Skip to content
← Jeremiah

Chapter 7 · Amharic

Jeremiah

1ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡ኤርምያስ፡የመጣ፡ቃል፡ይህ፡ነው፦ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

2በእግዚአብሔር፡ቤት፡በር፡ቁም፥ይህንም፡ቃል፡እንዲህ፡ብለኽ፡ተናገር፦እግዚአብሔርን፡ልታመልኩ፡ በእነዚህ፡በሮች፡የምትገቡ፡ከይሁዳ፡ያላችኹ፡ዅሉ፥የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ስሙ።

3የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡አሳምሩ፡በዚህም፡ስፍራ፡ አሳድራችዃለኹ።

4የእግዚአብሔር፡መቅደስ፥የእግዚአብሔር፡መቅደስ፥የእግዚአብሔር፡መቅደስ፡ይህ፡ነው፡እያላችኹ፡ በሐሰት፡ቃል፡አትታመኑ።

5መንገዳችኹንና፡ሥራችኹን፡ፈጽማችኹ፡ብታሳምሩ፥በሰውና፡በጎረቤቱ፡መካከል፡ቅን፡ፍርድ፡ብትፈርዱ፥

6መጻተኛውንና፡ድኻ፡አደጉን፡መበለቲቱንም፡ባትገፉ፥በዚህም፡ስፍራ፡ንጹሕ፡ደምን፡ባታፈሱ፟፥ክፉም፡ ሊኾንባችኹ፡እንግዳዎችን፡አማልክት፡ባትከተሉ፥

7ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፡ለአባቶቻችኹ፡በሰጠዃቸው፡ምድር፡በዚህ፡ስፍራ፡አሳድራችዃለኹ።

8እንሆ፥በማትረቡበት፡በሐሰት፡ቃል፡ታምናችዃል።

9ትሰርቃላችኹ፥ትገድላላችኹ፥ታመነዝራላችኹ፥በሐሰትም፡ትምላላችኹ፥ለበዓልም፡ ታጥናላችኹ፥የማታውቋቸውንም፡እንግዳዎች፡አማልክት፡ትከተላላችኹ፤

10መጣችኹም፥ስሜም፡በተጠራበት፡በዚህ፡ቤት፡በፊቴ፡ቆማችኹ፦ይህን፡አስጸያፊ፡የኾነ፡ነገርን፡ዅሉ፡ አላደረግንም፡አላችኹ።

11ይህስ፡ስሜ፡የተጠራበት፡ቤት፡በዐይናችኹ፡የሌቦች፡ዋሻ፡ኾኗልን፧እንሆ፥እኔ፡አይቻለኹ፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

12ነገር፡ግን፥በቀድሞ፡ዘመን፡ስሜን፡ወዳሳደርኹበት፡በሴሎ፡ወደነበረው፡ስፍራዬ፡ኺዱ፥ከሕዝቤም፡ ከእስራኤል፡ክፋት፡የተነሣ፡ያደረግኹበትን፡እዩ።

13አኹንም፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ስላደረጋችኹ፥በማለዳም፡ተነሥቼ፡በተናገርዃችኹ፡ጊዜ፡ ስላልሰማችኹ፥በጠራዃችኹም፡ጊዜ፡ስላልመለሳችኹ፥

14ስለዚህ፥በሴሎ፡እንዳደረግኹ፡እንዲሁ፥ስሜ፡በተጠራበት፥በምትታመኑበት፡ቤት፥ለእናንተና፡ ለአባቶቻችኹም፡በሰጠዃችኹ፡ስፍራ፡አደርጋለኹ።

15የኤፍሬምንም፡ዘር፡ዅሉ፥ወንድሞቻችኹን፡ዅሉ፡እንደ፡ጣልኹ፥እንዲሁ፡ከፊቴ፡እጥላችዃለኹ።

16እንግዲህም፡አልሰማኽምና፡ስለዚህ፡ሕዝብ፡አትጸልይ፡ስለ፡እነርሱም፡ልመናና፡ጸሎት፡ አታድርግ፤አትማልድላቸው።

17እነርሱስ፡በይሁዳ፡ከተማዎች፡ውስጥና፡በኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡ላይ፡የሚያደርጉትን፡አታይምን፧

18ያስቈጡኝ፡ዘንድ፥ለሰማይ፡ንግሥት፡ዕንጐቻ፡እንዲያደርጉ፡ለሌላዎችም፡አማልክት፡የመጠጥ፡ቍርባን፡ እንዲያፈሱ፟፡ልጆች፡ዕንጨት፡ይሰበስባሉ፥አባቶችም፡እሳት፡ያነዳ፟ሉ፥ሴቶችም፡ዱቄት፡ይለውሳሉ።

19እኔን፡ያስቈጣሉን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ለፊታቸውስ፡ዕፍረት፡አይደለምን፧

20እንግዲህም፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ቍጣዬና፡መዓቴ፡በዚህ፡ስፍራ፡ላይ፥በሰውና፡ በእንስሳ፡ላይ፥በዱር፡ዛፎችና፡በምድር፡ፍሬ፡ላይ፡ይፈሳ፟ል፤ይነዳ፟ል፥አይጠፋምም።

21እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ለሌላ፡መሥዋዕታችኹ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታችኹን፡ ጨምሩ፥ሥጋውንም፡ብሉ።

22ከግብጽ፡ምድር፡ባወጣዃችኹ፡ቀን፡ስለሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡ስለ፡ሌላ፡መሥዋዕት፡ለአባቶቻችኹ፡ አልተናገርኹምና፥አላዘዝዃቸውምም።

23ነገር፡ግን፦ቃሌን፡ስሙ፥እኔም፡አምላክ፡እኾናችዃለኹ፡እናንተም፡ሕዝብ፡ትኾኑኛላችኹ፤መልካምም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይኾንላችኹ፡ዘንድ፡ባዘዝዃችኹ፡መንገድ፡ዅሉ፡ኺዱ፡ብዬ፡በዚህ፡ነገር፡አዘዝዃቸው።

24ነገር፡ግን፥በክፉ፡ልባቸው፡ዐሳብና፡እልከኝነት፡ኼዱ፡ወደ፡ፊትም፡ሳይኾን፡ወደ፡ዃላቸው፡ኼዱ፡ እንጂ፡አልሰሙም፡ዦሯቸውንም፡አላዘነበሉም።

25አባቶቻችኹ፡ከግብጽ፡ምድር፡ከወጡበት፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፥በየዕለቱ፡እየማለድኹ፡ ባሪያዎቼን፡ነቢያትን፡ዅሉ፡ልኬባችኹ፡ነበር።

26ነገር፡ግን፥ዐንገታቸውን፡አደነደኑ፡እንጂ፡አልሰሙኝም፡ዦሯቸውንም፡አላዘነበሉም፤አባቶቻቸውም፡ ካደረጉት፡ይልቅ፡የባሰ፡አደረጉ።

27በዚህም፡ቃል፡ዅሉ፡ትነግራቸዋለኽ፥ነገር፡ግን፥አይሰሙኽም፤ትጠራቸውማለኽ፥ነገር፡ ግን፥አይመልሱልኽም።

28አንተም፦የአምላኩን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ያልሰማ፥ተግሣጽንም፡ያልተቀበለ፡ሕዝብ፡ይህ፡ ነው፤እውነት፡ጠፍቷል፡ከአፋቸውም፡ተቈርጧል፡ትላቸዋለኽ።

29እግዚአብሔር፡የቍጣውን፡ትውልድ፡ጥሏልና፥ትቶታልምና፡ጠጕርሽን፡ቍረጪ፥ጣዪውም፥በወናዎች፡ ኰረብታዎችም፡ላይ፡አሙሺ።

30የይሁዳ፡ልጆች፡በፊቴ፡ክፉን፡ነገር፡ሠርተዋል፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ያረክሱትም፡ዘንድ፡ስሜ፡ በተጠራበት፡ቤት፡ርኵሰታቸውን፡አኑረዋል።

31እኔም፡ያላዘዝኹትንና፡በልቤ፡ያላሰብኹትን፥ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆቻቸውን፡በእሳት፡ያቃጥሉ፡ዘንድ፡ በሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ያለችውን፡የቶፌትን፡መስገጃዎች፡ሠረተዋል።

32ስለዚህ፥እንሆ፥ስፍራ፡ከማጣት፡የተነሣ፡በቶፌት፡ይቀበራሉና፡የዕርድ፡ሸለቆ፡ይባላል፡እንጂ፡ቶፌት፡ ወይም፡የሄኖም፡ልጅ፡ሸለቆ፡ዳግመኛ፡የማይባልበት፡ዘመን፡ይመጣል፥ይላል፡እግዚአብሔር።

33የዚህም፡ሕዝብ፡ሬሳ፡ለሰማይ፡ወፎችና፡ለምድር፡አራዊት፡መብል፡ይኾናል፥የሚያስፈራራቸውም፡የለም።

34ምድሪቱም፡ባድማ፡ትኾናለችና፡ከይሁዳ፡ከተማዎችና፡ከኢየሩሳሌም፡አደባባይ፡የእልልታን፡ድምፅና፡ የደስታን፡ድምፅ፥የወንድ፡ሙሽራን፡ድምፅና፡የሴት፡ሙሽራን፡ድምፅ፡አጠፋለኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source