Skip to content
← Jeremiah

Chapter 6 · Amharic

Jeremiah

1እናንተ፡የብንያም፡ልጆች፥ክፉ፡ነገር፡ታላቅም፡ጥፋት፡ከሰሜን፡ይጐበኛልና፥ከኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡ ሽሹ፥በቴቁሔ፡መለከቱን፡ንፉ፥በቤትሐካሪም፡ላይ፡ምልክት፡አንሡ።

2የተዋበችውንና፡የተሰባቀለችውን፡የጽዮንን፡ልጅ፡አጐሰቍላለኹ።

3እረኛዎችና፡መንጋዎቻቸው፡ወደ፡ርሷ፡ይመጣሉ፥በዙሪያዋም፡ድንኳኖቻቸውን፡ ይተክሉባታል፥እያንዳንዱም፡በስፍራው፡መንጋውን፡ያሰማራል።

4በርሷ፡ላይ፡ሰልፍ፡አዘጋጁ፥ተነሡ፥በቀትርም፡እንውጣ።ቀኑ፡መሽቷልና፥የማታውም፡ጥላ፡ ረዝሟልና፥ወዮልን።

5ተነሡ፡በሌሊትም፡እንውጣ፥አዳራሾቿንም፡እናፍርስ።

6የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላልና፦ዛፎቿን፡ቍረጡ፥በኢየሩሳሌምም፡ላይ፡ዐፈርን፡ ደልድሉ፤ይህች፡ከተማ፡የምትቀሠፍ፡ናት፤መካከሏ፡ዅሉ፡ግፍ፡ብቻ፡ነው።

7በጕድጓድ፡ውሃ፡እንደሚፈልቅ፥እንዲሁ፡ክፋቷ፡ከርሷ፡ዘንድ፡ይፈልቃል፤ግፍና፡ቅሚያ፡በርሷ፡ዘንድ፡ ይሰማል፥ደዌና፡ቍስልም፡ዅልጊዜ፡በፊቴ፡አለ።

8ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ነፍሴ፡ከአንቺ፡እንዳትለይ፥አንቺንም፡ባድማና፡ወና፡እንዳላደርግሽ፥ተግሣጽን፡ተቀበዪ።

9እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሰው፡ወይኑን፡እንደሚቃርም፥እንዲሁ፡ከእስራኤል፡የቀሩትን፡ፈጽሞ፡ ይቃርሟቸዋል፤እጅኽንም፡እንደ፡ለቃሚ፡ወደ፡እንቅብ፡ዘርጋ።

10ይሰሙኝስ፡ዘንድ፡ለማን፡እናገራለኹ፧ለማንስ፡አስጠነቅቃለኹ፧እንሆ፥ዦሯቸው፡ያልተገረዘች፡ናት፡ ለመስማትም፡አይችሉም፤እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ለስድብ፡ኾኖባቸዋል፥ደስም፡አያሠኛቸውም።

11ስለዚህ፥በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ተሞልቻለኹ፤ከመታገሥ፡ደክሜያለኹ፤በሜዳ፡በሕፃናት፡ላይ፡ በጕልማሳዎችም፡ጉባኤ፡ላይ፡በአንድነት፡አፍሰ፟ው፤ባል፡ከሚስቱ፡ጋራ፡ሽማግሌውም፡ከጐበዙ፡ጋራ፡ ይያያዛልና። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

12እጄን፡በምድር፡በሚኖሩ፡ላይ፡እዘረጋለኹና፥ቤቶቻቸው፡ዕርሻዎቻቸውም፡ሴቶቻቸውም፡በአንድነት፡ ለሌላዎች፡ይኾናሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

13ከታናሹ፡ዠምሮ፡እስከ፡ታላቁ፡ድረስ፡ዅሉ፡ሥሥትን፡ያስባሉና፥ከነቢዩም፡ዠምሮ፡እስከ፡ካህኑ፡ድረስ፡ ዅሉ፡በተንኰል፡ያደርጋሉና።

14የሕዝቤንም፡ስብራት፡በጥቂቱ፡ይፈውሳሉ፤ሰላም፡ሳይኾን፦ሰላም፡ሰላም፡ይላሉ።

15ርኩስን፡ነገር፡ስለ፡ሠሩ፡ዐፍረዋልን፧ምንም፡አላፈሩም፥ዕፍረትንም፡አላወቁም፤ስለዚህ፥ከሚወድቁ፡ ጋራ፡ይወድቃሉ፤በጐበኘዃቸው፡ጊዜ፡ይዋረዳሉ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

16እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በመንገድ፡ላይ፡ቁሙ፡ተመልከቱም፥የቀደመችውንም፡መንገድ፡ ጠይቁ፤መልካሚቱ፡መንገድ፡ወዴት፡እንደ፡ኾነች፡ዕወቁ፥በርሷም፡ላይ፡ኺዱ፥ለነፍሳችኹም፡ዕረፍት፡ ታገኛላችኹ፤እነርሱ፡ግን፦አንኼድባትም፡አሉ።

17እኔም፦የመለከቱን፡ድምፅ፡አድምጡ፡ብዬ፡ጠባቂዎችን፡ሾምኹባችኹ፤እነርሱ፡ግን፦አናደምጥም፡ አሉ።

18አሕዛብ፡ሆይ፥ስለዚህ፡ስሙ፤ማኅበር፡ሆይ፥እነዚያ፡የሚያገኛቸውን፡ዕወቁ።

19ምድር፡ሆይ፥ስሚ፤እንሆ፥ቃሌን፡ስላልሰሙ፥ሕጌንም፡ስለ፡ጣሉ፥በዚህ፡ሕዝብ፡ላይ፡የዐሳባቸውን፡ ፍሬ፥ክፉን፡ነገር፡አመጣባቸዋለኹ።

20ስለ፡ምንስ፡ከሳባ፡ዕጣንን፥ከሩቅም፡አገር፡ቀረፋን፡ታቀርቡልኛላችኹ፧የሚቃጠለውን፡መሥዋዕታችኹን፡ አልቀበለውም፡ሌላ፡መሥዋዕታችኹም፡ደስ፡አያሠኘኝም።

21ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ከዚህ፡ሕዝብ፡ፊት፡ዕንቅፋቶችን፡አደርጋለኹ፤አባቶችና፡ ልጆች፡በአንድነት፡ይሰናከሉባቸዋል፥ጎረቤትና፡ባልንጀራም፡ይጠፋሉ።

22እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥ሕዝብ፡ከሰሜን፡አገር፡ይመጣል፥ታላቅ፡ሕዝብም፡ከምድር፡ ዳርቻ፡ይነሣል።

23ቀስትንና፡ጦርን፡ይይዛሉ፤ጨካኞች፡ናቸው፥ምሕረትንም፡አያደርጉም፤ድምፃቸው፡እንደ፡ባሕር፡ ይተማ፟ል፥በፈረሶችም፡ላይ፡ይቀመጣሉ፤የጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ለሰልፍ፡እንደ፡ተዘጋጀ፡ሰው፡ እያንዳንዳቸው፡ባንቺ፡ላይ፡ተሰለፉ።

24ወሬውን፡ሰምተናል፥እጃችን፡ደክማለች፤ምጥ፡ወላድን፡ሴት፡እንደሚይዛት፡ጭንቀት፡ይዞናል።

25የጠላት፡ሰይፍና፡ድንጋጤ፡ከበ፟ዋችዃልና፥ወደ፡ሜዳ፡አትውጡ፡በምንገድም፡ላይ፡አትኺዱ።

26የሕዝቤ፡ልጅ፡ሆይ፥ማቅ፡ልበሺ፡በዐመድም፡ውስጥ፡ተንከባለዪ፤አጥፊ፡በላያችን፡በድንገት፡ ይመጣብናልና፥ለአንድያ፡ልጅ፡እንደሚደረግ፡ልቅሶ፥መራራ፡ልቅሶ፡አልቅሺ።

27መንገዳቸውን፡እንድታውቅና፡እንድትፈትን፡በሕዝቤ፡መካከል፡ፈታኝ፡አድርጌኻለኹ።

28እነርሱ፡ዅሉ፡እጅግ፡ዐመፀኛዎች፡ናቸው፤በጠማማነት፡ይኼዳሉ፤ናስና፡ብረት፡ናቸው፤ዅሉ፡ ርኵሰትን፡ያደርጋሉ።

29ወናፍ፡አናፋ፡ርሳሱም፡በእሳት፡ቀለጠ፤አንጥረኛውም፡መልሶ፡በከንቱ፡ያቀልጠዋል፤ኀጢአተኛዎች፡ አልተወገዱም።

30እግዚአብሔር፡ጥሏቸዋልና፥የተጣለ፡ብር፡ብለው፡ይጠሯቸዋል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source