1አቤቱ፥ከአንተ፡ጋራ፡በተሟገትኹ፡ጊዜ፡አንተ፡ጻድቅ፡ነኽ፤ነገር፡ግን፥ከአንተ፡ጋራ፡ስለ፡ፍርድ፡ ልናገር።የኀጢአተኛዎች፡መንገድ፡ስለ፡ምን፡ይቃናል፧በደልንስ፡ለሚያደርጉ፡ዅሉ፡ስለ፡ምን፡ደኅንነት፡ ይኾናል፧
2ተክለኻቸዋል፤ሥር፡ሰደ፟ዋል፤አድገዋል፡አፍርተውማል፤በአፋቸው፡አንተ፡ቅርብ፡ነኽ፥ከልባቸው፡ግን፡ ሩቅ፡ነኽ።
3አንተ፡ግን፥አቤቱ፥ዐውቀኸኛል፤አይተኸኛል፥ልቤንም፡በፊትኽ፡ፈትነኻል፤እንደ፡በጎች፡ለመታረድ፡ ጐትተኽ፡ለያቸው፥ለመታረድም፡ቀን፡አዘጋጃቸው።
4ምድሪቱ፡የምታለቅሰው፥የአገሩ፡ሣርስ፡ዅሉ፡የሚደርቀው፡እስከ፡መቼ፡ነው፧የተቀመጡባት፡ ሰዎች፦ፍጻሜያችንን፡አያይም፡ብለዋልና፥ስለ፡ክፋታቸው፡እንስሳዎችና፡ወፎች፡ጠፍተዋል።
5ከእግረኛዎች፡ጋራ፡በሮጥኽ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ቢያደክሙኽ፥ከፈረሶች፡ጋራ፡መታገል፡እንዴት፡ ትችላለኽ፧በሰላምም፡ምድር፡ታምነኽ፡ብትቀመጥ፥በዮርዳኖስ፡ትዕቢት፡እንዴት፡ታደርጋለኽ፧
6ወንድሞችኽና፡የአባትኽ፡ቤት፡እነርሱ፡ጭምር፡አታለ፟ውኻልና፥በዃላኽም፡ጮኸዋልና፤በመልካምም፡ ቢናገሩኽም፡አትታመናቸው።
7ቤቴን፡ትቻለኹ፡ርስቴንም፡ጥያለኹ፥ነፍሴም፡የምትወዳ፟ትን፡በጠላቶቿ፡እጅ፡አሳልፌ፡ሰጥቻለኹ።
8ርስቴ፡በዱር፡እንዳለ፡አንበሳ፡ኾናብኛለች፤ድምፇን፡አንሥታብኛለች፤ስለዚህ፥ጠልቻታለኹ።
9ርስቴ፡እንደ፡ዝንጕርጕር፡አሞራ፡ኾነችብኝን፧አሞሮችስ፡በዙሪያዋና፡በላይዋ፡ኾነዋልን፧ኺዱ፥የምድር፡ አራዊትን፡ዅሉ፡ሰብስቡ፥ይበሉም፡ዘንድ፡አምጧቸው።
10ብዙ፡እረኛዎች፡የወይኑን፡ቦታዬን፡አጥፍተዋል፥ዕድል፡ፈንታዬንም፡ረግጠዋል፤የአምሮቴን፡ዕድል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ፈንታ፡ምድረ፡በዳ፡አድርገውታል።
11ባድማ፡አድርገውታል፥ፈርሶም፡ወደ፡እኔ፡ያለቅሳል፤ምድር፡ዅሉ፡ባድማ፡ኾናለች፡በልቡም፡የሚያስባት፡ የለም።
12በወናዎች፡ኰረብታዎች፡ዅሉ፡ላይ፡በዝባዦች፡መጥተዋል፥የእግዚአብሔር፡ሰይፍ፡ከምድር፡ዳር፡ ዠምሮ፡እስከምድር፡ዳር፡ድረስ፡ይበላልና፤ለሥጋ፡ለባሽ፡ዅሉ፡ሰላም፡የለም።
13ስንዴን፡ዘሩ፡ሾኽንም፡ዐጨዱ፤ደከሙ፥ምንም፡አልረባቸውም፤ስለእግዚአብሔር፡ጽኑ፡ቍጣ፡ ከፍሬያችኹ፡ታፍራላችኹ።
14እግዚአብሔር፡ለሕዝቤ፡ለእስራኤል፡ያወረስኹትን፡ርስት፡ለሚነኩት፡ክፉዎች፡ጎረቤቶች፡ዅሉ፡እንዲህ፡ ይላልና፦እንሆ፥ከምድራቸው፡እነቅላቸዋለኹ፥የይሁዳንም፡ቤት፡ከመካከላቸው፡እነቅለዋለኹ።
15ከነቀልዃቸውም፡በዃላ፡መልሼ፡እምራቸዋለኹ፥እያንዳንዱንም፡ወደ፡ርስቱ፡እያንዳንዱንም፡ወደ፡ምድሩ፡ እመልሳለኹ።
16በበዓል፡ይምሉ፡ዘንድ፡ሕዝቤን፡እንዳስተማሩ፡በስሜ፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ብለው፡ይምሉ፡ዘንድ፡ የሕዝቤን፡መንገድ፡በትጋት፡ቢማሩ፥በዚያን፡ጊዜ፡በሕዝቤ፡መካከል፡ይመሠረታሉ።
17ባይሰሙኝ፡ግን፡ያንን፡ሕዝብ፡ፈጽሜ፡እነቅለዋለኹ፡አጠፋውማለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።