Skip to content
← Jeremiah

Chapter 13 · Amharic

Jeremiah

1እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይለኛል፦ኺድ፥ከተልባ፡እግር፡የተሠራችን፡መታጠቂያ፡ለአንተ፡ ግዛ፥ወገብኽንም፡ታጠቅባት፤በውሃውም፡ውስጥ፡አትንከራት።

2እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡መታጠቂያን፡ገዛኹ፡ወገቤንም፡ታጠቅኹባት። 3-

4ኹለተኛም፡ጊዜ፦የገዛኻትን፡በወገብኽ፡ያለችውን፡መታጠቂያ፡ወስደኽ፡ተነሥ፥ወደ፡ኤፍራጥስም፡ ኺድ፥በዚያም፡በተሰነጠቀ፡አለት፡ውስጥ፡ሸሽጋት፡የሚል፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡መጣልኝ።

5እግዚአብሔርም፡እንዳዘዘኝ፡ኼድኹ፡በኤፍራጥስም፡አጠገብ፡ሸሸግዃት።

6ከብዙ፡ቀንም፡በዃላ፡እግዚአብሔር፦ተነሥተኽ፡ወደ፡ኤፍራጥስ፡ኺድ፥በዚያም፡ትሸሽጋት፡ዘንድ፡ ያዘዝኹኽን፡መታጠቂያ፡ከዚያ፡ውስጥ፡ውሰድ፡አለኝ።

7እኔም፡ወደ፡ኤፍራጥስ፡ኼድኹ፡ቈፈርኹም፥ከሸሸግኹበትም፡ስፍራ፡መታጠቂያዪቱን፡ ወሰድኹ።እንሆም፥መታጠቂያዪቱ፡ተበላሽታ፡ነበር፥ለምንም፡አልረባችም።

8የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደ፡እኔ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፤

9እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንዲሁ፡የይሁዳን፡ትዕቢት፡ታላቁንም፡የኢየሩሳሌምን፡ትዕቢት፡ አበላሻለኹ።

10ቃሌን፡ይሰሙ፡ዘንድ፡እንቢ፡የሚሉ፥በልባቸውም፡እልከኝነት፡የሚኼዱ፥ያመልኳቸውና፡ይሰግዱላቸው፡ ዘንድ፡ሌላዎችን፡አማልክት፡የሚከተሉ፡እነዚህ፡ክፉ፡ሕዝብ፡አንዳች፡እንዳማትረባ፡እንደዚች፡መታጠቂያ፡ ይኾናሉ።

11መታጠቂያ፡በሰው፡ወገብ፡ላይ፡እንደምትጣበቅ፥እንዲሁ፡ሕዝብና፡ስም፡ምስጋናና፡ክብር፡ይኾኑልኝ፡ ዘንድ፡የእስራኤልን፡ቤት፡ዅሉ፡የይሁዳንም፡ቤት፡ዅሉ፡ከእኔ፡ጋራ፡አጣብቄያለኹ፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤ነገር፡ግን፥አልሰሙም።

12ስለዚህ፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ማድጋ፡ዅሉ፡የወይን፡ጠጅ፡ይሞላል፡ ብለኽ፡ትነግራቸዋለኽ፤እነርሱም፦ማድጋ፡ዅሉ፡የወይን፡ጠጅ፡እንዲሞላ፡በእውኑ፡እኛ፡ አናውቅምን፧ይሉኻል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13አንተም፡እንዲህ፡ትላቸዋለኽ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በዚች፡ምድር፡የሚኖሩትን፡ ዅሉ፥በዳዊት፡ዙፋን፡የሚቀመጡትን፡ነገሥታት፡ካህናቱንም፡ነቢያቱንም፡በኢየሩሳሌምም፡የተቀመጡትን፡ዅሉ፡ በስካር፡እሞላቸዋለኹ።

14ሰውንም፡በሰው፡ላይ፥አባቶችንና፡ልጆችን፡ባንድ፡ላይ፥እቀጠቅጣለኹ፥ይላል፡ እግዚአብሔር፤አጠፋቸዋለኹ፡እንጂ፡አልራራም፥አላዝንም፥አልምርም።

15ስሙ፥አድምጡ፤እግዚአብሔር፡ተናግሯልና፥አትታበዩ።

16ሳትጨልም፡እግራችኹም፡በጨለመችው፡ተራራ፡ላይ፡ሳትሰናከል፥በተስፋ፡የምትጠባበቁትን፡ብርሃን፡ ለሞት፡ጥላና፡ለድቅድቅ፡ጨለማ፡ሳይለውጠው፡ለአምላካችኹ፡ለእግዚአብሔር፡ክብርን፡ስጡ።

17ይህን፡ባትሰሙ፡ነፍሴ፡ስለ፡ትዕቢታችኹ፡በስውር፡ታለቅሳለች፤የእግዚአብሔርም፡መንጋ፡ ተማርኳልና፥ዐይኔ፡ታነባለች፥እንባንም፡ታፈሳ፟ለች።

18ለንጉሡና፡ለንጉሥ፡እናት፡ለእቴጌዪቱ፦የክብራችኹ፡አክሊል፡ከራሳችኹ፡ወርዷልና፥ተዋርዳችኹ፡ ተቀመጡ፡በል።

19የደቡብ፡ከተማዎች፡ተዘግተዋል፥የሚከፍታቸውም፡የለም፤ይሁዳ፡ዅሉ፡ተማርኳል፥ፈጽሞ፡ተማርኳል።

20ዐይናችኹን፡አንሥታችኹ፡እነዚህን፡ከሰሜን፡የሚመጡትን፡ተመልከቱ፤ለአንቺ፡የተሰጠ፡መንጋ፥የተዋበ፡ መንጋሽ፥ወዴት፡አለ፧

21ወዳጆችሽ፡እንዲኾኑ፡ያስተማርሻቸውን፡በራስሽ፡ላይ፡አለቃዎች፡ባደረጋቸው፡ጊዜ፡ምን፡ትያለሽ፧እንደ፡ ወላድ፡ሴት፡ምጥ፡አይዝሽምን፧

22በልብሽም፦እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡ስለ፡ምን፡ደረሰብኝ፧ብትዪ፥ከኀጢአትሽ፡ብዛት፡የተነሣ፡የልብስሽ፡ ዘርፍ፡ተገልጧል፡ተረከዝሽም፡ተገፏ፟ል።

23በእውኑ፡ኢትዮጵያዊ፡መልኩን፡ወይስ፡ነብር፡ዝንጕርጕርነትን፡ይለውጥ፡ዘንድ፡ይችላልን፧በዚያን፡ጊዜ፡ ክፋትን፡የለመዳችኹ፡እናንተ፡ደግሞ፡በጎ፡ለማድረግ፡ትችላላችኹ።

24ስለዚህ፥እንደሚያልፍ፡እብቅ፡በምድረ፡በዳ፡ነፋስ፡እበትናቸዋለኹ።

25ረስተሽኛልና፥በሐሰትም፡ታምነሻልና፥ዕጣሽ፡የለካኹልሽም፡ዕድል፡ፈንታ፡ይህ፡ነው፥ይላል፡ እግዚአብሔር።

26ስለዚህም፡የልብስሽን፡ዘርፍ፡በፊትሽ፡እገልጣለኹ፡ዕፍረትሽም፡ይታያል።

27አስጸያፊ፡ሥራሽን፥ምንዝርናሽን፥ማሽካካትሽን፥የግልሙትናሽንም፡መዳራት፡በኰረብታዎች፡ላይ፡ በሜዳም፡አይቻለኹ።ኢየሩሳሌም፡ሆይ፥ወዮልሽ! ለመንጻት፡እንቢ፡ብለሻል፤ይህስ፡እስከ፡መቼ፡ነው፧

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source