዕ፡ሐሰተኛ፡ነው፥በሐሰትም፡አድርጓል።

9ጥበበኛዎች፡ዐፍረዋል፥ደንግጠውማል፥ተማርከውማል፤እንሆ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ጥለዋል፤ምን፡ ዐይነት፡ጥበብ፡አላቸው፧

10ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ዅሉ፡ሥሥትን፡ያስባሉና፥ከነቢዩም፡ዠምሮ፡እስከ፡ካህኑ፡ድረስ፡ ዅሉ፡በተንኰል፡ያደርጋሉና፡ስለዚህ፡ሚስቶቻቸውን፡ለሌላዎች፥ዕርሻቸውንም፡ለሚወርሱባቸው፡እሰጣለኹ።

11የሕዝቤንም፡ሴት፡ልጅ፡ስብራት፡በጥቂቱ፡ይፈውሳሉ፤ሰላም፡ሳይኾን፦ሰለም፡ሰላም፡ይላሉ።

12አስጸያፊ፡ነገርን፡ስለ፡ሠሩ፡ዐፍረዋልን፧ምንም፡አላፈሩም፥ዕፍረትንም፡አላወቁም፤ስለዚህ፥ከሚወድቁ፡ ጋራ፡ይወድቃሉ፤በጐበኘዃቸው፡ጊዜ፡ይዋረዳሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

13ፈጽሜ፡አጠፋችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤በወይን፡ላይ፡ፍሬ፥በበለስ፡ዛፍ፡ላይ፡በለስ፡ አይኾንም፥ቅጠልም፡ይረግፋል፤የሚያልፉባቸውንም፡ሰጠዃቸው።

14ዝም፡ብለን፡ለምን፡እንቀመጣለን፧እግዚአብሔርን፡ስለ፡በደልን፡አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ አጥፍቶናልና፥የሐሞትንም፡ውሃ፡አጠጥቶናልና፥ተሰብስባችኹ፡ወደተመሸጉ፡ከተማዎች፡እንግባ፥በዚያም፡ እንጥፋ።

15ሰላምን፡በተስፋ፡ተጠባበቅን፥መልካምም፡አልተገኘም፤መጠገንን፡በተስፋ፡ ተጠባበቅን፥እንሆም፥ድንጋጤ፡ኾነ።

16የፈረሰኛዎቹ፡ድምፅ፡ከዳን፡ተሰማ፤ከዐርበኛዎች፡ፈረሶች፡ማሽካካት፡የተነሣ፡ምድር፡ዅሉ፡ ተንቀጠቀጠች፤መጡም፡ምድሪቱንና፡በርሷም፡ያለውን፡ዅሉ፥ከተማዪቱንና፡የተቀመጡባትንም፡በሉ።

17እንሆ፥አስማት፡የማይከለክላቸውን፡እባቦችንና፡እፍኝቶችን፡እሰድ፟ባ፟ችዃለኹ፤እነርሱም፡ይነድፏችዃል።

18ሐዘኔ፡የማይጽናና፡ነው፥ልቤም፡በውስጤ፡ደክሟል።

19እንሆ፦እግዚአብሔር፡በጽዮን፡የለምን፧ወይስ፡ንጉሧ፡በርሷ፡ዘንድ፡የለምን፧የሚል፡የወገኔ፡ሴት፡ ልጅ፡ጩኸት፡ድምፅ፡ከሩቅ፡አገር፡ተሰማ።በተቀረጹ፡ምስሎቻቸውና፡በባዕድ፡ከንቱነትስ፡ያስቈጡኝ፡ስለ፡ ምንድር፡ነው፧

20መከሩ፡ዐልፏል፥በጋው፡ኼዷል፥እኛም፡አልዳን፟ም።

21በሕዝቤ፡ሴት፡ልጅ፡ስብራት፡እኔ፡ተሰብሬያለኹ፡ጠቍሬማለኹ፤አድናቆትም፡ይዞኛል።

22በገለዓድ፡የሚቀባ፡መድኀኒት፡የለምን፧ወይስ፡በዚያ፡ሐኪም፡የለምን፧የወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡ፈውስ፡ስለ፡ ምን፡አልኾነም፧

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source