Skip to content
← Jeremiah

Chapter 5 · Amharic

Jeremiah

1በኢየሩሳሌም፡መንገድ፡እየተመላለሳችኹ፡ሩጡ፥ተመልከቱም፥ዕወቁም፥በአደባባይዋም፡ፈልጉ፤ፍርድን፡ የሚያደርገውን፡እውነትንም፡የሚሻውን፡ሰው፡ታገኙ፡እንደ፡ኾነ፡ይቅር፡እላታለኹ።

2እነርሱም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ቢሉ፡የሚምሉት፡በሐሰት፡ነው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3አቤቱ፥ዐይንኽ፡እውነትን፡የምትመለከት፡አይደለችምን፧አንተ፡ቀሥፈኻቸዋል፥ነገር፡ ግን፥አላዘኑም፥ቀጥቅጠኻቸውማል፥ነገር፡ግን፥ተግሣጽን፡እንቢ፡አሉ፤ፊታቸውን፡ከድንጋይ፡ይልቅ፡ አጠንክረዋል፤ይመለሱ፡ዘንድ፡እንቢ፡አሉ።

4እኔም፦የእግዚአብሔርን፡መንገድና፡የአምላካቸውን፡ሕግ፡አላወቁምና፡እነዚህ፡በእውነት፡ድኻዎችና፡ ሰነፎች፡ናቸው፤

5ወደ፡ታላላቆቹ፡እኼዳለኹ፡እናገራቸውማለኹ፤የእግዚአብሔርን፡መንገንድና፡የአምላካቸውን፡ሕግ፡ ያውቃሉና፡አልኹ።እነዚህ፡ግን፡ቀንበሩን፡በአንድነት፡ሰብረዋል፥እስራቱንም፡ቈርጠዋል።

6ስለዚህ፥ኀጢአታቸው፡በዝቷልና፥የክዳታቸውም፡ብዛት፡ጸንቷልና፤ስለዚህ፥አንበሳ፡ከዱር፡ወጥቶ፡ ይሰብራቸዋል፥የበረሓም፡ተኵላ፡ያጠፋቸዋል፥ነብርም፡በከተማዎቻቸው፡ላይ፡ይተጋል፥ከዚያም፡የሚወጣ፡ ዅሉ፡ይነጠቃል።

7በእነዚህ፡ነገሮች፡ይቅር፡የምልሽ፡እንዴት፡አድርጌ፡ነው፧ልጆችሽ፡ትተውኛል፡አማልክትም፡ባልኾኑ፡ ምለዋል፤ካጠገብዃቸውም፡በዃላ፡አመነዘሩ፡በጋለሞታዎቹም፡ቤት፡ተሰበሰቡ።

8እንደ፡ተቀለቡ፡ፈረሶች፡ኾኑ፤እያንዳንዳቸውም፡ከባልንጀራዎቻቸው፡ሚስቶች፡ዃላ፡አሽካኩ።

9በእውኑ፡ስለ፡እነዚህ፡ነገሮች፡አልቀሥፍምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ነፍሴስ፡እንደዚህ፡ባለ፡ሕዝብ፡ላይ፡ አትበቀልምን፧

10ወደ፡ቅጥሯ፡ወጥታችኹ፡አፍርሱ፥ነገር፡ግን፥ፈጽማችኹ፡አታጥፉ፤ለእግዚአብሔር፡አይደሉምና፡ ቅርንጫፏን፡ውሰዱ።

11የእስራኤል፡ቤትና፡የይሁዳ፡ቤት፡በእኔ፡ላይ፡እጅግ፡ወንጅለዋል፡ይላል፡እግዚአብሔር።

12እነርሱም፦ርሱ፡አይደለም፥ክፉ፡ነገርም፡አይመጣብንም፡ሰይፍንና፡ራብንም፡አናይም፤ነቢያትም፡ነፋስ፡ ይኾናሉ፥

13የእግዚአብሔርም፡ቃል፡በእነርሱ፡ዘንድ፡የለም፥እንዲህም፡ይደረግባቸዋል፡ብለው፡እግዚአብሔርን፡ ክደዋል።

14ስለዚህም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦በዚህ፡ቃል፡ተናግራችዃልና፥እንሆ፥በአፍኽ፡ ውስጥ፡ቃሌን፡እሳት፡ይህንም፡ሕዝብ፡ዕንጨት፡አደርጋለኹ፥ትበላቸውማለች።

15የእስራኤል፡ቤት፡ሆይ፥እንሆ፥ሕዝብን፡ከሩቅ፡አመጣባችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤ኀያል፡ጥንታዊ፡ ሕዝብ፡ነው፥ቋንቋቸውንም፡የማታውቀው፡የሚናገሩትንም፡የማታስተውለው፡ሕዝብ፡ነው።

16የፍላጻቸውም፡ሰገባ፡እንደ፡ተከፈተ፡መቃብር፡ነው፥ዅሉም፡ኀያላን፡ናቸው።

17መከርኽንና፡እንጀራኽን፡ይበላሉ፤ወንዶችና፡ሴቶች፡ልጆችኽንም፡ይበሏቸዋል፤በጎችኽንና፡ላሞችኽንም፡ ይበላሉ፤ወይንኽንና፡በለስኽንም፡ይበላሉ፤የምትታመናቸውን፡የተመሸጉ፡ከተማዎችን፡በሰይፍ፡ይደበድባሉ።

18ነገር፡ግን፥በዚያ፡ዘመን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ፈጽሜ፡አላጠፋችኹም።

19እንዲህም፡ይኾናል፤እናንተ፦አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ስለ፡ምን፡ አደረገብን፧ብትሉ፥አንተ፦እንደ፡ተዋችኹኝ፡በአገራችኹም፡ሌላዎችን፡አማልክት፡እንዳመለካችኹ፥እንዲሁ፡ ለእናንተ፡ባልኾነ፡አገር፡ለሌላዎች፡ሰዎች፡ትገዛላችኹ፡ትላቸዋለኽ።

20ይህን፡በያዕቆብ፡ቤት፡አውሩ፥በይሁዳም፡አሰሙ።

21እናንተ፡ሰነፎች፡ልበ፡ቢሶች፥ዐይን፡እያላችኹ፡የማታዩ፥ዦሮም፡እያላችኹ፡የማትሰሙ፡ሕዝብ፡ ሆይ፥ይህን፡ስሙ።

22በእውኑ፡እኔን፡አትፈሩምን፧ከፊቴስ፡አትደነግጡምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤እንዳያልፍ፡አሸዋን፡ በዘለዓለም፡ትእዛዝ፡ለባሕር፡ዳርቻ፡አድርጌያለኹ፤ሞገዱም፡ቢናወጥ፡አያሸንፍም፥ቢጮኽም፡አያልፍበትም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

23ለዚህ፡ሕዝብ፡ግን፡የሸፈተና፡ያመፀ፡ልብ፡አላቸው፤ዐምፀዋል፥ኼደውማል።

24በልባቸውም፦የፊተኛውንና፡የዃለኛውን፡ዝናብ፡በጊዜው፡የሚሰጠውን፥ለመከርም፡የተመደቡትን፡ ወራት፡የሚጠብቅልንን፡አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡እንፍራ፡አላሉም።

25በደላችኹ፡እነዚህን፡አስቀርታለች፥ኀጢአታችኹም፡መልካምን፡ነገር፡ከለከለቻችኹ።

26በሕዝቤ፡መካከል፡ክፉዎች፡ሰዎች፡ተገኝተዋል፤እንደ፡አጥማጆችም፡ያደባሉ፥ወጥመድንም፡ይዘረጋሉ፡ ሰዎችንም፡ያጠምዳሉ።

27ቀፎ፡ወፎችን፡እንደሚሞላ፥እንዲሁ፡ቤታቸው፡ሽንገላን፡ሞልታለች፤እንዲሁም፡ከብረዋል፡ባለጠጋዎችም፡ ኾነዋል።

28ወፍረዋል፡ሰብተውማል፥ክፋታቸውንም፡ያለልክ፡አብዝተዋል፤የድኻ፡አደጎች፡ነገር፡መልካም፡እንዲኾን፡ አልተሟገቱላቸውም፥የችግረኛዎችንም፡ፍርድ፡አልፈረዱላቸውም።

29በእውኑ፡ስለ፡እነዚህ፡ነገሮች፡አልቀሥፍምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ነፍሴስ፡እንደዚህ፡ባለ፡ሕዝብ፡ላይ፡ አትበቀልምን፧

30የምታስደንቅና፡የምታስደነግጥ፡ነገር፡በምድር፡ላይ፡ኾናለች፤

31ነቢያት፡በሐሰት፡ትንቢት፡ይናገራሉ፥ካህናትም፡በእነዚህ፡እጅ፡ይገዛሉ፥ሕዝቤም፡እንዲህ፡ያለውን፡ነገር፡ ይወዳ፟ሉ፤በፍጻሜውስ፡ምን፡ታደርጋላችኹ፧

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source